ክላውድ ቴሌፎን/ቨርቹዋል ፒ.ቢ.ኤክስ ምን ማለት ነው?የፒ.ቢ.ኤክስ ሳጥን እና ኬብል ማዘጋጀት ሳይጠበቅብዎ የኢንተርኔት እና ክላውድ አገልግሎትን በመጠቀም ከደንበኞችዎ፣ አጋሮችዎ እና ሰራተኞችዎ ጋር የሚደረግ የስልክ ግንኙነት በቦታ እና በጊዜ ያልተገደበ እንዲሆን የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡ ጥቅሞች ደህንነቱ በተጠበቀ የዳታ ማዕከል መሰረት አድርጎ የቀረበ አገልግሎት በመሆኑ ያልተቋረጠ አገልግሎት አለው ከመደበኛው የፒ.ቢ.ኤክስ አገልግሎት ጋር ሲነፃፀር ወጪ ቆጣቢ በኢንተርኔት የቀረበ አገልግሎት በመሆኑ የጥገና ወጪ የሌለበት ሰራተኞችዎ በስራ ገበታቸው፣ በጉዞ ላይ እንዲሁም በቤታቸው ውስጥ ሁነው የደንበኞችን ጥሪ እንዲቀበሉ እና እንዲያስተላልፉ ያግዛል የጥሪ ቅጂዎች እና ዝርዝር መረጃዎች እንዲያገኙ ስለሚረዳ በቀላሉ መረጃ መተንተን እና አፈፃፀምን መገምገም ይችላሉ ለአጠቃቀም ቀላል የእንኳን ደህና መጡ ሰላምታ፣ የድምፅ መልዕክት ወደ ኢሜል መላክ እንዲሁም ጥሪ ማስተላለፍ የሚያስችል በመሆኑ ድርጅቶች ገፅታቸውን እና የደንበኞች አገልግሎታቸውን ለማጎበት ያግዛል መደበኛ ጥቅል የተጠቃሚ የጥሪ ሁኔታ ጥሪ ማስተላለፍ አይቪአር ማውጫ የድምፅ መልዕክት የጥሪ ዝረዝር መረጃ ጥሪ ማስተዳደር ጥሪ ማዘዋወር የጥሪ ማቆያ የጥሪ ፓርኪንግ የፍጥነት መደወያ ያልተገደበ ማከማቻ ሞባይል መተግበሪያ ወርሃዊ ክፍያ በኤክስቴሽን፡- 200 ብርEmail us your purchase request! Standard Package Plusአድቫንስድ ጥቅልየመደበኛ ጥቅሎችን እንዲሁም የጥሪ ኮንፈረንስ ሪሰፕሽኒስት የማቆያ ሙዚቃ የጥሪ ማሰራጫ የጥሪ ቅጂ የጥሪ መለያ መስጠት ከጥሪ በኋላ ዳሰሳ ማስሞላት ወርሃዊ ክፍያ በኤክስቴሽን፡- 300 ብርEmail us your purchase request here! Advanced Package Plusየኮል ሴንተር ጥቅል የጥሪ ማቆያ የማስተዳደሪያ ፖርታል የአድራሻ ማውጫ የተለያዩ ሶፍትዌሮችን፣ ገፆችን እና መተግበሪያዎን ማገናኘት የጥሪ ሪማይንደር ጥሪ መገደቢያ ወርሃዊ ክፍያ ኤጀንት፡- 1500 ብርEmail us purchase request here! ደንብና ሁኔታ ለመደበኛ እና አድቫንስድ ጥቅል የሚፈቀደው አነስተኛ የፒ.ቢ.ኤክስ አገልግሎት ብዛት 5 ነው፡፡ ለኮል ሴንተር ጥቅል የሚፈቀደው አነስተኛ የኤጀንት ብዛት 2 ነው፡፡ ለመደበኛ ስልክ እና ሞባይል አገልግሎት የድምፅ ጥሪ መገልገያ በመደበኛው ታሪፍ መሰረት ይሆናል፡፡ ደንበኞች እየተገለገሉበት ያለውን ቁጥር መጠቀም ወይም አዲስ የአገልግሎት ቁጥር መጠየቅ ይችላሉ፡፡ አገልግሎቱ ቪፒኤን እና የኢንተርኔት ግንኙነትን በመጠቀም የሚቀርብ ይሆናል፡፡