የተለያዩ የኢትዮ ቴሌኮም የራስ አገዝ ቻናሎችን ተጠቅመው የተለያዩ የሚከፈልባቸውንም ሆነ የማይከፈልባቸው አገልግሎቶችን ስለተጠቀሙ ብቻ በየቀኑ ለሽልማት ብቁ የሚያደርጎትን የሎተሪ ዕጣ የሚያገኙ ሲሆን በየዕለቱ ከሚሸለሙት 100 ሰዎች ውስጥ አንዱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ የሽልማት መርሃ ግብር የሚቆየው እስከ ኅዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን በአጠቃላይ 8994 ደንበኞችን ይሸለማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሽልማቱ የሚሆነው 127 ደቂቃ እና ቀነ ደብ የሌለው 999 ሜ.ባ ዳታ ጥቅል ይሆናል፡፡
አሸናፊዎች ሁሌም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ በሚወጣ ዕጣ የሚለዩ ይሆናል፡፡