ዘኔክሰስ
ዘኔክሰስ በተመጣጣኝ ዋጋ ክላውድን በመጠቀም የሚሰራ፣ አስተማማኝ የስማርት ሞባይል ስልክ ገጽታ ያለው ሲሆን የክላውድ ኮምፒውቲንግ አቅምን በማካተት የዋጋ ተመጣጣኝነትን ያረጋግጣል። ብራንዱ ሰውን ማዕከል ያደረገ እና በቴሌክላውድ የሚሰራ ሲሆን የሚከተሉት መፍትሄዎች ያሉት ነው፡-
- የፕሮሰሲንግ አቅምን ወደ ቴሌክላውድ (teleCloud) በማዘዋወር የዲቫይሶችን ዋጋ ተመጣጣኝ ያደርጋል፣
- ለተጠቃሚ ምቹ የሆኑ (keypad + touchscreen) በመጠቀም የተጠቃሚዎችን ልምድ ያቀላል፣
- ለገጠራማ እና አነስተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ላላቸው አካባቢዎች ረጅም የባትሪ ዕድሜ አለው፣
- በተገጠመ የቴሌስቶሬጅ (teleStorage) አማካኝነት የፋይል ማከማቻ ገደቦችን ያስወግዳል፣
- እንደ ቴሌብር፣ የትምህርት ይዘት፣ ሚዲያዎች ያሉ ወሳኝ አፕሊኬሽኖችን ተጭኖባቸዋል፣
- ከሁሉም በላይ ደግሞ የመጀመሪያ ጊዜ ተጠቃሚዎች በቀላሉ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ያስችላል፡፡
ዘኔክሰስ ስማርት ስልክ ላይ የሚገኙ ወሳኝ መተግበሪያዎችን በክላውድ አማካይነት በማቅረብ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የዲጂታል ተጠቃሚነት ተግዳሮት የሆነውን የዋጋ ውድነት በዘላቂነት በመፍታት የDigital-First ማኅበረሰቦችን እውን ለማድረግ ያስችላል።
ክላውድን መሰረት ያደረጉ የዘኔክሰስ ስማርት ስልኮች
ኢትዮ ቴሌኮም ዘኔክሰስ ዲቫይሶችን ከመደበኛዎቹ ስማርት ስልኮች አንጻር በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ለተጠቃሚዎች አስፈላጊ የሆኑ የስማርት ስልክ አገልግሎቶችን በሙሉ ይሰጣል። ይህንንም የበለጠ ለማሳደግና ሁሉም ኢትዮጵያውያን የዲጂታልና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ክላውድን መሰረት ባደረገው ዘኔክሰስ ላይ ቴሌብርን አካትቶ አቅርቧል።
ይፋ የተደረጉት ስማርት ዲቫይሶች ዘኔክሰስ 127 ላይት (znexus 127 Lite)፣ ዘኔክሰስ 131 ላይት (znexus 131 Lite) እና ዘኔክሰስ 2028 ላይት (znexus 2028 Lite) ሞዴሎች ሲሆኑ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ጌሞች፣ አጫጭር ፊልሞች እና ዜናዎች የመሳሰሉ መተግበሪያዎች በክላውድ በማቅረብ ተጠቃሚዎች በቀላሉ የስማርት ስልክ (smartphone-lite) ተሞክሮ እንዲያገኙ ያስችላሉ።
ሞባይል
ዘኔክሰስ L127
| Memory | 128MB RAM + 64MB storage |
|---|---|
| Size | 130 x 54 x 15mm |
| Network | 2G/3G/4G |
| Camera | 0.3MP Rear |
| Battery | 2000mAh |
| Features | FM Wireless, Wi-Fi, Hotspot |
| Pre-Installed apps | Facebook, YouTube, TikTok, telebirr |
| Storage | Free 2GB telecloud storage |
ነፃ 2 ጊ.ባ ዳታ ለ3 ወራት
ዘኔክሰስ L131
| Memory | 128MB RAM + 64MB storage |
|---|---|
| Size | 135.5 x 58 x 14.5mm |
| Network | 2G/3G/4G |
| Camera | 0.3MP Rear |
| Battery | 2000mAh |
| Features | FM Wireless, Wi-Fi, Hotspot |
| Storage | Free 2GB telecloud storage |
| Pre-Installed apps | Facebook, YouTube, TikTok, telebirr |
ነፃ 2 ጊ.ባ ዳታ ለ3 ወራት
ዘኔክሰስ L2028
| Memory | 128MB RAM + 64MB storage |
|---|---|
| Size | 140 x 62 x 14mm |
| Network | 2G/3G/4G |
| Camera | 0.3MP Rear |
| Battery | 2500mAh |
| Features | FM Wireless, Wi-Fi, Hotspot, Bluetooth |
| Storage | Free 2GB telecloud storage |
| Pre-Installed apps | Facebook, YouTube, TikTok, telebirr |
ነፃ 2 ጊ.ባ ዳታ ለ3 ወራት
ዘኔክሰስ ክላውድ ወርክስፔስ ሶሉሽን
የክላውድ ወርክስፔስ ሶሉሽን ቢዝነሶችን፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ቨርቹዋል ዴስክቶፖችን እና አፕሊኬሽኖችን ከማንኛውም ዲቫይስ ጋር ለማገናኘት የሚያስችል ሲሆን፣ ይህም የአይ.ቲ ወጪዎችን በመቀነስ ምርታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ይህ ሶሉሽን የሚቀርበው በዘኔክሰስ ፓድስ (PADs)፣ ላፕቶፖች እና ቲን ክሊያንትስ (thin clients) ማለትም ዘኔክሰስ R2025 Rise-Cloud Tab፣ ዘኔክሰስ E2025 ፕሮ ክላውድ ላፕቶፕ፣ ዘኔክሰስ E131 ፕሮ ክላውድ ላፕቶፕ እና ዘኔክሰስ E2025 አልትራ ቲን ክሊያንትስ (ultra thin clients thin client) አማካኝነት ነው።
ዋና ዋና ጥቅሞች፡
- የዳታ ደህንነት፡ አስተማማኝ ስቶሬጅ እና ፕሮሰሲንግ በክላውድ ውስጥ መኖር፣
- ሊያድግ የሚችልበት ሪሶርስ፡ ድርጅቶች ሲያድጉ፣ ሪሶርሳቸውን በቀላሉ ለማስፋፋት፣
- ወጪ ቆጣቢነት፡ “በተጠቀምንበት በመጠን ለመክፈል” (Pay-as-you-go) የሚያስችል በመሆኑ የካፒታል ወጪዎችን ይቀንሳል፣
- በራሱ ጊዜ ማዘመን እና መረጃዎችን ማስቀመጥ፣ የአይ.ቲ ማኔጅመንትን ለማቅለል እና የቢዝነስ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ፣
- ከፍተኛ ደህንነት፡ ለከፍተኛ ጥበቃ ባለ ብዙ ሽፋን ኢንክሪፕሽን እና የመዳረሻ ቁጥጥር (access control) ያለው መሆኑ የሚሉ ናቸው፡፡
ታብሌት R2025 ራይዝ ክላውድ ፓድ
-
MT6771/ Octa Core Up to 1.6GHz
MT6771/ Octa Core Up to 1.6GHz
-
4 ጊ.ባ + 64 ጊ.ባ
4 ጊ.ባ + 64 ጊ.ባ
-
10.1 ኢንች INCELL 1200*1920 ጥራት ያለው ስክሪን
10.1 ኢንች INCELL 1200*1920 ጥራት ያለው ስክሪን
-
5 ሜጋፒክስል የፊት ካሜራ
5 ሜጋፒክስል የፊት ካሜራ
-
13 ሜጋፒክስል የኋላ ካሜራ ከአውቶ ፎከስ ጋር
13 ሜጋፒክስል የኋላ ካሜራ ከአውቶ ፎከስ ጋር
-
5000 ሚሊ አምፒር አወር ሊነቀል የሚችል ባትሪ ጋር
5000 ሚሊ አምፒር አወር ሊነቀል የሚችል ባትሪ ጋር
-
ኃይል መሙያ Type C (5V 2A)
ኃይል መሙያ Type C (5V 2A)
-
ሁለት ድምጽ ማጉያዎች
ሁለት ድምጽ ማጉያዎች
-
አንድሮይድ 13.0 ኦፐሬቲንግ ሲስተም
አንድሮይድ 13.0 ኦፐሬቲንግ ሲስተም
-
ሁለት ናኖ ሲም ካርዶች + ከሚሞሪ ካርድ ማስገቢያ
ሁለት ናኖ ሲም ካርዶች + ከሚሞሪ ካርድ ማስገቢያ
-
የፊት መክፈቻ
የፊት መክፈቻ
-
ዋይ-ፋይ የሚቀበል
ዋይ-ፋይ የሚቀበል
-
ብሉቱዝ 5.0
ብሉቱዝ 5.0
E2025 ፕሮ ክላውድ ላፕቶፕ (ሞዴል ACN21S-140P3-CS)
| Platform | AMD Bacelo-Refresh |
|---|---|
| LCD | 14” 16:9,FHD IPS |
| Thermal | 15W, Single FAN |
| Material | Full plastic |
| Weight | <1.4Kg |
| Dimension | 322.6*210.2*19.8mm (Plastic) |
| Open Angle | 175±3° |
| Memory | SO-DIMM, DDR4*2, 8GB integrated |
| Storage | 1*M.2 2280 SSD, 256GB PCIE 3 |
| Camera | 2MP |
| Battery | 7.6V/6000mAh_45.6Wh |
| OS | Windows11 |
| MB I/O | 2*USB Type-C 1*USB Type-A 1*HDMI |
| DB I/O | 1*Audio 2*USB Type-A 1*RJ45 1*Micro SD |
E131 ፕሮ ክላውድ ላፕቶፕ (DN21C-140P3-CS)
| Platform | Intel ADL-U I3-1215U |
|---|---|
| LCD | 14” 16:9,FHD IPS |
| Thermal | 15W, Single FAN |
| Material | Full plastic |
| Weight | <1.4Kg |
| Dimension | 322.6*210.2*19.8mm (Plastic) |
| Open Angle | 175±3° |
| Memory | SO-DIMM, DDR4*2, 8GB integrated |
| Storage | 1*M.2 2280 SSD, 256GB PCIE 3 |
| Camera | 2MP |
| Battery | 7.6V/6000mAh_45.6Wh |
| OS | Windows11 |
| MB I/O | 2*USB Type-C 1*USB Type-A 1*HDMI |
| DB I/O | 1*Audio 2*USB Type-A 1*RJ45 1*Micro SD |
ሚኖተር M2453F
| Size | 23.8 inch |
|---|---|
| Resolution | 1920x1080 |
| Refresh rate | 120Hz (overclock 144Hz) |
| Panel Type | TIANMA IPS |
| Aspect Ratio | 6:09 |
| Brightness | 250cd/M² |
| Color Support | 16.7M (8bit) |
| Color Gamut | 72% DCI-P3 / 99% sRGB |
| View Angle | 178/178 |
| Response Time | 5ms (OD) |
| Connections | VGA, HDMI, Audio Out |
| VESA mount | 75x75mm |
| Tilt | -5° ~ 15° |
| New weight | 2.79KG |
ቲን ክላይንት HT3300
| Dimensions | 170*136*34mm |
|---|---|
| Mali | G52 2EE |
| CPU | RK3568 4 Core ARM CPUA55 |
| Flash | 8GB |
| Ethernet | 1000M RJ-45 |
| Display | HDMI Output *2 |
| Power Supply | 12V/2A DC-in |
| USB interface | o USB2.0 interface *2 o USB3.0 interface * |
| Certification | CE, CB, REAHC, RoHS, WEEE |
| Audio | o 3.5mm headphone/Mic o 2-in-1 jack, CTIA int'l standard |
| Accessories | o Power cable, power adapter (12V/3A), Vertical bracket, wall bracket |
በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ
ጠቅላላ የዘኔክሰስ ስልክ ጥያቄዎች
- ዘኔክሰስ ክላውድ መደበኛ ስልክ ተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያገኛሉ፡
- ቴሌብርን፣ ቴሌስቶሬጅን፣ የማኅበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎችን መጠቀም፣ እንዲሁም ወቅታዊ ዜናዎችን መከታተል ያስችላል፤
- የምንገለገልባቸው መተግበሪያዎች ቀድመው ስለተጫኑ እንዳዲስ መጫንና ማዘመን ሳይጠበቀብን መጠቀም ያስችላል፤
- ረጅም የባትሪ እድሜ አለው።
- በተመጣጣኝ ዋጋ የ4ጂ ኢንተርኔትን መጠቀም ማስቻሉ፤
- እንደ ቴሌብር የመሳሰሉ አስፈላጊ መተግበሪዎች መኖሩ፤
- ከሌሎች መደበኛ ስልኮች በተሻል፤ በቀላሉ የስልካችንን ኪቦርድ በመጠቀም ብቻ መቆጣጠር ማስቻሉ፤
- በቴሌስቶሬጅ አማካኝነት የማከማቻ እጥረትን በማስቀረት ሰፊ የዳታ ማስቀመጫ ቦታ ማስገኘቱ፤
- በገጠራማና አነስተኛ የኃይል እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ረጅም የባትሪ እድሜ ያለው በመሆኑ ከሌሎች መደበኛ ስልኮች ይለየዋል።
- ዳታዎችን፤ ኢትዮ ቴሌኮም በሚያስተዳድረው በክላውድ ሰርቨር ላይ ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ያከማቻል።
- በትክክል! ዘኔክሰስ ክላውድ መደበኛ ስልክ የተደፈው ደኅንነቱን በተጠበቀና አስተማማኝ በሆነ፤ ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌሮች ባሉት ሰርቨር ላይ ነው።
- በትክክል! ተጠቃሚ ዳታዎችን በክላውዱ ላይ ቀደም ብለው ጭነውት ከሆነ፤ ስልኩ እንኳን ቢጠፋ እንደገና መልሶ ማግኘትና መጠቀም ይችላል።
- የዘኔክሰስ ክላውድ ክፍሎችን ደኅንነት ለማጠናከር የተዘረጋ ቴክኖሎጂን ይጠቀማሉ። ተጠቃሚዎች የተወሰነ ሚና በመጫወት በውስብስብ፣ ልዩና ያልተደጋገመ የይለፍ ቃልን በመጠቀም የይለፍ ቃላቸውን ደኅንነት ማጠናከር እንዲችሉ ይረዳል።
- ቀደም ብለው የተጫኑ እንደ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ጎግል፣ ቀላል ጌሞች፣ እንደ BBCና CNN የመሳሰሉ የዜና አውታሮችን፤ እንዲሁም የቴሌብር መተግበሪያዎ መጠቀም ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮ ቴሌኮም ወደፊት አዳዲስ መተግበሪያዎን ያካትታል።
- የድምፅ ጥራቱ በ HD Voice ቴክኖሎጂ የተደገፈ በመሆኑ፤ ከመደበኛ ስልክ ጋር ሲነጻጸር የበለጠ ጥርት ያለ ድምፅን ያቀርባል። በተጨማሪም፤ የሚያስተጋባ፣ የድምፅ ጫጫታ፣ የተቆራረጠ ድምፆችን በማስወገድ የተሻለ የጥሪ ተመክሮን ይሰጣል።
- በትክክል! የዘኔክሰስ ክላውድ ስልክን በደንብ ለመጠቀም ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ አልያም የዋይ ፋይ ኢንተርኔት ግንኙነትና ሲም ካርድ አስፈላጊ ነው።
- የዘኔክሰስ ማከማቻ መጠን የተገደበ ስለሆነ፤ ከዩቲዩብ ላይ ቪዲዮችን ማውረድ አይቻልም። ነገር ግን፤ ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚፈልጓቸውን ይዘቶች በቀጥታ በቀላሉ ማየት ይችላሉ።
- ዘኔክሰስ ክላውድ ስልክ በተመጣጣኝ ዋጋ አስፈላጊ የሆኑ፤ የተወሰኑ የስማርት ስልክ ባሕርያትን ለመስጠት የተነደፉ እንጂ፤ ልክ እንደ ስማርት ስልክ ለከፍተኛ የፎቶግራፊ ወይም ቪዲዮ ቀረፃ ዐቅማቸው የተገደበ ነው።
- አዎ! ኢትዮ ቴሌኮም የዘኔክሰስ ስልክ ተደራሽነት ለማድረግ ተመጣጣኝና የተለየ የኢንተርኔት ጥቅልን በቅርቡ ያስተዋውቃል። በተጨማሪም፤ ደንበኞች የዘኔክሰስ ስልክን ሲገዙ ለሦስት ወራት ነጻ የኢንተርኔት ጥቅልን ያገኛሉ።
- ለዘኔክሰስ ሆነ ሌሎች የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶች ወደ ጥሪ ማዕከሎቻችን መደወል፤ ዲጂታል የደንበኞች አገልግሎት ማዕከልን መጠቀም ወይም አቅራቢዎ ወደሚገኙ የቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመምጣት ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።
- ኢትዮ ቴሌኮም ለዘኔከሰስ ስልኮች የስድስት ወራት ዋስትና ይሰጣል። በመሆኑም ገጠራማ አካባቢ የሚገኙ ደንበኞች፤ አቅራቢያቸው የሚገኙ የቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በመጎብኘት፤ አልያም ስልካቸው ከገዙበት የመሸጫ መደብር ለዋስትና ጥያቄዎችና ዝርዝር ጉዳዮች ማነጋገር ይችላሉ።
ከቴሌብር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች፤
- በአጭር ቁጥር (*127#) አማካኝት፤ ቴሌብርን በማንኛውም መደበኛ ስልኮች ላይ መጠቀም ይቻላል። ነገር ግን፤ ዘኔክሰስ ስልክ ቀድሞ የተጫነ የቴሌብር መተግበሪያ ስላለው፤ የተፈቀዱትን አገልግሎቶች ማግኘት ይቻላል።
- አይቻልም! ቴሌብርን ለመጠቀም የተረጋጋ የ4ጂ ኢንተርኔት ያስፈልጋል፤ ሆኖም ከኢንተርኔው ውጪ ያሉ አገልግሎቶች በአጭር ቁጥር (*127#) መጠቀም ይቻላል።
- አዎ! በመደበኛ የተቀመጠው የቴሌብር የገንዘብ ዝውውር መጠን ገደብ በዘኔክሰስ ክላውድ ስልክ ላይም ተግባራዊ ይደረጋል።
- የሚከተሉትን የቴሌብር አገልግሎቶችን በዘኔክሰስ ስልክ ማግኘት ይቻላል፡
- ገንዘብ መላክና መቀበል፣
- ጥሬ ገንዘብ ማውጣት፣
- ለነጋዴዎች ክፍያ መፈጸም፣
- QR ኮድ ክፍያ መፈጸም፣
- የአየር ሰዓት/ጥቅሎችን መግዛትና
- የወኃዊ የፍጆታ/ቢል/ ክፍያ መፈጸም፣ (የመብራት፣ የውኃ፣ የቴሌኮም ቢል ወዘተ.)
- በቀጥታ ወደ 127 በደመወል የቴሌብር መለያዎን ማዘጋት ይችላሉ። አዲስ ስልክ ከያዙ በኋላ እንደ ገና መለያዎን በማስከፈት መለያዎትን በማስከፈት ማስጀመር ያገኛሉ።
- ወደ 127 በደመወል፤ ማንነትዎ ባስመዘገቡት ዝርዝር መሠረት ከተረጋገጠ በኋላ የይለፍ ቃልዎን እንደ ገና ማግኘት ይችላሉ።
- እንደዚህ ዐይነት አጋጣሚዎች በመተግበሪያው ወይም ኔትወርክ ምክንያት ሊከሰቱ ይችላሉ። በመሆኑም ችግሩን ለምቅረፍ፡ የ4ጂ ኢንተርኔትዎ አስተማማኝ መሆኑን ያረጋግጡ፤ ወደ 127 በመደወል የጥሪ ማዕከል ሠራተኞችን ያግኙ፤ እንዲሁም የቴሌብር ማኅበራዊ ሚዲያ ድጋፍ ሰጪዎች ጋር ይወያዩ ወይም 126 በመጠቀም አጭር የጽሑፍ መልእክት ይላኩ፤ አልያም አቅራቢያዎ የሚገኙ የኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎት መስጫ ማዕከልን ይጎብኙ።
- እንደዚህ ዐይነት ሁኔታዎች በኔትዎርና ሰርቨሩ ምክንያት ሊከሠቱ ይችላሉ፤ በቀጥታ ወደ 127 በመደወል፤ አልያም የቴሌብር ማኅበራዊ ሚዲያ ድጋፍ ሰጪዎች ጋር በመወያየት ወይም ወደ 126 አጭር የጽሑፍ መልእክት በመላክ ማሳወቅ ይችላሉ።
- በትክክል! ወደ ዘኔክሰስ ክላውድ ስልክ ቴሌብር የሚጠቀሙበትን ሲም ካርድ በማስገባት፤ በስልክዎ ላይ በሚላክልዎ የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል(OTP) በማረጋገጥና የምስጢር ቁጥርዎን አስገብተው ካጠናቀቁ በኋላ የቴሌብር አገልግሎቶችን መጠቀም ይችላሉ።
- አይደለም! በአሁኑ ጊዜ ዘኔክሰስ ስልክ ስድስት አገልግሎቶችን ብቻ መጠቀም የሚያስችል ሲሆን (18ተኛ ጥያቄን ይመልከቱ)፤ ወደ ፊት ተደራሽነቱን በማስፋት ተጨማሪ አገልግሎቶች የሚካተቱ ይሆናል።
- በዘኔክሰስ ስልክ ቴሌብርን መጠቀም የሚቻለው እርስዎ በተመዘገቡበት ሲም ካርድ ብቻ በመሆኑ፤ በሌላ ሰው መለያ መጠቀም አያስቻልም።
ከቴሌስቶሬጅ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች
- አይቻልም! የተረጋጋ የ4ጂ ኢንተርኔት ያስፈልጋል።
- በቴሌስቶሬጅ ሁለት ቋንቋዎችን የሚያስጠቀም ሲሆን፤ የአማርኛና እንግሊዘኛ ቋንቋ ናቸው።
- አዎ! ባሁኑ ጊዜ መጠቀም የሚቻለው እስክ 2 ጊጋባይት የዳታ መጠን ያላቸውን ዳታዎችን ብቻ ነው። ሆኖም፤ በቅርቡ ተጨማሪ አገልግሎቶች ይካተታሉ።
- ወዲያውኑ በሌላ ዘኔክሰስ ክላውድ ስልክ በመጠቀም የክላውድ መረጃዎትንና የይለፍ ቃልዎን መቀየር ይችላሉ።
- ተጠቃሚው በቴሌ ማከማቻ መድረክ ላይ የሚገኘውን "የይለፍ ቃል ረሳሁ" የሚለውን አማራጭ በመጠቀም የይለፍ ቃላቸውን ዳግም ማስጀመር ይችላሉ።