ይወቁ ይጠበቁ

ይወቁ ይጠበቁ

ኦንላይን ሲሆኑ ደህንነትዎን ለመጠበቅ 4 ቀላል መንገዶች

ኦንላይን የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) አጠቃቀማችን ደህንነቱ የተጠበቀ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህንን ለማረጋገጥ እና መረጃዎቻችንን ከዘራፊዎች ለመጠበቅ እነዚህን ቀላል መንገዶች ይከተሉ፡፡

የመረጃ ጠለፋ (phishing) ሲያጋጥም ጥቆማ ማድረግ

የመረጃ ጠለፋ (phishing) በአብዛኛው የመረጃ መንታፊዎች የሚጠቀሙት የማጭበርበሪያ ዘዴ ሲሆን ለኦንላይን ተጠቃሚዎች አሳሳች መልዕክት በመላክ ማልዌሮችን እንዲያወርዱ ወይም የግል መረጃቸውን ለዘራፊዎች አሳልፈው እንዲሰጡ የሚያደርጉበት ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት የመረጃ መንታፊዎች የአሰራር ሂደት ያልተከተለ ወይም በሚልኩት እውነት ከማይመስል የመልዕክት ይዘታቸው በመለየት ደህንነትዎን ይጠብቁ፡፡

የመረጃ ጠለፋውን በመጠቆም እና መልዕክቱን በማጥፋት ደህንነትዎን ይጠብቁ!

ጠንካራ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ

ቀላል የይለፍ ቃል በአጭበርባሪዎች በቀላሉ ተገማች ይሆናል፡፡ ለሚጠቀሟቸው ለእያንዳንዱ አካውንት ከ16 ፊደላት/ቁጥር ያላነሰ የይለፍ ቃል እንዲያስገቡ ይመከራል፡፡ ደህንነቱ የተጠበቀውን የይለፍ ቃል አስተዳደር (password manager) በመጠቀም  የይለፍ ቃል መፍጠር እና መያዝ ይችላሉ፡፡ ይህን ፕሮግራም ሲጠቀሙ የይለፍ ቃልዎን ማስታወስ ሳያስፈልግዎ የሚይዝ እንዲሁም ድረ ገፆችን ሲጠቀሙ በራሱ ይሞላልዎታል፡፡

ከሁለት ደረጃ በላይ ማረጋገጫ (multifactor authentication) ያብሩ

ከሁለት ደረጃ በላይ ማረጋገጫ የሚፈቅዱ የኦንላይን ሳይቶች ተጠቃሚ ከሆኑ አብርተው መጠቀም አይዘንጉ፡፡ ይህንን ተግባራዊ ካደረጉ የተለያዩ አካውንቶችን እና መተግበሪያዎችን ሲጠቀሙ ከይለፍ ቃል በተጨማሪ ሌላ የደህንነት መጠበቂያ ለምሳሌ በፊት ገፅታ መለያ ወይም የፅሁፍ መልዕክት ማረጋገጫ እንዲደርስዎ ማድረግ ይችላሉ፡፡

ከሁለት ደረጃ በላይ ማረጋገጫ ተጠቃሚ ሲሆኑ አካውንትዎ የመጠለፍ ዕድሉ አነስተኛ ነው!

ሶፍትዌር ያዘምኑ!

የተለያዩ መገልገያዎች፣ መተግበሪያዎች፣ እና የሶፍትዌር ፕሮግራሞች (በተለይ አንቲ ቫይረስ) ሶፍትዌሮች እንድናዘም ማሳወቂያ ሲደርሰን በፍጥነት ብንጭን ይመከራል፡፡ሶፍትዌር ስናዘምን የደህንነት ክፍተት በመድፈን መረጃችንን በተሻለ እንዲጠበቅ ያግዘናል፡፡

በቀላሉ ከስልክዎ መቼት ላይ በራሳቸው እንዲዘምኑ መፍቀድ ይችላሉ

እርስ በዕርስ መረዳዳት እንችላለን ,