የደስታ ሰዓት የሞባይል ጥቅል

የደስታ ሰዓት የሞባይል ጥቅል

በደስታ ሰዓት ጥቅል  መልዕክት ሲላላኩና ሲደዋወሉ እንዲሁም ዳታ ሲጠቀሙ ደስስስ….እንደሚሎት አንጠራጠርም፡፡

በቴሌብር ሲገዙ ተጨማሪ 10% ያገኛሉ!

  • ሁሉም የቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ሞባይል ተጠቃሚዎች ለአገልግሎቱ መመዝገብና መጠቀም ይችላሉ፡፡
  • ደንበኞች ለደስታ ሰዓት ሞባይል ጥቅል በማንኛውም ጊዜ መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን ለመጠቀም ግን በተጠቀሱት የመጠቀሚያ ሰዓት ብቻ ይሆናል፡፡
  • የደስታ ምሳ ጥቅል ገዝተው ያልተጠቀሙበት ቀሪ የጥቅል መጠን ካለ በቀጣዩ ቀን በጥቅሉ የመጠቀሚያ ሰዓት ሳይባክንብዎ መገልገል ይችላሉ፡፡ ቀጣዩ ቀን እሁድ ከሆነ ደግሞ ያልተጠቀሙበትን ቀሪ የደስታ ምሳ ጥቅል እሁድ ጠዋት ከ4፡00 – 5፡00 ባለው ጊዜ መጠቀም ይችላሉ፡፡
  • የደስታ ሌሊት ዳታ ጥቅል የገዙ ደንበኞች የመጠቀሚያ ጊዜው ከመጠናቀቁ በፊት የአንድ ሰዓት ያልተገደበ ዳታ ጥቅል መግዛት አይችሉም፡፡ ነገር ግን የአንድ ሰዓት ያልተገደበ ዳታ ጥቅል የገዙ ደንበኞች የደስታ ሌሊት ጥቅልን መግዛት ይችላሉ፡፡
  • የተገደቡ የሌሊት ዳታ ጥቅሎችን የገዙ ደንበኞች የደስታ ሌሊት ዳታ ጥቅል መመዝገብ የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን የደስታ ሌሊት ሞባይል ጥቅልን የገዙ ደንበኞች ሌሎች የሌሊት ዳታ ጥቅሎችን መግዛተ አይችሉም፡፡
  • ደንበኞች ለራሳቸው መግዛት እንዲሁም ለሌሎች በስጦታ ገዝተው መላክ ይችላሉ፡፡
  • ሁሉም የደስታ ሰዓት ጥቅሎች ወደ ሌላ ጥቅል መቀየር ወይም ወደ ሌሎች ማስተላለፍ አይቻልም፡፡
  • ነባር የጥቅል ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡