በአጋርነት የሚሰጥ የክላውድ ሶሉሽን Click Here for more ሶፍትዌር እንደ አገልግሎት- ኢአርፒ (SaaS-ERP) አሰራር ፣ የስራ ሂደት አና አስተዳደርን የሚያዘምን የተቀናጀ የኮምፒውተር መተግበሪያዎች ስብስብ ሲሆን ፤ አገልግሎቶች ወጪ ቆጣቢ ፣ ቀልጣፋ እና ምርታማ እንዲሆኑ ያግዛል። Click here for more ሶፍትዌር እንደ አገልግሎት– የፋይል አስተዳደር ስርዓት (SaaS-FMS) የዲጅታል ፋይሎችን ለማከማቸት እና ለማሰተዳደር የሚያግዝ የሶፍትዌር ስርዓት ነው። ይህ ሰርዓት በአሁናዊ እና በትብብር መንገድ ፋይሎች ላይ የአርትዖት ፣ የማከማቸት እና የማጋራት ስራዎችን ለመከወን ያስችላል። Click here for more ሶፍትዌር እንደ አገልግሎት- ኢሜል (SaaS-Email) ፈጣን ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ የሆነ በድርጅት ውስጥ እንዲሁም ከደንበኞች ጋር የሚደረጉ ስራ እና ገበያ ነክ መልዕክቶችን ለመቀያየር የሚያስችል የኤሌክትሮኒክስ መድረክ ነው። የራስ የሆነ የኢሜል ጎራ/መነሻ ስም (ኢሜል ዶሜን ኔም) በመጠቀም ድርጅቶች ሙያዊ ገፅታ እንዲላበሱ እና በደንበኞቻቸው ዘንድ ተአማኒነታቸው እንዲጨምር ከማድረግም ባሻገር ድርጅታዊ ምስላቸውም በዘለቄታዊነት እንዲጨምር ያግዛል። Click here for more ሶፍትዌር እንደ አገልግሎት – የኤሌክትሮኒክስ የግብይት መድረክ (SaaS-Ecommerce) የኤሌክትሮኒክስ የግብይት መድረክ በይነ መረብን መሠረት ያደረገ የገበያ፣ የሽያጭ፣ የመረጃ ልውውጥ እና የደንበኞች አገልግሎቶን ለመስጠት የሚያስችል የኤሌክትሮኒክስ መላ ነው። ይህ የግብይት መድረክ ወጪ ቆጣቢ በሆነ እና ተአማኒነትን ባተረፈ መንገድ ድርጅቶች ደንበኞቻቸውን በቀላሉ ለ 24/7 እንዲያገለግሉ ያስችላቸዋል። Click here for more ክላውድ ሰርቨር - ሲፒዩ ተኮር ሲፒዩ ተኮር የሆኑ ሶፍትዌሮችን ወደ ስራ ለማስገባት ደንበኞች በሚፈልጉት መጠን ማዘዝ የሚችሉት ከፍተኛ የማሰላሰል አቅም ያለው ሰርቨር ነው፡፡ ደንበኞች የሰርቨሩን የማሰላሰል እና የማከማቸትን መጠን በፈለጉ ጊዜ መጨመር ይችላሉ። ይህ ሰርቨር የሚቀርበው ኢትዮ ቴሌኮም የኢንዱስትሪውን የጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ከገነባቸው ዳታ ሴንተሮች ውስጥ በሚገኙ የክላውድ መሰረተ ልማቶች ነው። Click here for more ክላውድ ሰርቨር - ራም ተኮር ራም ተኮር የሆኑ ሶፍትዌሮችን ወደ ስራ ለማስገባት ደንበኞች በሚፈልጉት መጠን ማዘዝ የሚችሉት ከፍተኛ የራም አቅም ያለው ሰርቨር ነው፡፡ ደንበኞች የሰርቨሩን የማሰላሰል እና የማከማቸትን መጠን በፈለጉ ጊዜ መጨመር ይችላሉ። ይህ ሰርቨር የሚቀርበው ኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ማዕከሎች ላይ የኢንዱስትሪውን የጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ከገነባነው የክላውድ መሰረተ ልማታችን ነው። Click here for more ክላውድ ስርቨር – ቤር ሜታል ሶፍትዌሮችን ወደ ስራ ለማስገባት ከፍተኛ የማሰላሰል እና የማከማቸት አቅም ያለው እና ለደንበኛው ብቻ የሚመደብ (ማለትም ሌሎች ደንበኞች የማይጋሩት) ቁሳዊ/ፊዚካል ሰርቨር ነው። ይህ ሰርቨር ተዘጋጅቶ የሚቀርበው የኢንዱስትሪውን የጥራት ደረጃ ከጠበቀ ከኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ማዕከል ነው። Click here for more መጠባበቂያ አገልግሎት ለክላውድ ሰርቨር በየሰዓቱ፣ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ ወይም በየወሩ (ወይም የእነዚህ ማናቸውም ጥምረት) በታቀደ መልኩ ለመጠባበቂያ በክላውድ ሰርቨሮች ላይ ያሉ መረጃዎችን ቅጂ ለማከማቸት የሚያስችል አገልግሎት ነው። ይህን በማድረግ ደንበኞች የወሳኝ መረጃዎቻቸውን ደህንነት በከፍተኛ ደረጃ እንዲጠብቁ ያስችላቸዋል። Click here for more ክላውድ የኤችዲዲ ማከማቻ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል፤ በደንበኛ ፍላጎት የማከማቸት መጠኑ ማደግ የሚችል የኤችዲዲ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ማከማቻ ነው። ማከማቻው የሚቀርበው ኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ማዕከሎች ላይ የኢንዱስትሪውን የጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ከገነባነው የክላውድ መሰረተ ልማታችን ነው። Click here for more ክላውድ የኤስኤስዲ ማከማቻ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ፤ በደንበኛ ፍላጎት የማከማቸት መጠኑ ማደግ የሚችል የኤስኤስዲ ቴክኖሎጂ የሚጠቀም ማከማቻ ነው። ማከማቻው የሚቀርበው ኢትዮ ቴሌኮም ዳታ ማዕከሎች ላይ የኢንዱስትሪውን የጥራት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ከገነባነው የክላውድ መሰረተ ልማታችን ነው። Click here for more ክላውድ ፋየርዋል የክላውድ ሰርቨሮችን ከበይነ መረብ ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ፤ የመከላከል አቅሙ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተመሰከረለት እንዲሁም ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ የፋየርዎል ስርአት ነው። Click here for more ቪፒኤን ለክላውድ የክላውድ ሰርቨሮችን ቢሮዎ ከሚገኝ የኔትዎርክ መሰረተ ልማት ወይም ከሚፈልጉት ሌላ ቦታ ሆነው ምስጢራዊነቱ እንደተጠበቀ ለመጠቀም የሚያስችል አገልግሎት ነው።