በአጋርነት የሚሰጥ የክላውድ ሶሉሽን

 አሰራር ፣ የስራ ሂደት አና አስተዳደርን የሚያዘምን የተቀናጀ የኮምፒውተር መተግበሪያዎች ስብስብ ሲሆን ፤ አገልግሎቶች ወጪ ቆጣቢ ፣ ቀልጣፋ እና ምርታማ እንዲሆኑ  ያግዛል።
የዲጅታል ፋይሎችን ለማከማቸት እና ለማሰተዳደር የሚያግዝ የሶፍትዌር ስርዓት ነው። ይህ ሰርዓት በአሁናዊ  እና በትብብር መንገድ ፋይሎች ላይ የአርትዖት ፣ የማከማቸት እና የማጋራት ስራዎችን ለመከወን ያስችላል።
ፈጣን ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ የሆነ በድርጅት ውስጥ እንዲሁም ከደንበኞች ጋር  የሚደረጉ ስራ እና ገበያ ነክ መልዕክቶችን ለመቀያየር የሚያስችል የኤሌክትሮኒክስ መድረክ ነው። የራስ የሆነ የኢሜል ጎራ/መነሻ ስም (ኢሜል ዶሜን ኔም) በመጠቀም ድርጅቶች ሙያዊ ገፅታ እንዲላበሱ እና በደንበኞቻቸው ዘንድ ተአማኒነታቸው እንዲጨምር ከማድረግም ባሻገር ድርጅታዊ ምስላቸውም በዘለቄታዊነት እንዲጨምር ያግዛል።
የኤሌክትሮኒክስ የግብይት መድረክ በይነ መረብን መሠረት ያደረገ የገበያ፣ የሽያጭ፣ የመረጃ ልውውጥ እና የደንበኞች አገልግሎቶን ለመስጠት የሚያስችል የኤሌክትሮኒክስ መላ ነው።  ይህ  የግብይት መድረክ ወጪ ቆጣቢ በሆነ እና ተአማኒነትን ባተረፈ መንገድ ድርጅቶች ደንበኞቻቸውን በቀላሉ ለ 24/7 እንዲያገለግሉ ያስችላቸዋል።
ሲፒዩ ተኮር የሆኑ ሶፍትዌሮችን ወደ ስራ ለማስገባት ደንበኞች በሚፈልጉት መጠን ማዘዝ የሚችሉት ከፍተኛ የማሰላሰል አቅም ያለው ሰርቨር ነው፡፡ ደንበኞች የሰርቨሩን የማሰላሰል እና የማከማቸትን መጠን በፈለጉ ጊዜ መጨመር ይችላሉ። ይህ ሰርቨር የሚቀርበው ኢትዮ ቴሌኮም የኢንዱስትሪውን የጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ከገነባቸው ዳታ ሴንተሮች ውስጥ በሚገኙ የክላውድ መሰረተ ልማቶች ነው።
ራም ተኮር የሆኑ ሶፍትዌሮችን ወደ ስራ ለማስገባት ደንበኞች በሚፈልጉት መጠን ማዘዝ የሚችሉት ከፍተኛ የራም አቅም ያለው ሰርቨር ነው፡፡ ደንበኞች የሰርቨሩን የማሰላሰል እና የማከማቸትን መጠን በፈለጉ ጊዜ መጨመር ይችላሉ።  ይህ ሰርቨር የሚቀርበው ኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ማዕከሎች ላይ የኢንዱስትሪውን የጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ከገነባነው የክላውድ መሰረተ ልማታችን ነው።
ሶፍትዌሮችን ወደ ስራ ለማስገባት ከፍተኛ የማሰላሰል እና የማከማቸት አቅም ያለው እና ለደንበኛው ብቻ የሚመደብ (ማለትም ሌሎች ደንበኞች የማይጋሩት) ቁሳዊ/ፊዚካል ሰርቨር ነው።  ይህ ሰርቨር ተዘጋጅቶ የሚቀርበው የኢንዱስትሪውን የጥራት ደረጃ ከጠበቀ ከኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ማዕከል ነው።
cloud-backup
በየሰዓቱ፣ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ ወይም በየወሩ (ወይም የእነዚህ ማናቸውም ጥምረት) በታቀደ መልኩ ለመጠባበቂያ በክላውድ ሰርቨሮች ላይ ያሉ መረጃዎችን ቅጂ ለማከማቸት የሚያስችል አገልግሎት ነው። ይህን በማድረግ ደንበኞች የወሳኝ መረጃዎቻቸውን ደህንነት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጠብቁ ያስችላቸዋል።
ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል፤ በደንበኛ ፍላጎት የማከማቸት መጠኑ ማደግ የሚችል የኤችዲዲ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ማከማቻ ነው። ማከማቻው የሚቀርበው ኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ማዕከሎች ላይ የኢንዱስትሪውን የጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ከገነባነው የክላውድ መሰረተ ልማታችን ነው።
ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ፤ በደንበኛ ፍላጎት የማከማቸት መጠኑ ማደግ የሚችል የኤስኤስዲ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ማከማቻ ነው። ማከማቻው የሚቀርበው ኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ማዕከሎች ላይ የኢንዱስትሪውን የጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ከገነባነው የክላውድ መሰረተ ልማታችን ነው።
የክላውድ ሰርቨሮችን ከበይነ መረብ ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ፤ የመከላከል አቅሙ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተመሰከረለት እንዲሁም ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የፋየርዎል ስርአት ነው።
የክላውድ ሰርቨሮችን ቢሮዎ ከሚገኝ የኔትዎርክ መሰረተ ልማት ወይም ከሚፈልጉት ሌላ ቦታ ሆነው ምስጢራዊነቱ እንደተጠበቀ ለመጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ነው።