ያገለገሉ ጄኔሬተሮች፤ማንሆል ኮንክሪት ማምረቻ ማሽን፤አሳንሰር ሊፍቶች (Elevetors) እና መፈተሻ በሮች (Human Walkthrough) ሽያጭ ጨረታ ቁጥር FD/A&FR/03/2016 ማስታወቂያ ኢትዮ ቴሌኮም የተለያዩ ሞዴል ያላቸውን ያገለገሉ ጄኔሬተሮች፤ማንሆል ኮንክሪት ማምረቻ ማሽን፤አሳንሰር ሊፍቶች (Elevetors) እና መፈተሻ በሮች (Human Walkthrough) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
  • ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ከሚያዝያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአፍሮ ቴንደር (www.afrotender.com) እና መርካቶ ዶት ኮም (www.2merkato.com) ድህረ ገጽ (web site) የማይመለስ ብር 300  (ሦስት መቶ) በ ቴሌ ብር በመክፈል መግዛትይችላሉ   ፡፡
  • ንብረቶቹን ለማየት ተጫራቾች መታወቂያቸውን በመያዝ አቃቂ እና መስቀል ፍላወር በሚገኘው የኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ከሚያዝያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት (ከሰኞ-አርብ) ማየት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በመዝጊያው ቀን ሚያዝያ 16 ጠዋት 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማየት የሚችሉ ይሆናል፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ የሚገዙበትን እቃ የግዥ ዋጋ አሥር በመቶ 10% (አስር ፐርሰንት) የሚመለስ በቴሌ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የጨረታው ሰነድ ገቢ የሚደረገው ትራኮን ታወር በሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም 10ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ትራኮን ታወር 10ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
  • ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
                                           ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives