ጥቅል ያጋሩ አገልግሎት

በጥቅል ያጋሩ አገልግሎታችን ካልዎት ላይ ሙሉውን ወይም በከፊል ለወዳጅ ዘመድ ጓደኛ ያካፍሉ።

  • በማንኛውም ቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እንዲሁም ሀይብሪድ ሞባይል ቁጥራቸውን በመጠቀም ጥቅል የገዙ ደንበኞች በሙሉ አገልግሎቱን ለመጠቀም ብቁ ናቸው፡፡
  • የግለሰብ ቅድመ/ድህረ ክፍያ ወይም ሀይብሪድ ሞባይል ደንበኞች ካላቸው የጥቅል ቀሪ ሀብት ላይ ለግለሰብ ወይም የድርጅት ቅድመ/ድህረ ክፍያ ወይም ሀይብሪድ ሞባይል ተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡
  • ደንበኞች የጥቅል ሀብታቸውን ወደ ሌሎች ሲያስተላልፉ የአገልግሎት ክፍያ 12 ሣንቲም ለአንድ ጊዜ መላኪያ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
  • የድርጅት ደንበኞች ሲላክላቸው መቀበል የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን ወደ ሌሎች ያላቸውን ቀሪ ጥቅል ማጋራት አይችሉም፡፡
  • የኢትዮ ቴሌኮም ሠራተኛ የሆነ ደንበኛ ድርጅቱ ከሰጠው ጥቅማ ጥቅም ላይ ለሌሎች ደንበኞች ማጋራት የማይችል ሲሆን ነገር ግን ከሌሎች መቀበል ይችላል፡፡
  • ደንበኞች የገዙት የሞባይል ጥቅል ከ24 ሰዓት በላይ የአገልግሎት ጊዜ ካለው ለሌሎች ለማጋራት ይችላሉ፡፡
  • የሚተላለፈው የጥቅል ሀብት የአገልግሎት ጊዜ የዋናው/ተላላፊው ጥቅል የአገልግሎት ጊዜ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

ምሳሌ፡ አንድ ደንበኛ የአገልግሎት ጊዜው በሚያዚያ 1 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያበቃ ጥቅል ኖሮት ከሌሎች ቢያጋራ ተቀባዩም ደንበኛ በተመሳሳይ ሚያዚያ 1 ቀን 2014 ዓ.ም የአገልግሎት ጊዜ ማብቂያ ይኖረዋል ማለት ነው፡፡

  • ደንበኞች ከሌሎች የተቀበሉትን ጥቅል መልሰው ለሌላ ደንበኛ ማጋራት ይችላሉ፡፡
  • አገልግሎቱን በኢትዮ ገበታ (*999#) እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል ሞባይል መተግበሪያ ያገኙታል፡፡
  • ያልተገደበ የሞባይል ጥቅል አገልግሎት ተጠቃሚዎች ለሌሎች ጥቅላቸውን ማጋራት አይችሉም፡፡
  • የመደበኛ ስልክ ተጠቃሚዎች ማንኛውንም አይነት ጥቅል መቀበል አይችልም፡፡
  • ወደሌሎች ያጋሩትን ጥቅል መመለስ አይችሉም፡፡ ጥቅል ከማጋራትዎ በፊት ማረጋገጫ ሲመጣልዎት ተመልክተው መላክ ይኖርብዎታል፡፡
  • ጥቅል የማጋራት አገልግሎት ለመጠቀም የላኪው እና የተቀባዩ የሞባይል ቁጥር የሚሰራ በአገልግሎት ጊዜው ያላለፈ መሆን አለበት፡፡
  • የሚያጋራው ደንበኛ ጥቅል የሚልክበት በሞባይል ቁጥሩ ዝቅተኛም ቢሆን ሂሳብ ሊኖረው ይገባል፡፡
  • ደንበኞች ያላቸውን የጥቅል መጠን ሙሉ በሙሉ ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡
  • የተቀባዩ ሞባይል ቁጥር በአገልግሎት ጊዜ ማለፍ ምክንያት ከተዘጋ፣ ከታገደ እንዲሁም የተቋረጠ ከሆነ ለላኪው መቀበል እንደማይችል ማሳወቂያ ይደርሰዋል፡፡
  • ደንበኞች በቀን እስከተፈቀደው ገደብ ድረስ ለአንድ ተቀባይ በተደጋጋሚ ጥቅል ማጋራት ይችላሉ፡፡
  • የማስታወቂያ እና የማበረታቻ ጥቅል ስጦታዎች ለሌሎች ማጋራት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን ከማሽን ወደ ማሽን ጥቅል እና ለመጀመሪያ ጊዜ ሞባይል ቁጥር ሲያወጡ የሚያገኙት የማበረታቻ ስጦታ ወደ ሌሎች ለማስተላለፍ አይችሉም፡፡
  • ጥቅሉ በተሳካ ሁኔታ መጋራቱን የሚገልፅ መልዕክት ለተቀባዩም ለላኪውም የሚደርሳቸው ይሆናል፡፡ መልዕክቱ የጥቅሉ መጠን፣ አሁን ያለው ቀሪ መጠን፣ የአገልግሎት ጊዜ ማብቂያ እንዲሁም የላኪው ስልክ ቁጥር የያዘ ይሆናል፡፡

ጥቅል

በቀን ውስጥ ሊያካፍሉ የሚችሉት ትንሹ ጥቅል

በቀን ውስጥ ሊያካፍሉ የሚችሉት ትልቁ ጥቅል

ድምጽ

3 ደቂቃ

100 ደቂቃ

ዳታ

30 ሜባ

1 ጂቢ

አጭር የጽሁፍ መልእክት

5 አጭር የጽሁፍ መልእክት

500 አጭር የጽሁፍ መልእክት

ጥቅል ይቀይሩ አገልግሎት

ጥቅል ይቀይሩ አገልግሎት ያሎትን ጥቅል እንደምርጫዎ ወደ ድምጽ፣ዳታ እና አጭር የጺሁፍ መልእክት እየቀያየሩ እንዲጥቀሙ ይረዳዎታል።

  • የቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እንዲሁም ሀይብሪድ ተጠቃሚ ደንበኞች አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • አገልግሎቱን ለመጠቀም የሞባይል ቁጥሩ በአገልግሎት ጊዜ ማለፍ ምክንያት የተዘጋ፣ የታገደ እንዲሁም የተቋረጠ መሆን የለበትም፡፡
  • ሁሉም ያልተገደቡ ጥቅሎች ፣ ከማሽን ወደ ማሽን አገልግሎት የቀረቡ ጥቅሎች፣ ዳታ ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ የሞባይል ቁጥሮች እንዲሁም ለድርጅት ደንበኞች የቀረቡ ጥቅማ ጥቅሞች (የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞችን ጨምሮ) ጥቅል የመቀየር አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን አይችሉም፡፡
  • ሣምንታዊ እና ወርሃዊ ጥቅል አገልግሎቶች ብቻ ለጥቅል ይቀይሩ አገልግሎት ብቁ ናቸው፡፡
  • የተለያየ ጥቅል ካለዎት አነስተኛ የአገልግሎት ጊዜ ያለው ጥቅል ለመቀየር ቅድሚያ ይሰጠዋል፡፡
  • በቀን ውስጥ መቀየር የሚችሉት ዝቅተኛው የጥቅል መጠን
  • ዝቅተኛው የድምፅ መጠን = 5 ደቂቃ
  • ዝቅተኛው የዳታ መጠን = 20 ሜ.ባ
  • ዝቅተኛው አጭር የፅሁፍ መልዕክት መጠን = 20 መልዕክት
  • ደንበኞች የቀየሩትን ጥቅል ለሌሎች ማጋራት አይችሉም፡፡
  • በስጦታ የተቀበሉትን ጥቅል ወደ ሌላ አይነት ጥቅል ከቀየሩ በኋላ መመለስ አይችሉም፡፡
  • የተቀየረው ጥቅል የአገልግሎት ጊዜ ከዋናው ጥቅል የአገልግሎት ዘመን ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
  • አንድን ጥቅል ከአንድ ጊዜ በላይ መቀየር ወይም ወደ መጀመሪያው መመለስ የማይቻል ነው፡፡ ለምሳሌ የድምፅ ጥቅልን ወደ ዳታ መቀየር ይችላሉ፡፡ ቀጥሎ የቀየሩትን ዳታ ወደ አጭር የፅሁፍ መልዕክት መቀየር አይችሉም፡፡
  • ደንበኞች ከሌሎች የተበረከተላቸውን ሳምንታዊ እና ወርሃዊ ጥቅል እንደፍላጎታቸው ወደ ሌላ አይነት ጥቅል መቀየር ይችላሉ፡፡
  • የጥቅል መቀየር አገልግሎት ያልተገደበ ጥቅል ለሚጠቀሙ ደንበኞች አያገለግልም፡፡
  • አገልግሎቱ በኢትዮ ገበታ፣ በማይ ኢትዮቴል መተግበሪያ፣ በኢ-ኬር እንዲሁም በአካል ቀርበው ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • ደንበኞች ያላቸውን ቀሪ የጥቅል መጠን መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • የተቀየረው ጥቅል የመጨረሻ ዋጋ በሂሳብ ህግ መሰረት ወደላይ ሊያድግ ወይም ወደታች ሊደረግ ይችላል፡፡ (ከ0.5 በላይ ከሆነ ወደ ላይ እንዲሁም ከ0.5 በታች ከሆነ ሊቀንስ ይችላል፡፡)