አርዲ የእርስዎ ኢትዮ ቴሌኮም ቻትቦት እና ረዳት
አርዲ ለእርስዎ ድጋፍ የምትሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ቻትቦት ስትሆን፤ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ከቴሌኮምና ቴሌብር አገልግሎት ጋር ተያያዥነት ያለው ድጋፍ እንዲያገኙ ታስችላለች። አርዲ አንድ ጊዜ የስልክዎን በተን በመጫን ብቻ፤ የእርስዎን የኢትዮ ቴሌኮም ተሞክሮ ለማሻሻል በቀን ለ24 ሰዓታት፣ በሳምንት 7 ቀናት ትሠራለች። እንዲሁም፤ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በቀላሉ እንዲገናኙ በማስቻል፤ ዘወትር ቆይታዎን ታረጋግጣለች።
እንዴት መጠቀም ይቻላል?
አርዲን በመጠቀም የሚከተሉትን አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ፡
- አካውንትዎን ለማስተዳደር
- የቀረቡትን ምርትና አገልግሎቶች ለማየት
- የፒዩኬ (PUK) ቁጥር ለማግኘት
- ለአገልግሎቶች ለመምዝገብ/ለማቋረጥ
- የአየር ሰዓት ለማስተላለፍ
- ጥቅሎችን ለመቀየር
- ቢላችንን ለማወቅ
- የአሻም ቴሌ አገልግሎትን ለማስተዳደር
- ለቴሌብር አገልግሎት
- ከቴሌብር ገንዘብ ዝውውር ጋር የተያያዙ ድጋፎችን
- የተመዘገብናቸው ለማረጋገጥ
- ከወኪሎች ድጋፍ ለማግኘት
- የአየር ሰዓት ለመሙላት ታስችላለች