የሐጅ ሮሚንግ ጥቅል ከኢትዮጵያ እስላማዊ ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት (EIASC) ጋር በመተባበር፣ለሐጅ ተጓዦች የቀረበ ልዩ የሐጅ ሮሚንግ ጥቅል!የእስልምና መሠረት ወደሆነው ሳዑዲ ዐረቢያ፤ የሐጅ ሃይማኖታዊ ሥርዐት ለመፈጸም የሚያቀኑ ምእመናን፤ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጅ የሐጅ ጥቅሎችን ከተጨማሪ ድምፅና የዳታ ሮሚንግ ጋር በኢትዮ ገበታ (*999#)ና በቴሌብር ሱፐርአፕ። ጉዞ የሚደረግበት አገር የጥቅል ዐይነት ዳታድምፅዋጋ ወደ ኢትዮጵያ ለመደወል ጥሪ ለመቀበል 1 ጊባ——1290 ብር 2 ጊባ——2590 ብርሳዑዲ ዐረቢያ፣ መካ—100 ደቂቃ100 ደቂቃ4350 ብር 500 ሜባ50 ደቂቃ50 ደቂቃ2800 ብር 1 ጊባ100 ደቂቃ100 ደቂቃ5650 ብር ሐጅ ሮሚንግ መመሪያ (Terms and Conditions) ሐጅ ሮሚንግ መመሪያ (Terms and Conditions) ብቁነት፤አገልግሎቱ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት (EIASC) በኩል ለሐጅ ጉዞ የተመዘገቡ የስልክ ቁጥሮች ብቻ ይሆናል።የግዢ አማራጮች፤የሐጅ ሮሚንግ ጥቅሎችን በኢትዮ ገበታ፣ ወደ 127 በመደወል፣ በቴሌብር ሱፐርአፕ በኩልና በማይ ኢትዮ አፕ፣ እንዲሁም በአገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን በኩል መግዛት ይችላሉ።ጥቅሉን፤ ለራስና ሌሎች ሐጅ ተጓዦች በስጦታ መላክ መግዛት ይቻላል።የቆይታ ጊዜ፤የሐጅ ሮሚንግ ጥቅሎች እስከ ሰኔ 23፣ 2017 ዓ.ም. ድረስ ይቆያሉ።እያንዳንዱ ጥቅል ከተገዛበት ጀምሮ ለ 30 ቀናት ያገለግላል።ከተፈቀደው ጥቅል በላይ ስላለው አጠቃቀም፤የሐጅ ሮሚንግ ጥቅሉ 75 ደቂቃ ወደ ኢትዮጵያ መደወልና 70 ደቂቃ ሲደወልላቸዉ መቀበልን ያካትታል።የሐጅ ጥቅሎች፤ ለሳዑዲ ቁጥሮች፣ ከሳዑዲ ዐረቢያ ወደ ዓለም አቀፍ መዳረሻ ጥሪዎች፣ ዳታዎችንና አጭር የጽሑፍ መልእክቶች መጠቀም አያካትትም።ወደ መዳረሻ የሚደረጉ ጥሪዎች አሁን ባለው የሮሚንግ ታሪፍ መሠረት የሚከፈሉ ይሆናል።ወቅታዊ የታሪፍ መረጃ ለማግኘት የኢትዮ ቴሌኮም ድረ-ገጽን (Roaming Service–www.ethiotelecom.et) ይጎብኙ።ለሮሚንግ አገልግሎት በቁ ለመሆን፤ በEIASC ዝርዝር ላይ የሚገኙ የቅድመ ክፍያ ደንበኞች ለሮሚንግ አገልግሎት ሲመዘገቡ ወዲያውኑ ያገኛሉ።በEIASC ዝርዝር ላይ ያልተመዘገቡ የቅድመ ክፍያ ደንበኞች፤ በ8994 አጭር የጽሑፍ መልእክት ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ (በፌስቡክ፣ ኤክ፣ ቴሌግራም፣ ዋትስአፕ፣ ሊንክዲንና በኢንስታግራም) መድረኮቻችን ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ።ለድኅረ ክፍያ ደንበኞች፣ ወደ ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከል በመቅረብ 10,000 (ዐሥር ሺህ) ብር በማስያዝ አገልግሎቱን ማስጀመር ይኖርባቸዋል። የደንበኛ ድጋፍ፤ለማንኛውም የድጋፍ ጥያቄ፣ በነጻ +251 116 111111 ይደውሉ ወይም በWhatsApp በ +251 994 000000 ይፃፉ።