የወዳጅ ዘመድ ጥቅል​

የወዳጅ ዘመድ ጥቅል

የራስዎን የወዳጅ ዘመድ ቡድን በመፍጠር የገዙትን የሞባይል ጥቅል ማጋራት የሚችሉበት አገልግሎት ነው።

የወዳጅ ዘመድ ጥቅልን የተሻሻለውን የማይ ኢትዮቴል መተግበሪያን በማውረድ ወይም በአካል በአቅራቢያዎ በሚገኝ የሸያጭ ማእከላችን በመገኘት መመስረት ይችላሉ።

ያጋሩ

የድምጽ

  • 2500 ደቂቃ. የሃገር ውስጥ ጥሪ
  • ሲዩጂ ኪራይ 25 ብር በወር
  • እስከ አምስት (5) አባላት
20% ቅናሽ

ዳታ

  • 20 ጊ.ባ ሞባይል ዳታ
  • ሲዩጂ ኪራይ 25 ብር በወር
  • እስከ አምስት (5) አባላት
30% ቅናሽ

ድምጽ + ዳታ

  • 2500 ደቂቃ. የሃገር ውስጥ ጥሪ
  • 20 ጊ.ባ ሞባይል ዳታ
  • ሲዩጂ ኪራይ 25 ብር በወር
20% ቅናሽ

  • ሁሉም አገልግሎት የሚሰጡ የቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ሞባይል ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • የመደበኛ ስልክ፣ ዳታ ብቻ ሲም፣ ከማሽን ወደ ማሽን እንዲሁም የሲዲ.ኤም.ኤ አገልግሎት ደንበኞች የወዳጅ ዘመድ ጥቅል ተጠቃሚ መሆን አይችሉም፡፡
  • ያልተገደበ ጥቅል ተጠቃሚዎች (የድምፅ፣ የዳታ እና የአጭር መልዕክት) አገልግሎቱን አባል ሆነው መጠቀም አይችሉም ነገር ግን መስራች ሆነው በመመዝገብ ሌሎች አባላትን በማካተት ተጠቃሚ ማድረግ ይችላሉ፡፡
  • የተለያዩ የወዳጅ ዘመድ ጥቅል አይነቶችን መስራች ሆኖ የተመዘገበው ደንበኛ  ለሌሎች አባላት በመግዛት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ይችላል፡፡ (የቡድኑ መስራች የተለያዩ የድምፅ፣ የዳታ ወይም ሁለቱንም የያዘ ጥቅል አባል ላደረጓቸው ደንበኞች ማከፋፈል ይችላል)፡፡
  • መስራቹ ቋሚ ደንበኛ መሆን ሲኖርበት ከተገዛው የጥቅል  ሀብት መጠን ከ 50% በላይ ለራሱ ብቻ መጠቀም አይችልም፡፡
  • የወዳጅ ዘመድ ጥቅል ቡድን መስራቹ በማንኛውም ጊዜ የማይ ኢትዮቴል የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም ወይም በአካል በመቅረብ ቡድን መፍጠር፣ አባላትን ማካተት፣ ማስተካከያ ማድረግ እንዲሁም አባላትን መሰረዝ ይችላል፡፡ በተጨማሪም የጥቅል ሀብቱን ለቀን፣ ለሣምንት እና ለወር ከፋፍሎ መመደብ ይችላል፡፡
  • እስከተፈቀደው የአባል መጠን (5 አባላት) ድረስ ለመመዝገብ በነፃ ሲሆን ነገር ግን ከተፈቀደው በላይ አባላትን ለማካተት በአንድ ደንበኛ 5 ብር መስራቹ የሚከፍል ይሆናል፡፡ በአንድ የወዳጅ ዘመድ ቡድን የሚፈቀደው ከፍተኛው የአባላት ብዛት መስራቹን ጨምሮ 15 ነው፡፡
  • የቡድን መስራቹ እስከ 5 አባላት ድረስ የሲ.ዩ.ጂ ኪራይ 25 ብር መክፈል ይጠበቅበታል፡
  • ለአገልግሎቱ የተመዘገበው ቁጥር ወይም የቡድኑ መስራች ለጥቅል አገልግሎቱ ወርሃዊ ኪራይ የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
  • አገልግሎቱ በየወሩ ቀጣይነት እንዲኖረው በወሩ መጀመሪያ የሞባይል መስመሩ ቅድመ ክፍያ ከሆነ በቂ ሂሳብ እንዲሁም ድህረ ክፍያ ከሆነ በቂ ተቀማጭ ሂሳብ ሊኖረው ይገባል፡፡
  • አገልግሎቱን ለማቋረጥ የማይ ኢትዮቴል የሞባይል መተግበሪያ መጠቀም ወይም በአቅራቢያ ያሉ የሽያጭ ማዕከሎቻችን መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  • ሁሉም ዋጋዎች ተ.እ.ታ ያካትታሉ፡፡