መደበኛ ባለገመድ ስልክ + መደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ኮምቦ

በኮምቦ ሁለት አገልግሎቶችን በአንድ መስመር ያግኙ!

ደንብና ሁኔታዎች

 • የግለሰብ ደንበኞች ብቻ ለአገልግሎቱ ብቁ ናቸው፡፡
 • የአንድ ወር የመደበኛ ብሮድባንድ ክፍያ ላይ የ8% ቅናሽ በማድረግ በ12 ወራት ከፍለው እንዲያጠናቅቁ የተደረገ ሲሆን ይህም ተግባራዊ እንዲሆን የአገልግሎት ቁጥሩ መቋረጥ የለበትም፡፡
 • ነባር መደበኛ ባለገመድ ስልክ ያለው ደንበኛ መደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት መመዝገብ ከፈለገ የሞደም 50% በመክፈል 50% የሞደሙ ዋጋ ደግሞ ቅናሽ ይደረግለታል፡፡
 • ለኮምቦ አገልግሎት አዲስ መመዝገብ የሚፈልግ ደንበኛ (ለመደበኛ ባለገመድ ስልክ እና ብሮድባንድ ኢንተርኔት) የሞደም 35% በመክፈል 65% የሞደሙ ዋጋ ደግሞ ቅናሽ ይደረግለታል፡፡ በተጨማሪም የስልክ ቀፎ በነፃ የሚያገኙ ሲሆን የመጀመሪያው ወር ከመደበኛ ስልክ ወደ መደበኛ ስልክ የሚደረግ የሀገር ውስጥ ጥሪ ነፃ እና ያልተገደበ ይሆናል፡፡
 • ደንበኞች ወርሃዊ ክፍያቸውን በጊዜው ካልከፈሉ የቀረበው የቦነስ እና ቅናሽ አገልግሎት ላልከፈሉበት ወር የማይቀርብ ሲሆን ደንበኞች በቀጣይ ሲከፍሉ እና አገልግሉቱ ሲቀጥል የቀረበላቸው ቦነስ በድጋሜ የሚጀመርላቸው ይሆናል፡፡
 • የአገልግሎት ሂሳብ ማሳወቂያ እንዲሁም ከቢል መመሪያ ጋር ተዛማጅ ሂደቶች ሳይቀየሩ የሚተገበሩ ይሆናል፡፡
 • ደንበኞች መደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔትን ከነባር ባለገመድ ስልክ አገልግሎታቸው ጋር እንዲጣመር ሲያደርጉ ሁሉም የኮምቦ አገልግሎት መመሪያዎች ሳይለወጡ የሚተገበሩ ሲሆን ነገር ግን የማስተዋወቂያ ማበረታቻ ጋር የተያያዙትን አያካትትም፡፡
 • የጥሬ ገንዘብ ተቀማጭ እንዲደረግ የሚጠይቀው መመሪያ ሳይለወጥ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
 • ያልተጠቀሙበት ነፃ የጥሪ ደቂቃዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው ካለፈ በኋላ አያገለግሉም፡፡
 • የቀረቡት ነፃ አገልግሎቶች ለሀገር ውስጥ ብቻ መጠቀም የሚችሏቸው ሲሆኑ የውጭ ሀገር እና አጫጭር ቁጥሮች ላይ ጥሪ ካደረጉ በነባር የአገልግሎት ዋጋ መሰረት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
 • ደንበኞች በማስተዋወቂያ ቀናት ውስጥ ማለትም እስከ ነሐሴ 23 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ተመዝግበው ነገር ግን በተለያየ ምክንያት በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ አገልግሎቱን ማግኘት ባይችሉም ከማስተዋወቂው ቀን በኋላ አገልግሎቱን ከተፈቀደው ነፃ እና ከተደረገው ቅናሽ ጋር ያገኛሉ፡፡
 • አሁን ያለው ወርሃዊ የአገልግሎት ኪራይ ዋጋ 9 ብር ተግባራዊ ይሆናል፡፡