ለድርጅት የማስጀመሪያ ጥቅላችን መጠይቅ ከማቅርብዎ በፊት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ደንብና ሁኔታዎች በጥንቃቄ ያንብቡ፡፡
ስለብቁነት
- ይህ አገልግሎት በልዩነት የቀረበው ለድርጅት ደንበኞች ብቻ ስለሆነ
- ከቅናሽ ጋር የቀረበው መደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔታችን በልዩነት የተዘጋጀው ለጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ስራዎች ለተሰማሩ ብቻ ነው፡፡
- እንዲሁም በቅናሽ የቀረቡት ሞባይል ጥቅሎች የቀረቡት ከአዲስ ሲም ካርድ ተጠቃሚዎች ነው፡፡
ለመመዝገብ
- አንድ የድርጅት ደንበኛ ይህንን አገልግሎት መግዛት የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
- የሞባይል ጥቅል አገልግሎት ለመግዛት ካሰቡ ለአንድ ጊዜ ወይም በቋሚነት በየወሩ ብለው መምረጥ ይችላሉ፡፡
ለውጦች ስለሚስተናገዱበት ሁኔታ
- ለማቋረጥ፡ ለኮምቦ አገልግሎት (መደበኛ ብሮድባንድና መደበኛ ስልክ) ካመለከቱ በኋላ ሁለቱም አገልግሎቶች ወይም ከሁለቱ አንዱ እቋረጥልዎ በማንኛውም ጊዜ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ከሁለቱ አንዱን በሚያቋርጡበት ጊዜ ታድያ በምዝገባ ወቅት የቀረበልዎ ቅናሽ እስከፈለጉት ጊዜ ድረስ እንደተጠበቀ ይቆያል፡፡
- ፍጥነትለማሳደግና ዝቅ ለማድረግ
- የሚቻልባቸው ሁኔታዎች:
- ለአነስተኛና ጥቃቅን የብሮድባንድ ፍጥነቶች ውስጥ መርጠው ማሳደግ ወይም ዝቅ ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ነገር ግን በልዩነት ከቀረቡት ፍጥነቶች ውጪ ማለትም የቢዝነስ ቴሌ ፋይበር የፍፍነት አማራጮችን ከፈለጉ መቀየር የሚችሉ ቢሆንም ነገር ግን የተፈቀደልዎ 20% ቅናሽ የሚነሳ ይሆናል፡፡
- የማይቻልባቸው ሁኔታዎች:
- ለመደበኛ የጥቃቅንና አነስተኛ የብሮድባንድ አማራጮች ወይም ከቴሌ ቢዝነስ ፋይበር አገልግሎት ወደ እዚህ አገልግሎት የፍጥነት ለውጥ አድርገው መግባት አይችሉም፡፡
ስለቢል አከፋፈል
- የአከፋፈል ሁኔታ:
- መደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት የቀረበው በድህረ ክፍያ የአከፋፈል ስርዓት ብቻ ነው፡፡
- ከአዲስ ሲም ካርድ የቀረቡት የሞባይል ጥቅሎችን ግን በቅድመ ክፍያ፣ ድህር ክፍያ እና ሀይብሪድ አማራጭ ቀርቧል፡፡
- የመጀመሪያ ወር አከፋፈል፡ለሁሉም የአከፋፈል ዘዴዎች (ቅድመ ክፍያ/ድህረ ክፍያ) አማራጭ ክፍያ ለመጀመሪያ ወር ብቻ ቅድሚያ መከፈል አለበት፡፡
- ስለቀጣይ የአከፋፈል ሁኔታዎች (ለቋሚ ወርኃ ጥቅል ተጠቃሚዎች): ከመጀመሪያው ወር በኋላ ግን የቋሚ ወርኃዊ ጥቅል ተጠቃሚዎች በመደበኛ የአከፋፈል ሁኔታቸው ማለትም በድህረ ክፍያ ወይም ቅድመ ክፍያ የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡
- ተ.እ.ታ:ሁሉም የቀረቡት ዋጋዎች 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እና 2% ኤክሳይስ ግብር ታሳቢ ያደረጉ ናቸው፡፡
ስለ ኮምቦ አገልግሎታችን በተመለከተ
- የአከፋፈል ሁኔታ:ለአዲስ የኮምቦ አገልግሎት ጠያቂዎች በምዝገባ ወቅት የመደበኛ ብሮድባንድ ወይም ስልክ አገልግሎት የምዝገባ ክፍያ ሊካተት ይችላል፡፡
- ስለነፃ የመደበኛ ስልክ አገልግሎት:ለኮምቦ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ለተከታታይ 3 ወራት በዋና ገፅ ላይ የተጠቀሱትን አገልግሎቶች ከተከታታይ 3 ወራት በነፃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ነፃ የመደበኛ ስልክ ጥሪዎችን ለማስቀጠል፡ ከ3 ወራት በኋላ የቀረቡት ነፃ ጥሪዎች ማስቀጠል ቢፈልጉ በየወሩ ተጨማሪ 100 ብር በመክፈል በቋሚነት ማስቀጠል ይችላሉ፡፡
ስለ ሞደም የተራዘመ ክፍያ ሁኔታ፡
- ስለብቁነት፡ አገልግሎት ጠያቂዎች ማለትም አዲስ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ከአዲስ ሲም ካርድ ጋር የሚጠይቁ ደንበኞች የኤዲኤስኤል ሞደም በ12 ወራት የተራዘመ አከፋፈል ሁኔታ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ይህን የተራዘመ የአከፋፈል ሁኔታ ለማግኘት የሚገቡት ውል ይኖራል፡፡
- ቀድሞ አገልግሎት ስለማቋረጥ: በተራዘመ ክፍያ ሞደም ለማግኘት ውል ቢገቡም ማቋረጥ ቢፈልጉ፤ የሞደሙን ዋጋ ቀሪ ክፍያ መፈፀም ይጠበቅብዎታል፡፡
የሞባይል ጥቅል በመግዛትዎ የሚያገኟቸው ጥቅሞች
- ማንኛውም ያልተጠቀሙበት ቀሪ ጥቅል (ደቂቃ፣ መልዕክት ወይም ዳታ) ካለዎት 100% ወደ ቀጣይ ወር ብቻ የሚተላለፍልዎ ይሆናል፡፡
- ከጥቅለ ውጪ ሲጠቀሙ:የቀረቡትን ጥቅሎች ከወር በፊተ ቀድመው ቢጨርሱ የአገልግሎት ቀኑ (Expiry date) እስኪደርስ ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ዝቅተኛ ዋጋዎች የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
- ዳታ:11 ሳንቲም በሜ.ባ
- ድምጽ: 50 ሳንቲም በደቂቃ
- መልዕክት: 12 ሳንቲም በመልክዕት