ዕለታዊ እና የአንድ ሰዓት ያልተገደበ የሞባይል ጥቅል

አዲስ አገልግሎት

 • ዕለታዊ እና የአንድ ሰዓት ያልተገደበ የሞባይል ጥቅል አገልግሎት በቴሌብር፣ በማይ ኢትዮቴል እና *999# ይዘን መጥተናል፡፡

 • በቴሌብር ሲገዙ ተጨማሪ የ10% ቅናሽ ያገኛሉ


ያልተገደበ የአንድ ሰዓት ጥቅል
12 ብር
 • ፍትሃዊ የዳታ አጠቃቀም መጠን: 1 ጊ.ባ
 • ከፍትሃዊ የዳታ አጠቃቀም ፖሊሲ ትግበራ በኋላ የሚኖረው ከፍተኛው ፍጥነት: 512 ኪ.ባ/ሰከንድ
ያልተገደበ ዕለታዊ ጥቅል
55 ብር
 • ፍትሃዊ የዳታ አጠቃቀም መጠን: 5 ጊ.ባ
 • ከፍትሃዊ የዳታ አጠቃቀም ፖሊሲ ትግበራ በኋላ የሚኖረው ከፍተኛው ፍጥነት: 512 ኪ.ባ/ሰከንድ

 • አገልግሎቱ ለቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች የቀረበ ነው፡፡
 • ያልተገደበ ዳታ የፍትሃዊ የዳታ አጠቃቀም መመሪያ ተግባራዊ የሚደረግበት አገልግሎት ነው፤ ይህም ማለት የዳታ አጠቃቀምዎ ቀድሞ ከተወሰነው መጠን ላይ ሲደርስ የኢንተርኔት ፍጥነቱ እንዲቀንስ የሚደረግበት አሰራር ነው፡፡ ለምሳሌ፡ የአንድ ሰዓት ያልተገደበ የኢንተርኔት ጥቅል ገዝተው የአገልግሎት ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት የተጠቀሙት የዳታ መጠን ከ 1 ጊ.ባ በላይ ከሆነ የኢንተርኔት ፍጥነቱ ከመደበኛው ወደ 512 ኪሎ ባይት በሰከንድ ዝቅ እንዲል ይደረጋል ማለት ነው፡፡
 • የጥቅል አገልግሎቱን በኢትዮ ገበታ (*999#)፣ ማይ ኢትዮቴል የሞባይል መተግበሪያ እና በቴሌብር ያገኙታል፡፡
 • ሁሉም ነባር የጥቅል አገልግሎት ደንብና ሁኔታዎች ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡

ዕለታዊ ያልተገደበ የድምፅ ጥቅል

ዕለታዊ ያልተገደበ የድምፅ ጥቅል
35 ብር
 • ዕለታዊ ያልተገደበ የድምፅ ጥቅል