ለቴሌብር አገልግሎት እንዴት መመዝገብ ይቻላል?

ለቴሌብር አገልግሎት ይመዘገቡ የ15 ብር ቦነስ/ጉርሻ/ስጦታ ያግኙ!

የቴሌብር አካውንት በቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ ሲከፍቱ 70 ሜ.ባ ነጻ የዳታ ስጦታ ያገኛሉ፡፡

                                                        የቴሌብር ደንበኝነት ደረጃዎች እና የመመዝገቢያ መስፈርቶች

 1. ደረጃ 1 ደንበኞች

የደረጃ 1 አካውንት ደንበኞች ማስቀመጥ የሚገባቸው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን 5,000 ብር ሲሆን፣ በቀን የተፈቀደ የገንዘብ ግብይት እንቅስቃሴ መጠን ደግሞ 1,000 ነው፡፡ በተጨማሪም አጠቃላይ ወርሃዊ የተፈቀደ የግብይት እንቅስቃሴ ሂሳብ ገደብ መጠን 10,000 ብር ነው፡፡

     የምዝገባ መስፈርቶች

 • የአመልካቹ ሙሉ ስም ወይም የአካውንት ስም
 • የአመልካቹ የትውልድ ቦታና ቀን
 • የአመልካቹ የሞባይል ቁጥር
 • አመልካቹ በቅርቡ የተነሳው ፎቶ
 • አመልካቹ አሁን የሚኖርበት አድራሻ
 • አመልካቹ ከዚህ በፊት የቴሌብር አካውንት ባለው ሰው መተዋወቅ ወይም መቅረብ አለበት
 1. ደረጃ 2 ደንበኞች

 

የደረጃ 2 አካውንት ደንበኞች ማስቀመጥ የሚገባቸው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን 20,000 ብር ሲሆን፣ በቀን የተፈቀደ የገንዘብ ግብይት እንቅስቃሴ መጠን ደግሞ 5,000 ነው፡፡ በተጨማሪም አጠቃላይ ወርሃዊ የተፈቀደ የግብይት እንቅስቃሴ ሂሳብ ገደብ መጠን 40,000 ብር ነው፡፡

     የምዝገባ መስፈርቶች

 • የአመልካቹ መታወቂያ
 • የአመልካቹ ሙሉ ስም ወይም የአካውንት ስም
 • የአመልካቹ የትውልድ ቦታና ቀን
 • የአመልካቹ የሞባይል ቁጥር
 • አመልካቹ በቅርቡ የተነሳው ፎቶ
 • አመልካቹ አሁን የሚኖርበት አድራሻ
 1. ደረጃ 3 ደንበኞች

የደረጃ 3 አካውንት ደንበኞች ማስቀመጥ የሚገባቸው ከፍተኛው የገንዘብ መጠን 30,000 ብር ሲሆን፣ በቀን የተፈቀደ የገንዘብ ግብይት እንቅስቃሴ መጠን ደግሞ 8,000 ነው፡፡ በተጨማሪም አጠቃላይ ወርሃዊ የተፈቀደ የግብይት እንቅስቃሴ ሂሳብ ገደብ መጠን 60,000 ብር ነው፡፡

      የምዝገባ መስፈርቶች

 • የአካውንቱ ባለቤት መታወቂያ
 • የአመልካቹ ሙሉ ስም ወይም የአካውንት ስም
 • የአመልካቹ የትውልድ ቀን
 • የአመልካቹ የሞባይል ቁጥር
 • አመልካቹ በቅርቡ የተነሳው ፎቶ
 • አመልካቹ አሁን የሚኖርበት አድራሻ
 • የንግድ ፈቃድ
 • የሞባይል ቁጥር
 • የሲም ካርድ መለያ ወይም ሴሪያል ቁጥር
 • አድራሻ (የመኖሪያ ቦታ፣ ዋና ከተማ፣ መንገድ፣ ፖስታ ሳጥን ቁጥር)
 • አጭር ቁጥር
 • የድርጅቱ ስም
 • ክልል
 • አድራሻ (ከተማ፣ ዋና ከተማ)
 • የፖስታ ሳጥን ቁጥር

ü  የፈራሚው ስምü  የፈራሚው የሞባይል ቁጥርü  የፈራሚው ኢ-ሜይል

 • የንግድ ፈቃድ
 • የሞባይል ቁጥር
 • የሲም ካርድ መለያ ወይም ሴሪያል ቁጥር
 • አድራሻ
 • የህጋዊ ወኪሉ መታወቂያ
 • ኦሪጅናል የፍቃድ ሰነድ
 • የምዝገባ ቅጽ
 • የውክልና ደብዳቤ
 • የተወካይ መታወቂያ
 • የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር

ለግለሰብ የቴሌብር ደንበኝነት ምዝገባ ከዚህ በታች የተጠቀሱትና የታደሱ መታወቂያዎች ተቀባይነት አላቸው፡፡

 • ህጋዊ የቀበሌ መታወቂያ
 • ህጋዊ ጉዞ ሰነድ ወይም ፓስፖርት
 • ህጋዊ የግብር ከፋይነት መታወቂያ
 • ህጋዊ የመንጃ ፈቃድ
 • የተማሪ መታወቂያ
 • የሰራተኛ መታወቂያ

የቃላት ትርጉም

 • ቴሌብር፡- የሞባይል ስልክ ቁጥርን በመጠቀም ግብይት መፈጸም፣ ገንዘብ መስቀመጥ፣ መላክ እና መቀበል የሚያስችል አገልግሎት ነው።
 • ዋና ወኪል (Master Agent)፡- የቴብር አገልግሎትን ለመስጠት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ህጋዊ ስምምነት ያለውና ኢትዮ ቴሌኮምን ወክሎ ወይም የውክልና አገልግሎት ለደንበኞች የሚሰጥ አካል ወይም ድርጅት ሲሆን ኢትዮ ቴሌኮምን ወክሎ ከወኪሎቹ ጋር የአገልግሎት ለመስጠት የውል ስምምነት ያደርጋል፡፡
 • ወኪል፡- የኤጀንሲ የቢዘዝነስ አገልግሎትን ለማስተባበር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የውል ስምምነት ያለውና ኢትዮ ቴሌኮም ስምና ውክልና መመሪያዎችን ተከትሎ እና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ህጎችን መሰረት አገልግሎት የሚሰጥ አካል ወይም ተቋም ነው።
 • ገንዘብ ማስገባት፡- ይህ ሂደት ተጠቃሚው አካል ገንዘቡን በኤሌክትሮኒክስ የግብይት ሥርዓት ወደ አካውንቱ በማስገባት ያለውን የተቀማጭ ገንዘብ መጠን መጨመር ነው።
 • ገንዘብ ማውጣት፡- ይህም ተጠቃሚው አካል በቴሌብር ያከማቸውን ገንዘብ ለአገልግሎት ክፍያ በማዋል ወይም ወደ ሌላ አካውንት በማስተላለፍ የነበረውን ተቀማጭ ገንዘብ መጠን መቀነስ ወይም መጨረስ ነው፡፡
 • የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ፡- ተቀማጭ የተደረገው የገንዘብ ዋጋ ወይም እሴት በተጠቃሚው አካል ተቀባይነቱን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ሲያሟላ ነው።
 • የኢትዮጵያን ብር በሚጠቀሙ አካላት ተቀባይነቱ ሲረጋገጥ
 • ገንዘቡ ህጋዊ ካደረገው አካል ይልቅ ሰዎች እንደመገበያያነት ለመጠቀም ሲቀበሉት
 • በኢትዮጵያ ብር ከሚከናወን የኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ጋር እኩል ዋጋ ሲኖረው
 • በኤሌክትሮኒክ መሳሪያ ገንዘቡን ማስቀመጥ ሲቻል

ለቴሌብር አገልግሎት እንዴት መመዝገብ ይቻላል?

ለቴሌብር አገልግሎት ለመመዝገብ ስልክዎትን በመጠቀም በሞባይል መተግበሪያ ወይም በቴሌብር አጭር ቁጥር አገልግሎትን በመጠቀም አልያም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል በአካል በመቅረብ እንዲሁም በህጋዊ ወኪሎች ወይም በአጋር የባንክ ቅርንጫቾች መመዝገብ ይችላሉ፡፡

 • “አዲስ አካውንት” የሚለውን ይምረጡ
 • “ፈጣን አካውንት ይክፈቱ” ወይም “በራስ አገዝ አካውንት ይክፈቱ” የሚለውን ይምረጡ
 • የሞባይል ቁጥርዎን ያስገቡና “ማረጋገጫ ቁጥር ያግኙ” የሚለውን ይጫኑ
 • ቀጥሎ ባለ 6 አሃዝ የማረጋገጫ ቁጥር በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል
 • የደረስዎትን የማረጋገጫ ቁጥር ያስገቡና “ይቀጥሉ“ የሚለውን ይጫኑ
 • ቀጥሎ ከታች የተዘረዘሩትን የግል መረጃዎች እንዲሞሉ ይጠየቃሉ
  • ማእረግ
  • የመታወቂያ አይነት
  • የመታወቂያ ቁጥር
  • ስም፤ የአባት ስም፤ የአያት ስም
  • ጾታ
  • የትውልድ ቀን
  • መጠቀም የሚፈልጉበት ቋንቋ
 • የግል መረጃዎን ሞልተው ካረጋገጡ በኋላ “ያስገቡ“ የሚለውን ይጫኑ
 • በመቀጠል በአጭር ፅሁፍ መልዕክት የሚስጥር መለያ ቁጥር (PIN) ይደርስዎታል
 • የደረስዎትን የሚስጥር መለያ ቁጥር (PIN) በመጠቀም ይግቡ የሚለውን ይጫኑ
 • አገልግሎቱን ለማስጀመር የሚስጥር መለያ ቁጥሩን በአዲስ ይቀይሩ (የራስዎትን የሚስጥር ቁጥር ይጠቀሙ) እና ለመጨረስ የሚለውን ይጫኑ
 • ከዚያም የቴሌብር አካውንትዎ በተሳካ ሁኔታ መጀመሩን የሚገልፅ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡
 • ወደ *127# ይደውሉ
 • ለመመዝገብ 1 ቁጥርን ይላኩ
 • የተላከልዎትን የግብዣ መለያ ቁጥር ሲያስገቡ ወይም የ # ሲልኩ ወደ ቀጣይ ያልፋሉ 
 • በድጋሜ *127# ይደውሉ
 • ለማስጀመር ዜሮ (0) ይላኩ
 • ቋንቋ ይምረጡ
 • በ 127 የደረስዎትን የሚስጥር ቁጥር በማስገባት በአዲስ የራስዎ ቁጥር ይቀይሩ
 • ከዚያም የቴሌብር አካውንትዎ በተሳካ ሁኔታ መጀመሩን የሚገልፅ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡

አገልግሎቱን እንዲሰጡ ህጋዊ ፈቃድ በተሰጣቸው ወኪሎች ወይም በሽያጭ ማዕከላችን ለመመዝገብ:

  • በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ወኪሎች ወይም የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል በአካል በመቅረብ
  • አገልግሎት ላይ ያለ የስልክ ቁጥርዎን እና የራስዎ ስለመሆኑ ለወኪሉ ማረጋጫ በማቅረብ (ማንነትዎን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ)

እስከ 10 ለሚደርሱ ግለሰቦች ቴሌብር እንዲመዘገቡ በመጋበዝ 300 ፍሌክሲ ዩኒት ስጦታ ለራስዎ ያግኙ!

ግብዣ እንዴት መላክ ይቻላል

ሀ) የቴሌብር የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም

 1. የመተግበሪያው መግቢያ ገፅ ላይ ከታች በቀኝ በኩል የሚያገኘውን “የኔ አካውንት” የሚለውን ይክፈቱ
 2.  “ጓደኛ ለመጋበዝ” የሚለውም ይምረጡ
 3. የጓደኛዎን የሞባይል ቁጥር በማስገባት “ላክ” የሚለውን ይምረጡ

ለ) አጭር ቁጥር በመጠቀም መጋበዝ

 1. *127# ይደውሉ
 2. # ምልክትን በማስገባት ‘ጓደኛ ለመጋበዝ’ የሚለውን (ቁጥር 9) ይምረጡ
 3. የጓደኛዎትን የሞባይል ስልክ ቁጥር ያስገቡ
 4. የሚስጥር ቁጥርዎትን ያስገቡ
 5. ‘እሺ’ የሚለውን በመምረጥ ያስገቡትን ስልክ ያረጋግጡ

የማረጋገጫ መልዕክት በ 127 ይደርስዎታል፡፡

ተጨማሪ መረጃ:- ስጦታው የሚያገለግለው ለ48 ሰዓታት ብቻ ነው፡፡