ዲቫይስ ፋይናንሲንግ

ዲቫይስ ፋይናንሲንግ ደንብ እና ሁኔታዎች

1.የውል ስምምነት
• ይህ ስምምነት (ከዚህ በኋላ "ደንቦች እና ሁኔታዎች" የሚባል) የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎትን በተመለከተ አጠቃላይ ደንብ እና ሁኔታዎች ያካትታል፡፡

• እነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኛው ተነበው ተቀባይነት ሲያገኙ (ይስማሙ የሚለውን ምርጫ ሲጫኑ) ሥራ ላይ ይውላሉ፡፡

2.ትርጓሜ
በዚህ የደንቦች እና ሁኔታዎች መረጃ ውስጥ የተዘረዘሩ ቃላት እና አባባሎች የሚከተለውን ትርጉሜ ይይዛሉ፡-

• "ኢትዮ ቴሌኮም" ማለት ክፍያ ለመፈፀም ፈቃድ ያለው የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለቴሌብር ደንበኞች ለመስጠት ስምምነት ያለው ነው፡፡

• "ቴሌብር" ማለት የሞባይል ስልክ በመጠቀም ገንዘብ ለማስቀመጥ፣ ለመላክ፣ ለመቀበል፣ አነስተኛ ክሬዲት፣ አነስተኛ ኢንሹራንስ፣ ጡረታ እና አነስተኛ ቁጠባ ወዘተ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት የንግድ ስም ነው።

• "የቴሌብር አካውንት" ማለት በቴሌብር ሲስተም ውስጥ ያለዎትን ኢሌክትሮኒክ ገንዘብ መጠን የሚገልፅ ነው፡፡
"የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት" ማለት በኢትዮ ቴሌኮም የሚሰጥ የክሬዲት አገልግሎት ሲሆን ግለሰብ የቴሌብር ደንበኞች የቴሌብር ቻናልን በመጠቀም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ውሎች እና ሁኔታዎች መሠረት የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

• "የግለሰብ ደንበኛ" ማለት በስሙ በቴሌብር አካውንት ለዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የተመዘገበ ደንበኛ ማለት ነው።

• "ኢ-ገንዘብ" ማለት እኩል መጠን ያለው ጥሬ ገንዘብን የሚወክል ደንበኛው የሚመለከተው የቴሌብር የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዋጋ ነው።

• "አንተ" ወይም "የአንተ" ማለት የግለሰብ ደንበኛ ማለት ሲሆን የግለሰቡን የግል ተወካዮች ያጠቃልላል።

• "እኛ" እና "የእኛ" ማለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም ማለት ነው፡፡

• "የማስተላለፊያ ክፍያዎች" ማለት አነስተኛ የብድር አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎች፣ ቅጣቶች እና ሌሎች ክፍያዎች ማለት ነው። የዝውውር ዋጋ በኢትዮቴሌኮም እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውሳኔ በማንኛውም ጊዜ ሊቀየር ይችላል።

• "የአገልግሎት ክፍያ" ማለት የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ክፍያ አገልግሎትን ለመጠቀም በደንበኞች የሚከፈል የክፍያ መጠን ነው።

• "የቅጣት ክፍያ" ማለት ለዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የመጨረሻ መክፍያ ቀነ ገደቡ አልፎ ክፍያው ሲፈጸም የሚከፍል ተጨማሪ የክፍያ መጠን ነው፡፡

• "የክፍያ ቀን ገደብ" ማለት የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ክፍያ መመለሻ የጊዜ ገደብን የሚያሳይ ቀነ ገደብ ነው፡፡

• "ቀነ ገደቡ ያለፈ" ማለት የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት መመለሻ ቀነ ገደቡ ያለፈ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

• "የተበላሸ ብድር" ማለት የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ90 ቀናት ውስጥ ያልተከፈለ ክሬዲት ሲሆን በወቅቱ ባለመመለሱ እንደ ተበላሸ ብድር መሆኑን የሚያሳይ ጊዜ ነው፡፡

• "ግለሰብ" የሚለው ቃል ሁለቱንም ወንድ እና ሴትን ያካትታል:

• የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎትን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት እነዚህን ደንብ እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ በማንበብ የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎትን አጠቃቀም እና መመሪያን አንብበው ይስማሙ፡፡

• በእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ካልተስማሙ እባክዎን ከዝርዝር መምረጫ ውስጥ ሰርዝ የሚለውን ይጫኑ፤

• ደንቦችና ሁኔታዎችን እንዳነበቡ፣ እንደተረዱና እንደተቀበሉ የሚቆጠረው፡-

o ✔ "ይስማሙ" የሚለውን አማራጭ ሲጫኑ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ ተረድተው ለማክበር መስማማትዎን እንዳረጋግጡ ወይም የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎትን ለመጠቀም እንደተስማሙ ይወሰዳል

• የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ክፍያ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመተግበር እና የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ክፍያ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ በቴሌብር ሲስተም ለመጠቀም ተስማምተዋል።

• ደንብ እና ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆን በቴሌብር ፖርታል፣በቴሌብር መተግበሪያ ወይም ድህረ ገጽ ላይ ከተለቀቁበት ዕለት ጀምሮ በደንበኛው ላይ ተግባራው ይደረጋሉ፡፡

• ውሉ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ተቀባይነት ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ፣ እነዚህ ውሎች እና ሁኔታዎች በእርስዎ እና በእኛ መካከል በህጋዊ መንገድ አስገዳጅ ስምምነት ይሆናሉ። በዚህ ስምምነት ስር ያለዎትን ማንኛውንም መብት ወይም ግዴታ ለሌላ ለማንም ማስተላለፍ አይፈቀድልዎትም።

• ደንበኛው ገንዘቡን ለህጋዊ አላማ ለማዋል ተስምቷል።

3. የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ክፍያ አገልግሎትን ለማስጀመር
የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለማስጀመር ቢያንስ።

• ማንበብ እና መፃፍ ደንብ የሚችል በተጨማሪም ይህንን ደንብ እና ሁኔታዎች የተረዳ ብሎም የተቀበለ

• 18 አመት እና ከዚያ በላይ

• አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ

• የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ

• የቴሌኮም የደንበኝነት ቆይታ 5 አመት እና የቴሌብር የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን አለበት

4. የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለማግኘት መሰረታዊ መስፈርቶች
• የደንበኛ የመበደር አቅም ደንበኛው የክሬዲት ክፍያ አገልግሎት ለመጠቀም ጥያቄ ካቀረበበት ቀን በፊት ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ እና በቴሌኮም አጠቃቀም ይወሰናል። ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች እና የገንዘብ ልውውጥ የደንበኛ የብደር አቅምን ለማስላት ይውላሉ።

o ለእርስዎ ወይም ለስጦታ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል መግዛት (በራስ አገዝ ወይመ ከወኪሎች)

o ዕቃ ወይም አገልግሎት በመግዛት ግብይት መፈጸም

o ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ ቢል ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)

o ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)

o ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል

o የጅምላ ክፍያ (ደሞዝ፣ ሴፍቲኔት…)

o የትኬት ክፍያ

o ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ

o የቁጠባ አገልግሎት

o ገንዘብ መላክ

o የቴሌኮም ፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት) ወ.ዘ.ተ.

5. የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት መጠን እና ክፍያ
• በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።

• ሌላ የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ለማግኘት መጀመሪያ ቀድመው የወሰዱትን የዲቫይስ ፋይናንሲንግ ክሬዲት መክፈል ይጠበቅብዎታል፡

• ያለብዎትን ክሬዲት በከፊል ወይም በሙሉ መክፈል ይችላሉ።

• ያለብዎን ብድር በቀነ ገደቡ ውስጥ የማይከፍሉ ከሆነ ተጨማሪ የቅጣት ክፍያ 0.5% በየዕለቱ የሚሰላ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ ይህም 3% የሚቆም ይሆናል፡፡

• ጊዜው ካለፈ በኋላ ተበዳሪው በሰዓቱ ካልከፈለ አበዳሪው የቀረውን የብድር መጠን ከቴሌብር ሂሳቡ ወዲያው ተቀናሽ የሚደረግ ሲሆን እንዲሁም ከኮሚሽን አካውንት ይወሰዳል፡፡

• የክፍያ መመለሻ ጊዜ 6 ወር፣ እና 12 ወር ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ክፍያዎን በየወሩ መክፈል ይጠበቅቦታሎ።

• የ6 ወር ክሬዲት የማስተላለፊያ ክፍያዎች 20%፣ እና የ12ወር ክሬዲት የማስተላለፊያ ክፍያዎች 25% ሆኖ ተቀምጧል፡፡

6.የአስተዳደር ህግ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕጎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች፣ እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም አግባብነት ያላቸው አሠራሮች እነዚህን ውሎችና ሁኔታዎች ይቆጣጠራሉ።

7.መጠይቆች (መረጃ)
ከቴሌብር የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎት ሂደት፣ ውሎች እና ሁኔታዎች ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በቴሌብር የደንበኞች ግንኙነት ማእከል (127 በመደወል) ተጨማሪ መረማግኘት ይችላሉ።

8. የውል መቋረጥ
ማንኛውንም የዲቫይስ ፋይናንሲንግ አገልግሎትን ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ ወይም ያለ ማስታወቂያ በእርስዎ አላግባብ መጠቀም ወይም ማጭበርበር ምክንያት ይህን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማገድ ወይም ለማቋረጥ መብት ይኖረናል። የዚህ ውል መቋረጥ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች መብቶችን እና ግዴታዎችን ሊነካ አይችልም።

9.ቅሬታዎች
ቅሬታዎች በአካል፣ በጽሁፍ፣ በፖስታ፣ በፋክስ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊቀርቡ ይችላሉ። ኢትዮ ቴሌኮም ቅሬታዎትን በተገቢው ጊዜ ለመፍታት ሁሉንም እርምጃዎች ይወስዳል። በመልሱ ካልተደሰቱ ጉዳዩን ወደ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅደም ተከተል ማድረስ ይችላሉ።

10.የክርክር መፍትሄ
ከዚህ ውል ጋር በተያያዘ የሚነሳ ማንኛውም አለመግባባት ከላይ በአንቀጽ 9 መሠረት ያልተፈታ አለመግባባት ሥልጣን ላለው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፍርድ ቤት መቅረብ ይችላል።

11.በአደራ የተቀመጠ ንብርት
ዕዳ ካለብዎት በእጅዎት ላይ ባሉ ንብረቶችዎ፣ ጥሬ ገንዘብ፣ እቃዎች፣ ዋስትናዎች፣ ውድ ጌጦች፣ ቼኮች ወዘተ ላይ አጠቃላይ ዋስትና ይኖረናል። ሌላ ተንቀሳቃሽ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመልቀቂያ መብት በሚሰጥበት ሁኔታ ውስጥ ዕዳ ካለብዎ የተያዘው ንብረት በሙሉ ለዕዳው መያዣ ተደርጎ ይቆጠራል።

12. ዕዳ ክፈያ
የወሰዱትን የዲቫይስ ፋይናንሲንግ ክሬዲት መጠን እንዲከፍሉ ካሳዎቅን በኋላ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ውስጥ መመለስ ካልቻሉ ባንክ ውስጥ ካሉዎት ሌሎች የባንክ ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ፣ እቃዎች፣ ዋስትናዎች፣ ውድ ጌጦች፣ ቼኮች ላይ ያለበዎትን ክሬዲት መጠን ያህል ለመውሰድ ባንኩ ይገደዳል፡፡

13.ማስተባበያ
የቴሌብር ሚስጥር ቁጥር (ፒን) በሚስጥር መቀመጥ አለበት፡፡ ከዕርስዎ ሌላ ለማንም ተደራሽ መሆን የለበትም። ከሚስጥር ቁጥር አጠቃቀም፣የሚስጥር ቁጥርን በየጊዜው አለመቀየር፣ ያልተፈቀደ የቴሌብር አካውንት መጠቀም፣ የሞባይል ስልክ ወይም ሲም ካርድ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ኪሳራ ወይም ስርቆት የእርስዎ ሃላፊነት ብቻ ይሆናል።

For English click here