ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ.

ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
  1. ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከኤክስትራ ቴንደር (www.extratenders.com)፣አፍሮ ቴንደር (www.afrotender.com) እና ቱ መርካቶ ዶት ኮም (www.2Merkato.com) ድህረገፅ በመግባት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በቴሌ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተሽከርካሪዎቹን ለማየት ተጫራቾች መታወቂያቸውን በመያዝ አቃቂ በሚገኘው ኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ከታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህስስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ-አርብ) ማየት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በመዝጊያው ቀን ታህስስ 30 እስከ ጠዋት 6፡30 ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለስ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአንድ ተሽከርካሪ የመግዣ ዋጋ 10% (አስር በመቶ)  በቴሌ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የጨረታው ሰነድ ገቢ የሚደረገው አቃቂ በሚገኘው ኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት አቃቂ በሚገኘው ኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ይከፈታል፡፡
  5. ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
                          ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

ኢትዮ ቴሌኮም ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ፡ የተለያዩ የኔትዎርክ እና የፖወር ዕቃዎችን፣ የእንጨት ፖሎችን እና ኮምቦልቻ የሚገኘውን የፖል መቀቀያ ማሽን፣አዳዲስ ኘሪንተሮችን፣ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ እና ኤል.ኢ.ዲ መብራቶች እና የእሳት ማጥፍያዎችን፣ ቁርጥራጭ የኤች.ዲ.ፒ ዳክቶች፣ ብረታ ብረቶች፣ ካርቶኖች እና ወረቀቶችን፣ የእንጨት ማሸጊያ ሳጥኖች፣ አጣናዎች እና ፓሌቶችን ባሉበትሁኔታበጨረታአወዳድሮመሸጥይፈልጋል፡፡

Read More »
Archives