ለወዳጅ ዘመድዎ፣ ለፍቅር አጋርዎ፣ ለስራ አጋርዎ እንዲሁም ለሚያስቡላቸው የሚሆኑ ስጦታዎችን እስከ ገና በዓል ድረስ በዘመን ገበያ በተመረጡ የመደብር ምርቶች ላይ እስከ 65% በተደረገው ቅናሽ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡
ደንብና ሁኔታዎች
• የገንዘብ ተመላሹ ተግበራዊ የተደረገው በተመረጡ የመደብር ምርቶች ላይ ብቻ ነው፡፡
• ደንበኞች ተመላሽ የሚያገኙት በአንድ ምርት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ደንበኛ ቅናሽ የተደረገበትን ምርት ሁለት ጊዜ እና ከዛ በላይ የሚያዝ ከሆነ ተመላሽ ማግኘት የሚችለው ለአንድ ትዕዛዝ ብቻ ይሆናል፡፡
• ቅናሹን የሚያገኙት በቅድሚያ የምርቱን ሙሉ ዋጋ ከከፈሉ በኋላ ሲሆን ተመላሹ ወዲያውኑ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ የሚላክልዎ ይሆናል፡፡
• ቅናሽ የተደረገባቸው ምርቶች ለቤተሰብ፣ ለፍቅር አጋርዎ፣ ለስራ ባልደራባዎ፣ እንዲሁም ለሚያስቡላቸው በሚል የተከፋፈሉ ናቸው ይህም ደንበኞች በቀላሉ ቅናሽ የተደረገባቸውን ምርቶች እንዲያገኙ ያግዛቸዋል፡፡
• ለነፃ ዴሊቨሪ ብቁ ለመሆን የዘመን ገበያ ትዕዛዝዎ ድምር 3000 ብር እና ከዛ በላይ መሆን አለበት፡፡