አዋሽ ባንክ የፋይናንስ አገልግሎት
ኢትዮ ቴሌኮም ከአዋሽ ባንክ ጋር በመተባበር፤ ከምቹ የክፍያ አማራጭ ጋር ፈጣንና አስተማማኝ የዲጂታል ብድርና ቁጠባ አገልግሎት በቴሌብር አቀረበ።
Micro Credit and Saving Products
ጥላ አነስተኛ ክሬዲት
መግለጫ
ለግለሰብ ደንበኞች የቀረበ የክሬዲት አገልግሎት ሲሆን፤ በቴሌብር የግብይት መጠን መሠረት እስከ 75 ቀናት በሚቆይ የመክፈያ ጊዜ አማራጭ፣ ከ500 እስከ 16,000 ብር ድረስ ክሬዲት እንዲያገኙ ያስችላል።
| የክሬዲት ዐይነት | የክሬዲት መጠን | የአገልግሎት | ዕለታዊ | ቅጣት |
|---|---|---|---|---|
| 15 ቀናት | 500 – 5,000 | 1.25% | 0.50% to 1.20% | 0.11% |
| 40 ቀናት | 1,200 – 12,000 | 4.50% | 0.50% to 1.20% | 0.11% |
| 75 ቀናት | 1,200 – 16,000 | 6.50% | 0.50% to 1.20% | 0.11% |
ጥላ አነስተኛ ቁጠባ
መግለጫ
ደንበኞች የፈለጉትን የገንዘብ መጠን በቴሌብር አማካኝነት ከወለድ ነጻ ወይም 7.15% ወለድ ያለው የቁጠባ ዐይነት በመጠቀም በየትኛውም ቦታ ሆነው እንዲቆጥቡ ያስችላቸዋል።
ዝግ ቁጠባ
ይህ አገልግሎት፤ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ የፈለጉትን የገንዘብ መጠን በማስገባት ከፍተኛ ወለድ እንዲያገኙ ያስችላል።
| ዝግ የቁጠና ጊዜያት | የወለድ መጠን (%) |
|---|---|
| 3 ወራት | 7.50% |
| 6 ወራት | 7.75% |
| 9 ወራት | 8.00% |
| 12 ወራት | 8.50% |
የብድር አገልግሎት፡ ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች
መግለጫ
በዚህ የብርድ አገልግሎት፤ ለጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ተቋማት፣ ለነጋዴዎችና ለወኪሎች ያለ ምንም ማስያዣ በቴሌብር የግብይት መጠናቸው መሠረት እስከ 500,000 ብር የሚደርስ ክሬዲት እንዲያገኙ ይረዳል።
| የመክፈያ ጊዜ | አነስተኛ | ከፍተኛ | ወርኃዊ ክፍያ | የመክፈያ ዙር | ቅጣት |
|---|---|---|---|---|---|
| በ1-ወር | 1,000 | 30,000 | 9% | 1 | 0.11% |
| በ3-ወራት | 30,001 | 150,000 | 8% | 3 | 0.11% |
| በ4--ወራት | 150,001 | 250,000 | 7% | 4 | 0.11% |
| በ6--ወራት | 250,001 | 500,000 | 6% | 6 | 0.11% |
ጥላ የደመወዝ ክሬዲት
መግለጫ
በዚህ የክሬዲት አማራጭ፤ ወርኃዊ ደመወዛቸው በቴሌብር ወይም በአዋሽ ባንክ በኩል የሚከፈላቸው የግልና መንግሥት ተቋማት፤ በተራዘመ የ16 ወራት ክፍያ እስክ 1 ሚሊየን ብር (ከስድስት ወራት ደመወዛቸው ጋር የሚስተካከል) እንዲያገኙ ይፈቅዳል።
| የክሬዲት ዐይነት | የክሬዲት መጠን | የአገልግሎት | ዕለታዊ | የመክፈያ ጊዜ | ቅጣት |
|---|---|---|---|---|---|
| 6 ወራት ደመወዝ | 1,000 – 1,000,000 | 22% | 1.38% | 16 ወራት | 0.11% |
የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ለማስጀመር
- በቴሌብር የአዋሽ ባንክ የክሬዲትና ቁጠባ አገልግሎት ለማግኘት፦
- በመተግበሪያው ላይ የተቀመጡ ደንብና ሁኔታዎችን ማንበብ፣ መረዳትና መቀበል፤
- እድሜ 18 ዓመትና ከዚያ በላይ መሆን፤
- እየሠራ የሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ፤
- የዳታ/የድምፅ/የመልእክት የመሳሰሉ የኢትዮ ቴሌኮምና ቴሌብር ምርቶችን በመደበኛ መጠቀም፤
- የቴሌብርና የቴሌኮም የደንበኝነት ቆይታ 3 ወርና ከዚያ በላይ መሆን፤
- አገልግሎቱን ለማግኘት የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያን ማወረድ ወይም *127# አጭር ቁጥርን መጠቀም ይችላሉ።
መሠረታዊ መሥፈርቶች
- የደንበኛ የመበደር አቅም፤ ደንበኛው የክሬዲት ክፍያ አገልግሎት ለመጠቀም ጥያቄ ካቀረበበት ቀን በፊት ባደረገው የ6 ወራት የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴና በቴሌኮም አጠቃቀም ይወሰናል።
- ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶችና የገንዘብ ልውውጥ የደንበኛ የብደር አቅምን ለማስላት ይውላሉ።
- የአየር ሰዓት/ጥቅል ወይም ትኬት መግዛት፣
- የምርትና አገልግሎት ግብይት በቴሌብር መፈጸም፣
- የቢል፣ የፍጆታ፣ ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ፣
- የጅምላ ክፍያ (ደመወዝ፣ ሴፍቲኔት…)
- ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል
- የቁጠባ አገልግሎት፣ ገንዘብ መላክ/መቀበል
- የቴሌኮም ፍጆታ (ድምፅ፣ ዳታ ወይም መልእክት) ወዘተ.
- የደመወዝ ክሬዲት ለማግኘት ወርኃዊ ደሞዝን በቴሌብር አማካኝነት መቀበል ናቸው።
የክሬዲት መጠን እና ክፍያ
- በሚፈቀደው ዝቅተኛና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።
- የጠየቁትን የክሬዲት መጠን እንዳገኙ በዋናው የቴሌብር ሒሳብዎ (ኤሌክትሮኒክ-ገንዘብ አካውንት) ላይ ገቢ ይደረጋል።
- ሌላ ክሬዲት ለማግኘት፤ መጀመሪያ ቀድመው የወሰዱትን ክሬዲት መክፈል ይጠበቅብዎታል።
- ያለብዎትን ክሬዲት በከፊል ወይም በሙሉ መክፈል ይችላሉ።
- ያለብዎን ክሬዲት በቀነ ገደቡ ውስጥ የማይከፍሉ ከሆነ ተጨማሪ የቅጣት ክፍያ ይከፍላሉ።
- ጊዜው ካለፈ በኋላ ተበዳሪው በሰዓቱ ካልከፈለ አበዳሪው የቀረውን የክሬዲት መጠን ከቴሌብር ሒሳቡ ወዲያው ተቀናሽ የሚደረግ ሲሆን እንዲሁም ከኮሚሽን አካውንት ይወሰዳል።