ደንብና ሁኔታዎች

ከውጭ ሀገራት የአየር ሰዓት እና ጥቅል ለሚቀበሉ ደንበኞቻችን ከዚህ በታች የተጠቀሱት ዝርዝር ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡

  • ከ99 ብር ጀምሮ የአየር ሰዓት እንዲሁም የሞባይል ጥቅል ስጦታ ከውጭ ሃገራት ሲቀበሉ የተቀበሉትን 200% በስጦታ ያገኛሉ
  • ስጦታው የሚያገለግለው ለ15 ቀናት ብቻ ነው፡፡
  • ስጦታውን ለቴሌኮም ፍጆታ ማለትም ለመደወል፣ መልዕክት ለመላክ እና ዳታ ለመጠቀም ወይም ለራስዎ ጥቅል በመግዛት መጠቀም ያስችላል፡፡
  • ስጦታውን ወደ ሌላ ደንበኛ ማስተላለፍ አይችሉም
  • በስጦታው ወደ አጭር ቁጥር ለመደወል፣ ዓለም አቀፍ ጥሪ ለማድረግ፣ ለሮሚንግ አገልግሎት ለመጠቀም፣ ለሌላ ደንበኛ ጥቅል በስጦታ ለመላክ እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ውጪ ለመደዋወል አያገለግልም፡፡
  • ስለተቀበሉት ስጦታ የማሳወቂያ መልዕክት በስልክዎ የሚደርስዎ ይሆናል፡፡
  • እስከ ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከውጭ ሃገራት ጥቅል እና አየር ሰዓት በመቀበል 200% በስጦታ ማግኘት ይችላሉ፡፡