የጅምላ ንግድ

ኢንተርኮኔክት

ኢትዮ ቴሌኮም የኢንተርኮኔክት የድምፅ፣ የአጭር ፅሁፍ መልዕክት እና የትራንዚት አገልግሎት ይሰጣል። በአፍሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ እና በእስያ አህጉራት የድምፅ አገልግሎት የሚሰጡ አጋር ድርጅቶች አሉን። (በዓለም ካርታ ላይ ለመመልከት)።

በአሁኑ ሰዓት ኢትዮ ቴሌኮም በለንደን ቴሌሃውስ እና በጅቡቲ ማረፊያ ጣቢያ ይህን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። በዓለም አቀፍ ደረጃም አብረውን የሚሰሩ ከ 23 በላይ የኢንተርኮኔክት (interconnect) አጋሮች አሉን፡፡ ከዋና ዋና አጋሮቻችን መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

ኢትዮ ቴሌኮም የፋይናንስና የቴክኒክ መስፈርቶችን ከሚያሟሉ አጋሮች ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት አለው። ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ እና ተጨማሪ ትራፊክ ለማግኘት አቅም እና ፍላጎት ካላቸው አጋሮች ጋር የዋጋ ተመንን በተመለከተ ለመወያየትና ለመደራደር ዝግጁ ነን ።

ለበለጠ መረጃ
 • • ወ/ሮ ሄለን ተክሉ/አቶ ጌታቸው ስዩም ያግኙ
 • አድራሻ፡- ቸርችል ሆቴል ፊት ለፊት እዮር ህንጻ 11ኛ ፎቅ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
 • ሞባይል፡+251911247295 / +251911509571

ሮሚንግ

ኢትዮ ቴሌኮም ለድምጽ እና መልእክት፣ ጂ.ፒ.አር.ኤስ እና ከማሽን ወደ ማሽን (M2M) የሮሚንግ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ መደበኛ ታሪፍ እና የተመረጡ የ IOT (Internet of Things) ስምምነቶች አሉን፡፡ በተጨማሪም በ178 አገሮች ከ530 በላይ ከሚሆኑ የቴሌኮም ኦፕሬተሮች ጋር የሮሚንግ አገልግሎት ስምምነት አለን። ከዚህም ውስጥ ከ106 ኦፕሬተሮች ጋር ከ60 በሚበልጡ አገሮች የIOT (Internet of Things) ስምምነት አለን ። ኢትዮ ቴሌኮም የIOT (Internet of Things) ስምምነት ለማድረግ ፍቃደኛ ከሆኑ ተጨማሪ ኦፕሬተሮች ጋር ለመስራት ይጋብዛል።

ከማሽን ወደ ማሽን ሮሚንግ (M2M Roaming)

መሳሪያዎችን እና ማሽኖችን እርስ በርስ ለማግባባት እንዲሁም ባሉበት ቦታ ሁነው ለመቆጣጠር የሚረዱ ሲም ካርዶችን በመጠቀም ከማሽን ወደ ማሽን ሮሚንግ (M2M Roaming) እናቀርባለን፡፡ ፍላጎቱ ያላቸው ደንበኞች አገልግሎቱን፡-  አየር መንገዶች ላይ ካርጎዎችን ለመቆጣጠር፣ የጉዞ መስመሮች እና የጭነት መኪኖች፣ የትራንስፖርት አስተዳደር ስርዓት, ምናባዊ ጆኦግራፊክ ድንበር ለማዘጋጀት፣ ለጉዞ እና ቱሪዝም፣ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃ አቅራቢዎች እና አከፋፋዮች፣ ለአምራቾች፣ ለግብርና፣ ለኃይል እና መገልገያዎች፣ ጤና እና ኢንሹራንስ፣ መዝናኛ ወዘተ…አገልግሎቱን መጠቀም ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ
 • እባክዎ አቶ ጥላሁን ይመርን ያግኙ
 • አድራሻ፡- ቸርችል ሆቴል ፊትለፊት እዮር ህንጻ 1ኛ ፎቅ፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
 • ሞባይል፡:+251911254615

ዓለም አቀፍ ዳታ

ዓለም አቀፍ የመረጃ ሊንክ በኤል 3 ( L3)፣ ኤል 2  (L2) እና አይ. ፒ. ኤል. ሲ (IPLC) አማራጮች እናቀርባለን.

አሁን አብረናቸው እየሰራን ያለነው

ሌሎች ኦፕሬተሮችም ፕሮፖዛል በማቅረብ አብረውን መስራት ይችላሉ

ወርሃዊ እና የአንድ ግዜ የደንበኝት ክፍያ እስከ መዳረሻ ያለውን ለማየት ይህን ይጫኑ::

Cross connection
 • የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ወደሚፈልጉበት መዳረሻ ለመግባት የሚፈልጉ ኦፕሬተሮች የክሮስ ኮኔክሽን ወይም ትራንዚት ትራንስሚሽን ሊንክ (transit transmission link) አገልግሎት እንሰጣለን።

  ኢትዮ ቴሌኮም የሚሰጣቸው፡-

  • መሰረተ ልማትን ብቻ
  • የኢንተርኔት አቅም እና መሰረተ ልማት

   

የመገኛ አድራሻ

ዓለም አቀፍ ከክፍያ ነፃ (TOLL FREE) አገልግሎት

Inbound & ከውስጥ እና ወደ ውጭ ከክፍያ ነጻ አገልግሎት ላይ የተደረገ ማሻሻያ

ወጪ ጥሪ ሲደረግ አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ ወይም በተወሰነ ከክፍያ ነፃ ለደዋዩ የሚደረግ ሲሆን የጥሪው ተቀባዩ ለወጪ ጥሪው ክፍያ ሀላፊነት ይወስዳል፡፡

ከክፍያ ነጻ አለምአቀፍ የወጪ ጥሪ

ከክፍያ ነጻ አለምአቀፍ የወጪ ጥሪ ለደዋዩ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከክፍያ ነፃ የሆነ የስልክ ጥሪ አገልግሎት ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የጥሪ ማዕከላቸውን ከሚያስተናግዱበት አገር አድርገው ለኢትዮጵያውያን ደንበኞቻቸው የጥሪ ማዕከል አገልግሎት እንዲሰጡ ይፈቅዳል። 

ከክፍያ ነጻ አለምአቀፍ የገቢ ጥሪ

ከክፍያ ነጻ አለምአቀፍ የገቢ ጥሪ ለደዋዩ ምንም ዓይነት ክፍያ ሳይጠየቅ የሚደረግ የስልክ ጥሪ አገልግሎት ነው። ድርጅቶች በኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል አገልግሎት እንዲያቋቁሙና ደንበኞቻቸውን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲያገለግሉ ያስችላቸዋል፡፡

ጥቅሞች፡-

 • የአገልግሎቱን ጥራት ለማሻሻል እና ደንበኞችን የማዳረስ አቅም ለማሳደግ፤ እስከ 37% ቅናሽ ከክፍያ ነጻ አገልግሎት ላይ ተደርጓል
 • ከክፍያ ነፃ ቁጥሮች በብዛት ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን ለቢዝነስ እድገት በተለይ ለደንበኞች አገልግሎት እና ቴሌ ማርኬቲንግ ተመራጭ ነው፡፡
 • የደዋዮችን ቢዝነስ የተቀላጠፈ ያደርጋል
 • የደንበኞች አገልግሎት ምላሽን ይጨምራል
 • የብራንድ እውቅናን ማሻሻል፣ ለሁሉም ደንበኞች ተደራሽ የሆነ አስተማማኝ ልዩ ቁጥር መኖር
 • በውድድር ውስጥ ልቆ ለመውጣት

ዋና አጋሮቻችን፡-

 • የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች
 • አየር መንገዶች፣ ሆቴሎች እና ሪዞርቶች
 • የጉዞ እና ቱሪዝም ድርጅቶች
 • ፋይናንስ እና ባንኮች
 • የኮንፈረንስ ጥሪ አገልግሎት ሰጪዎች
 • ማኑፋክቸሪንግ
 • የአበባ አምራቾች
 • መድሀኒት አቅራቢዎች
 • የጥሪ ማዕከላት

ለበለጠ መረጃ

አቶ ታምራት ደፋሩን እባክዎ ያግኙ

የሆልሴል ኢንተርኔት እና ዳታ ስራስኪያጅ
ኢሜይል: Tamrat.Defaru@ethiotelecom.et 
ስልክ ቁጥር: +251(0) – 911510378

አዳም ደመቀ ይግለጡ
የሮሚንግ እና ቫስ ስራስኪያጅ
ኢሜይል: Adam.Demeke@ethiotelecom.et 
ስልክ ቁጥር: +251(0) – 911614858