የማስታወቂያ ማሳመሪያ አገልግሎት!

በእያንዳንዱ ጥሪዎች ድርጅትዎን በማስተዋወቅ ብራንድዎን ይገንቡ!

በሚደረግልዎ ጥሪዎች ያሉትን የቆይታ ጊዜያት ወደ ማስታወቂያ መንገድ በመለወጥ፤ የድርጅትዎን መልእክት ልዩ በመሆነ መልኩ ወደ ደንበኞች ያድረሱ።

የማስታወቂያ ጥሪ ማሳመሪያ፤

  • ድርጅቶች ምርትና አገልግሎታቸውን በተመረጡ ጥሪ ማሳመሪያዎች በኩል ማስተዋወቅ የሚያስችላቸው አገልግሎት ነው።
  • የራሳቸውን የማስታወቂያ ይዘት በመጠቀም የተመዘገቡ ደንበኞቻቸው ጥሪዎችን በሚቀበሉበት ጊዜ ደዋዩ ማስታወቂያውን ማዳመጥ ይችላል፤ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ በምላሹ የድምፅና ዳታ ጥቅሎችን በሽልማት መልክ ያገኛል።

የማስታወቂያ ጥሪ ማሳመሪያ መለያ፡

  • ድርጅቶች የራሳቸውን ማስታወቂያማበጀት ያስችላቸዋል፤
  • በቀጥታለታለመላቸው ደንበኞች በመድረስ ምርትና አገልግሎታቸውን እንዲያስተዋውቁ ይረዳል፤
  • በራስአገዝ ፖርታል በመመራት ማስታወቂያዎችን መጫንና ማስተዳደር ይችላሉ።
  • የብራንድታይታነትን በማሳደግ ንግዳቸውን እንዲያስፋፉ ያግዛቸዋል።

በእነዚህ ይመዝገቡ፤

  • በአጭርቁጥር፡ ወደ 822 ከደወሉ በኋል 8 መጫን፣
  • የድርጅት ደንበኞች በኢሜል፡ Enterprise@ethiotelecom.et /  Enterprise.Customer@ethiotelecom.et ወይም

ቸርችል ጎዳና፣ ከሊሴ ገ/ማርያም ት/ት አጠገብ በሚገኘው ፕሪሚየም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላችንን ይጎብኙ!

    1. ለአገልግሎቱብቁ ለመሆን፤
    • ሁሉም የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች፤ እንዲሁም ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ማስተዋወቅ የሚፈልጉ የድርጅት ደንበኞች ለአገልግሎቱ በመመዝገብ ብቁ መሆን ይችላሉ።
      1. ስለሚቀርቡ ይዘቶች፤
    • ድርጅቶች የሚለቁት የማስታወቂያ ይዘቶች ከ60 ሰከንድ ባልበለጠ በwav ፎርማት ማቅረብ አለባቸው።
    • የማስታወቂያ ይዘቶች ደንበኞች እንዲጠቀሙበት ከመጫናቸው በፊት፤ በኢትዮ ቴሌኮም  መመዝገብና መጽደቅ አለባቸው።
      1. ክፍያዎችን በተመለከት:
    • ከፍያዎች የሚፈጸሙት በቅድም ክፍያ አገልግሎት መሠረት ሲሆን በተመዘገበው የሞባይል ወይም መለያ ቁጥር መፈጸም አለባቸው።
    • ነባር ተጠቃሚዎች ወደ ማስታወቂያ ጥሪ ማሳመሪያ ሲቀይሩ የአገልግሎት ክፍያውን የአስተዋዋቂው ድርጅት የሚከፈል ይሆናል።
    • ነባርተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ወደ ማስታወቂያ ጥሪ ማሳመሪያ ሲቀይሩ የአገልግሎቱን ክፍያ አስተዋዋቂው ድርጅት ይከፈላል።
    • ሁሉም ክፍያዎች ቫትን ያካተቱ ናቸው።
      1. ሽልማቶችን በተመለከተ:
    • ተመዝጋቢዎች የማስታወቂያ ጥሪን ማሳመሪያን እንደ ጥሪ መለያ አድረገው ሲጠቀሙ የድምፅ፣ የዳታና ጥምር ጥቅሎች በሽልማት መልክ ይቀበላሉ።
    • ጥቅሎቱን ለሌላ ተጠቃሚ መተላለፍ አይቻልም፤ ሆንም ግን ወደ ሌሎች አገልግሎቶች መቀየር ይቻላል።
    • በማበረታቻ ጥቅል ላይ የዋሉ ክፍያዎች ተመላሽ አይደረጉም።ሆኖም እስከ ስድስት ወራት ድረስ በማራዘም መጠቀም ይችላሉ።
      1. ማሳወቂያ፡
    • ተጠቃሚዎች የማበረታቻ ጥቅሎችን በተመለከተ በአጭር የጽሑፍ መልእክት ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።
    • ሁሉንም የማስታወቂያ ጥሪ ማሳመሪያ አገልግሎቶችን በተመለከተ በ9316 አጭር ቁጥር በኩል ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።
    • ቀድመው የነበሩየጥሪ ማሳመሪያ አገልግሎት መመሪያዎችና የንግድ ደንቦች የጸኑ ናቸው።