መደበኛ ባለገመድ ስልክዎን ወደ አገልግሎት ይመልሱ!ነፃ የመደዋወያ ደቂቃዎችን በስጦታ ያግኙ!

እስከ
ነሐሴ 23 ቀን
2014 ዓ.ም

 ረዘም ላለ ጊዜ ሳይጠቀሙበት ቀርተው ጥሪ ማድረግ እና መቀበል የማይችል ባለገመድ ስልክዎን አገልግሎቱን በነፃ በማስቀጠል ለተከታታይ 6 ወራት የሚከፋፈል 600 ደቂቃዎችን ወደ መደበኛ ስልክ እንዲሁም 120 ደቂቃዎችን ወደ ሞባይል  ነፃ ጥሪ ማድረግ የሚያስችሎትን ስጦታ ያግኙ፡፡

ደንብና ሁኔታዎች

  • የመደበኛ ባለገመድ ስልክዎን ለአገልግሎት በድጋሜ ለማስጀመር አቅራቢያዎ የሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከልን ይጎብኙ፡፡
  • አዲስ የባለገመድ መደበኛ ስልክ ቀፎ ለመግዛት 160 ብር የሚከፍሉ ሲሆን የተበላሸ የስልክ ቀፎ ካሎት 100 ብር ብቻ በመክፈል በአዲስ ቀፎ መቀየር ይችላሉ፡፡
  • አገልግሎቱ ሲቀጠል የሚቀርቡት ነፃ የጥሪ ደቂቃዎች ከመለቀቃቸው በፊት ያልተከፈለ የአገልግሎት ሂሳብ (ቢል) ካለ በአንድ ጊዜ ወይም በየወሩ መከፈል ይኖርበታል፡፡
  • ያልተጠቀሙበት ነፃ የጥሪ ደቂቃዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው ካለፈ በኋላ የማያገለግሉ ሲሆን ወደ ሶስተኛ ወገንም መተላለፍ አይችሉም፡፡
  • አገልግሎቱ ካስቀጠሉ በኋላ ሂሳብ ባለመክፈል የሚቋረጥ ከሆነ ያልከፈሉበት ወር ነፃ የጥሪ ደቂቃዎች የማይለቀቁ ሲሆን በድጋሜ ሂሳብዎን ከፍለው የሚያስቀጥሉ ከሆነ ስጦታዎቹም በድጋሜ የሚቀርቡ ይሆናል፡፡