የጨረታ ቁጥር 01/2018
ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ቀን ከየካቲት 06 ቀን 2ዐ18 ዓ.ም
ጨረታዉ የሚዘጋበት ቀን ከየካቲት 25 ቀን 2ዐ18 ዓ.ም
ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን ከየካቲት 26 ቀን 2ዐ18 ዓ.ም
በኢትዮቴሌኮም የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ከአገልግሎት የተመለሱ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፤የተለያዩ አይነቶች ያገለገሉ ወንበሮች፤የተለያዩ የእንጨት ምሰሶዎች፤ያገለገሉ መጋረጃዎች፤የብረት በርሚሎች፤ከአገልግሎት የተበላሹ ካዝናዎች፤አሮጌ ጀነሬተር፤የማያገለግሉ ሶላር ፓኔሎች፤ከአገልግሎት የተመለሱ ቆርቆሮዎች፤እና ሌሎች የመሳሰሎት ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ ለብረታብረት ፋብሪካዎች ቅድሚያ በመስጠት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከየካቲት 06 ቀን 2ዐ18 ዓ.ም እስከ የካቲት 25 ቀን 2ዐ18 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ደሴ/ፒያሳ በሚገኘው የኢትዬ ቴሌኮም ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 202 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል እና በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ ተጫራቾች ደሴ/መላኩ አካባቢ በሚገኘው ዋናው ዕቃ ግ/ቤት ቢሮ በመገኘት መጠየቅ ይቻላል ፤ እንዲሁም ንብረቶቹን መመልከት ለሚፈልጉ ደሴ ካራጉቱ በሚገኘው ዕቃ ግምጃ ቤት የታደሰ መታወቂያችሁን እና የጨረታ ሰነዱን የገዛችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ መጎብኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደሴ/ፒያሳ በሚገኘው ዋናው ጽ/ቤት የካቲት 26 ቀን 2ዐ18 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሰ/ምስ/ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም ደሴ
በኢትዮቴሌኮም የሰሜን ምስራቅ ሪጅን ከአገልግሎት የተመለሱ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣የተለያዩ አይነቶች ያገለገሉ ወንበሮች፣የተለያዩ የእንጨት ምሰሶዎች፣ ያገለገሉ መጋረጃዎች፣የብረት በርሚሎች፣ከአገልግሎት የተበላሹ ካዝናዎች፣አሮጌ ጀነሬተር፣የማያገለግሉ ሶላር ፓኔሎች፣ከአገልግሎት የተመለሱ ቆርቆሮዎች፣እና ሌሎች የመሳሰሎት ዕቃዎች ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ የወጣ ግልጽ ጨረታ
Share This Post:
Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on reddit
Share on pinterest
Share on tumblr
Share on whatsapp