Terms & Conditions - Ethio Telecom

የአየር ሰዓት/ጥቅል ከውጭ አገራት ሲልኩ ከተጨማሪ 15% ቦነስ ጋር እናደርሳለን!

ለእያንዳንዱ ከውጭ አገር ለሚላክልዎ አየር ሰዓትና ጥቅል ሙሌት ከ15% ቦነስ ጋር ለተቀባዩ እናደርሳለን፡፡ በዚህም ተቀባዩ ተጨማሪ የሚነጋገሩበት ደቂቃና የተራዘመ የዳታ አጠቃቀም እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

Ethio Remit
Boss Revolution
Eze Call
Ding
Reloadly
Prepay Nation

ደንብና ሁኔታዎች

  • በአጋሮቻችን በኩል ከውጭ አገራት የአየር ሰዓት እና/ወይም ጥቅል ሲላክልዎ ለ15% ቦነሱ ብቁ ይሆናሉ፡፡
  • በሚያገኙት ተጨማሪ የአየር ሰዓት ስጦታ ወደ ሌላ የአገር ውስጥ ኔትወርክ መደወል፣ ዓለም አቀፍ ጥሪ ማድረግ፣ ወደ አጭር ቁጥር መደወል፣ ለሮሚንግ እና የሞባይል ጥቅል ለራስዎ ወይም በስጦታ መላክ ይችላሉ፡፡
  • ነገር ግን ስጦታዎቹ ወደ ሌላ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡
  • ቦነሱ የሚያገለግለው ለ15 ቀናት ብቻ ነው፡፡
  • ይህ አገልግሎት የሚቆየው እስከ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ነው፡፡