የኢትዮቴል ኢኖቬሽን ፕሮግራም

የሃገራችን ጀማሪ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ ቢዝነሶችና ባለሙያዎች የሚበረታቱበት!

 • የኢትዮቴል ኢኖቬሽን ፕሮግራም ዓላማ
 • የሀገር በቀል ችግር-ፈቺ ተግባራትን ለማበረታታት፣
 • ክህሎት ያላቸውን ወጣቶች ለመሳብ፣ ለማነሳሳትና አዳዲስ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ለማገዝ፣
 • ለህብረተሰቡ ጠቃሚ የሆኑ የፈጠራ ሀሳቦችን እንዲያጎለብቱና አዳዲስ ምርትና አገልግሎቶችን ወደ ገበያ እንዲያመጡ ለመደገፍ
 • ለእያንዳንዱ ጀማሪ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለሙያ፣ ለቴክኖሎጂ አጋሮች እና ለዘርፉ ተዋንያን የትብብር ከባቢያዊ ሁኔታን በመፍጠር ጥረታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ዲጂታል ኢትዮጵያን ዕውን የማድረግ ጉዞውን ማጠናከር ነው፡፡

ምዕራፍ አንድ

 • የመጀመሪያው ምዕራፍ ከየካቲት 03 እስከ ሚያዚያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ይተገበራል፡፡
 • በጀማሪ የክላውድና የሞባይል ፋይናንስ ቢዝነሶች ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡
 • 100 የውድድሩ አሸናፊዎች ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶችና እጥረቶችን የሚፈቱበትና ንግዳቸውን በስኬት የሚያስቀጥሉበት እንዲሁም ለተግባር የቀረቡ ጅምር የፋይናንስና ክላውድ ቢዝነስ ሀሳቦች በፍጥነት ወደ ስራ የሚገቡበት (accelerator) ፕሮግራም ነው፡፡
 • አሸናፊዎች ሙያዊ ምክርን ጨምሮ የባለሙያ፣ የገንዘብ እና ማቴሪያል አቅርቦቶችን የሚያገኙ ሲሆን የኩባንያችን አጋር ከሆነው ከሁዋዌ ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ወደ ቻይና ሀገር ተጉዘው አለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመመልከት ልምድ የሚካፈሉበትንም እድል ያመቻቻል፡፡

የውድድር መስፈርቶች

 • የተቋማችሁን ወይም ቡድናችሁን ማንነት የሚገልጽ መረጃ
 • የምርቶችን/ሶሎሽን ፍኖተካርታ፣ ችግር ፈችነት፣ የሚኖረውን አስተዋጽኦ እና የቢዝነስ ሞዴል የሚገልጽ ማብራሪያ
 • አሁናዊ የገበያ ጥናት መረጃ
 • የሚያስፈልጉ የክላውድ እና የቴሌኮም ሀብቶች ትንበያ
 • የገቢ ሪፖርትና እና እቅዶች 
 • በክላውድ እና ሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ላይ የሚሰሩ ጀማሪ ቢዝነሶች መሆን አለባቸው፡፡
 • የፈጠራ ሀሳቡ/የሞባይል መተግበሪያው ደንበኛን ማዕከል ያደረገ እና የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎቶችን (የድምጽ/የዳታ/የአጭር ጽሑፍ መልዕክት)፣ ቴሌክላውድ እና ቴሌብር ላይ ተጽህኖ መፍጠር የሚችል
 • ነዋሪነታቸው በኢትዮጵያ ውስጥ የሆነ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለሙያዎች፣ ወጣቶች፣ ተማሪዎች እና ጀማሪ የዲጂታል እና የፋይናንስ ቴክኖሎጂ ቢዝነሶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
 • አንድ ተወዳዳሪ መወዳደር የሚችለው በአንድ ፕሮጀክት ብቻ ነው፡፡
 • ተወዳዳሪዎች የተሻ የፈጠራ ሥራ ለማዘጋጀት በሚደረገው ሂደት በጋራ መስራት ይችላሉ፡፡
 • የሚያሸንፈው ፕሮጀክት በዳኞች/በኢትዮቴሌኮም የመገምገሚያ መስፈርት መሰረት ይወሰናል
 • ለዳኝነት አስቸጋሪ ለሚሆኑ የፈጠራ ስራዎች እንደአስፈላጊነቱ ተጨማሪ የመለያ መስፈርት ተግባራዊ ሊደረግ ይችላል፡፡

የማመልከቻ አድራሻ

 • የክላውድ እና የሞባይል ፋይናንስ ጀማሪ ቢዝነስ አመልካቾች ከየካቲት 03 እስከ መጋቢት 03 ቀን 2015 ዓ.ም በኢሜይል አድራሻችን ethiotelinnovation@ethiotelecom.et ላይ ማመልከት ይችላሉ፡፡

 

ምዕራፍ ሁለት

 • ሁለተኛው ምዕራፍ ከመጋቢት 11 እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ይተገበራል፡፡
 • ከፋይናንስና ቴክኖሎጂ ዘርፉ ባለፈ ዲጀታል ይዘቶች፣ አገልግሎቶች፣ ትንታኔዎች እና መተግበሪያዎች ላይ የሚሰሩ 150 ጀማሪ ቢዝነሶች ላይ የሚያተኩር ይሆናል፡፡

ምዕራፍ ሦስት

 • ሶስተኛው ምዕራፍ በነሐሴ ወር ይጀምራል፡፡
 • ተቋማዊ በሆነ አደረጃጀት በፅንሰ-ሀሳብ ደረጃ ያሉ የቢዝነስ ሀሳቦች የሚጎለብቱበትና ስራ ላይ መዋል እንዲችሉ የሚያደርግ የኢትዮ ቴሌኮም የቴክኖሎጂ ማብቂያ ማዕከል (techhub) እንዲሁም ከምዕራፍ አንድ እና ሁለት የተወሰዱ መልካም ተሞክሮዎችን በመጠቀም ወደ ጥናት፣ ምርምር እና ልማት (R&D) ደረጃ በማሳደግ የሚተገበር ይሆናል፡፡