DStv Bundling Service
ከብሮድባንድ ኢንተርኔት FBB(FTTH)ና ሞባይል ዳታ(OTT) ጥቅል (Bundling) ጋር
አስተማማኝ ትሥሥር፤ እንከን የለሽ መዝናኛ!

ለላቀ የዲጂታል አኗኗር፤ የብሮድባንድ ኢንተርኔት(FBB)ና ሞባይል ዳታን (OTT) በመጠቀም፤ የዲኤስቲቪ ኢትዮጵያ ቻናሎችን በጥቅል (package) አማራጮች እየተመለከቱ ይዝናኑ!

ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች፣ ፊልሞች፣ ተከታታይ የአቦል ድራማዎች፣ የቀጥታ ሥርጭቶችንና ሌሎችም፤ ከፍተኛ ፍጥነት ባለው የኢንተርኔት አገልግሎት በቅናሽ ያግኙ!

የእኛን DSTV Bundle አገልግሎት ለምን ይመርጡታል?

  • ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ መዝናኛዎች፦ የሚወዷቸው ታላላቅ የስፖርት ውድድሮችን፣ ፊልሞች፣ ተከታታይ ድራማዎች፣ ዘጋቢ ፊልሞችና ቀጥታ የቲቪ ሥርጭቶችን በማንኛውም ጊዜ መመልከት ማስቻሉ፤
  • እንከን የለሽ ግንኙነት፡- ፈጣንና አስተማማኝ በሆኑ የFTTH ኢንተርኔትና የሞባይል ዳታ ጥቅሎች ጋር መቅረቡ፤
  • የመረጡት የደንበኝነት ምዝገባ ዕቅዶች፡- ከፍላጎትዎ ጋር የሚጣጣሙ ተመጣጣኝ ጥቅሎች መኖራቸው፤
  • በቀላሉ ማስጠቀሙ፡– በስማርት ፎን፣ ታብሌትና ስማርት ቲቪ ለሆኑ፤ እንዲሁም ስማርት ላልሆኑ ቲቪዎች ደግሞ Set-Top Box (STB) በመጠቀም መመልከት ማስቻሉ ተመራጭ ያደርገዋል።

የዋይ ፋይ(FTTH/FBB) ጥቅሎች፦

  • ከፍተኛ ፍጥነት ካለው (ከ5 እስከ 75 ሜጋቢትስ) ኢንተርኔት ጋር ተጣምረው የቀረቡ የዲኤስቲቪ ጥቅሎች፡ ፕሪሚየም፣ ሜዳ ፕላስ፣ ሜዳ፣ ቤተሰብና የጎጆ ፓኬጆች አማራጮች፤

እንዴት መመዝገብ ይቻላል?

ለዋይ ፋይ (FTTH/FBB) ደንበኞች፡-

  1. አዲስ ለመመዝገብ ወይም ጥቅልዎን ለማሻሻል በአቅራቢያዎ የሚገኙ የኢትዮ ቴሌኮም ሱቆችን ይጎብኙ፤
  2. የሚፈልጉትን (FTTH/FBB) + DSTV ጥቅል ይምረጡ፤
  3. ዋይፋይዎን በቲቪዎ ላይ ይጫኑ፤ ቲቪዎ ስማርት ካልሆን STB ይግዙ።
  4. የመረጡትን የዲኤስቲቪ ጥቅል አስጀምረው በቀጥታ መከታለል ይጀምሩ።


(FTTH/FBB) + DSTV ወርኃዊ ጥቅልና ዋጋ በብር፦

የኢንተርኔት ፍጥነት ጎጆ ቤቴሰብ ሜዳ ሜዳ ፕላስ ፕሪሚየም
5 ሜጋቢትስ9291,1891,5802,5805,365
7 ሜጋቢትስ1,0991,3591,7502,7505,535
9 ሜጋቢትስ1,3341,5941,9852,9855,770
12 ሜጋቢትስ1,5591,8192,2103,2105,995
25 ሜጋቢትስ2,6992,9593,3504,3507,135
75 ሜጋቢትስ6,0596,3196,7107,71010,495


የዲቫይስ ጥቅል ዋጋ፦

የመሣሪያ ስም የአንድ ጊዜ ክፍያ ቅድመ ክፍያ ወርኃዊ ክፍያ (12 ወራት)
ZTE UHD TV Stick6,300 ብር1,322 ብር450 ብር
ZXHN F660 v9.2 GPON4,720 ብር993 ብር337 ብር

ማስታወሻ፦

  • የስማርት ቲቪ ተጠቃሚ ደንበኞች፤ በቅድሚያ የDSTV Stream መተግበሪያን በቲቪያቸው ላይ መጫን፤ ስማርት ካልሆነ ቲቪ ደግሞ STB (Set-Top Box) መጠቀም አላባቸው።
  • ሁሉም የዋጋ ዝርዝሮች 15% ታክስን ያካተቱ ናቸው።

የሞባይል ዳታ /OTT/ጥቅሎች፦

  • ከ5 ጂቢ ጀምሮ እስከ 100 ጂቢ ድረስ ባሉት የጥቅል አማራጮች ዲኤስቲቪ ስትሪምን በስማርት ስልክዎ ይመለከቱ።

እንዴት መመዝገብ ይቻላል?

ለሞባይል ኢንተርኔት /OTT/ ደንበኞች፡-

  1. *999# ይደውሉ ወይም የቴሌብር መተግበሪያን ይጠቀሙ።
  2. የሚፈልጉትን OTT + DSTV ጥቅል ይምረጡ (ለምሳሌ፡ ፕሪሚየም + 100 ጊባ....)።
  3. ክፍያዎን በአየር ሰዓት ወይም ቴሌብር በኩል መክፈልዎን ያረጋግጡ።
  4. የማረጋገጫ አጭር የጽሑፍ መልእክት፣ ከዲኤስቲቪ ስትሪም መመዝገቢያ ሊንክ ጋር እንደ ደረስዎ በቀጥታ መመልከት ይጀምራሉ።


የሞባይል OTT + DSTV ጥቅልና ዋጋ

ጥቅል የዳታ ቅል ዋጋ
ፕሪሚየም100 ጂቢ5,645
ሜዳ ፕላስ20 ጂቢ2,420
ሜዳ10 ጂቢ1,240
ቤቴሰብ5 ጂቢ729
ጎጆ5 ጂቢ469

ማስታወሻ፦

  • ደንበኞች አገልግሎቱን ለማግኘት የDSTV Stream መተግበሪያን በስማርት ስልኮቻቸው ላይ መጫን አለባቸው።
  • ሁሉም የዋጋ ዝርዝሮች 15% ታክስን ያካተቱ ናቸው።

  1. ብቁነት፡
    • ለአዲስና ነባር ደንበኞች፤ በአቅራቢያዎ ወደሚገኙ የኢትዮ ቴሌኮም ሱቆች በአካል በመቅረብ መመዝገብና ነባሩን ማሻሻል አለባቸው።
  2. የደንበኝነት ምዝገባ ሒደት፡
    • ለነባር ደንበኞች፡-
      • የነበረው የኢንተርኔት ፍጥነት ከዲኤስቲቪ ጥቅል ፍጥነት ጋር የማይዛመድ ከሆነ የደንበኝነት ምዝገባቸውን ማሻሻል አለባቸው።
      • ቲቪዎ ስማርት ካልሆነ፣ ስማርት ማድረጊያ Set-Top Box መግዛት አለባቸው።
      • እንደ ተመዘገቡ ወዲያውኑ ከቲቪዎ ጋር የሚያገናኝ ሊንክ በአጭር የጽሑፍ መልእክት ይደርስዎታል።
      • በቀጥታ የዲኤስቲቪ ስትሪም መመዝገቢያ ድረ ገጽ እንዲያመሩ በአጭር የጽሑፍ መልእክት የተላከልዎትን ሊንክ ይክፈቱ።
      • በመመዝገቢያ ገጹ ላይ የሚከተሉትን ዝርዝሮች ያስገቡ፦
        • የሞባይል ስልክ ቁጥር፣
        • ትክክለኛ የኢሜይል አድራሻ፣
        • የይለፍ ቃል ይፍጠሩ (ቢያንስ 6 መለያዎችን)
      • የDSTV Stream መተግበሪያን በእርስዎ Smart TV stick/ STB (Set-Top Box) ወይም በስማርት ቲቪ ላይ መጫን አለባቸው።
    • ለአዲስ ደንበኞች፡-
      • ደንበኞች፤ ለዋይፋይ አገልግሎት ምዝገባ በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማእከላት በአካል ቀርበው መጠየቅ አለባቸው።
      • የኢትዮ ቴሌኮም ባለሞያ ለማረጋገጥ በአካባቢዎ የቴክኒክ ዳሰሳ ያደርጋል።
      • ተቀባይነት ካገኘ፤ ደንበኞች በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመመዝገብ አስፈላጊውን ክፍያ መፈጸም አለባቸው።
      • ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ የኢትዮ ቴሌኮም ባለሞያዎች የዋይ ፋይ አገልግሎትን በቤትዎ ውስጥ ያስጀምራሉ።
      • ደንበኞች ቲቪያቸው ስማርት ካልሆነ፣ ስማርት ቲቪ (ስቲክ/Set-Top Box) መግዛት አለባቸው።
      • እንደ ተመዘገቡ ወዲያውኑ ከቲቪዎ ጋር የሚያገናኝ ሊንክ በአጭር የጽሑፍ መልእክት ይደርስዎታል።
      • በቀጥታ የዲኤስቲቪ ስትሪም መመዝገቢያ ዌብሳይት እንዲያመሩ በአጭር የጽሑፍ መልእክት የተላከልዎትን ሊንክ ይክፈቱ።
      • በመዝገቢያ ገጹ ላይ የሚከተሉትን ዝርዝሮች ያስገቡ፦
        • የሞባይል ስልክ ቁጥር፣
        • ትክክለኛ የኢሜይል አድራሻ፣/li>
        • የይለፍ ቃል ይፍጠሩ (ቢያንስ 6 መለያዎችን)
      • የDSTV Stream መተግበሪያን በእርስዎ Smart TV stick/ STB (Set-Top Box) ወይም በስማርት ቲቪ መጫን አለባቸው።
      • በDStv Stream መተግበሪያ ወይም ድረ-ገጽ በመግባት አገልግሎቱን ያስጀምሩ።
  3. የክፍያ ሁኔታ፡
    • ለ FBB + DSTV Bundling Pack የሚከፈለው በድኅረ ክፍያ ሲሆን፤ ክፍያውም ለድኅረ ክፍያ ደንበኞች በተመቻቹ የክፍያ ቻናሎች በኩል ይከናወናሉ።
  4. የደንበኝነት ምዝገባ ማሳወቂያዎች፡
      ደንበኞች በሚከተሉት ሁኔታዎች ልክ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል፦
    • የዋይፋይ አገልግሎት ምዝገባ ጥያቄ ማረጋገጫ (የዳሰሳ ጥናት ቅደም ተከተል ዝርዝሮችን ጨምሮ)፣
    • የዳሰሳ ጥናት ውጤቶች (ምዝገባው ከጸደቀ፤ ደንበኞች አስፈላጊውን መሣሪያ እንዲገዙ ይታዘዛሉ)፣
    • ወርኃዊ የሒሳብ ክፍያዎች፣
    • ያልተከፈሉ የክፍያ መጠየቂያዎችና
    • የአገልግሎት እገዳ ወይም እንደገና የተመለሱ አገልግሎቶች።

ለOTT ተመዝጋቢዎች፦

  1. የዳታ አጠቃቀም፡
    • ከDSTV OTT Bundling ጋር የቀረበው የኢንተርኔት ጥቅል ለዲኤስቲቪ ሞባይል ስትሪም ብቻ የተገደበ ሲሆን፤ ለሌሎች ድረ-ገጾች ማለትም ዩቲዩብ፣ ፌስቡክ፣ ጎግል፣ ወዘተ. መጠቀም አይቻልም።
  2. ብቁነት፡
    • ሁሉም የቅድመ ክፍያ፣ የድኅረ ክፍያና ሃይብሪድ ሞባይል ተጠቃሚ ደንበኞች (የመኖሪያና ድርጅትን ጨምሮ) መመዝገብ ይችላሉ።
  3. የመሣሪያ መስፈርቶች፡
    • የስትሪሚንግ ተሞክሮው የማይቆራረጥ መሆኑን ለማረጋገጥ፤ ደንበኞች በኤልቲኢ የሚደግፉ የ4ጂ ሲም ካርዶችን መጠቀም አለባቸው።
  4. የደንበኝነት ምዝገባ ሂደት፡
    • ደንበኞች ከመመዝገባቸው በፊት በቂ ቀሪ ሒሳብ ሊኖራቸው ይገባል።
    • ለመመዝገብ ወደ *999# ወይም የቴሌብር መተግበሪያን ይጠቀሙ።
    • የሚፈልጉትን ጥቅል ከመረጡ በኋላ ክፍያውን ያጠናቅቁ።
    • የደንበኝነት ምዝገባ ክፍያ ካጠናቀቁ በኋላ ወዲያውኑ ከስልክዎ ጋር የሚያገናኝ ሊንክ በአጭር የጽሑፍ መልእክት ይደርስዎታል።
    • ደንበኞች በመረጡት የOTT + DSTV ጥቅል መሠረት የኢንተርኔት ዳታ ጥቅል ያገኛሉ። ሆኖም፤ ጥቅሎች ለ30 ቀናት ብቻ የሚያገለግሉ ናቸው።
    • በቀጥታ የዲኤስቲቪ ስትሪም መመዝገቢያ ዌብሳይት እንዲያመሩ በአጭር የጽሑፍ መልእክት የተላከልዎትን ሊንክ ይክፈቱ።
    • በመመዝገቢያ ገጹ ላይ የሚከተሉትን ዝርዝሮች ያስገቡ፦
      • የሞባይል ስልክ ቁጥር፣
      • ትክክለኛ የኢሜይል አድራሻ፣
      • የይለፍ ቃል ይፍጠሩ (ቢያንስ 6 መለያዎችን)
    • በDStv Stream መተግበሪያ ወይም ድረ-ገጽ በመግባት አገልግሎቱን ያስጀምሩ።
  5. የአከፋፈል ሁኔታ፡
    • ከደንበኛው ቀሪ የአየር ሰዓት ሒሳብ ወይም ከቴሌብር ሒሳብ ይቀነሳል።
    • የድኅረ ክፍያ ደንበኞች በዚህ መሠረት እንዲከፍሉ ይደረጋሉ፣ የሃይብሪድ ክፍያዎች ደግሞ በነባሩ የመክፈያ ሁኔታቸው መሠረት እንዲከፍሉ ይደረጋሉ።