ስለ መጭበርበር ግንዛቤ

ሆን ተብሎ የሚፈፀም የማታለል ድርጊት ሲሆን አጭበርባሪው ህገ ወጥ ጥቅም እንዲያገኝ ወይም የተጎጂውን መብት ለመንፈግ የሚደረግ ተግባር ነው፡፡

ማህበራዊ ምህንድስና (Social engineering) ፡ በዚህ ዘዴ አጭበርባሪዎች ያልሆኑትን ማንነት በመላበስ (ተቋማትን ወይም ሌሎች ግለሰቦችን በመምሰል) ሚስጥራዊ ወይም የግል መረጃዎች እንዲሰጣቸው የሚያሳምኑበት ዘዴ ነው፡፡ አጭበርባሪዎች በአጭር የፅሁፍ መልዕክት፣ በኢሜይል፣ በማህበራዊ ገፆች መልዕክት በመላክ ወይም የስልክ ጥሪ በማድረግ  የማጭበርበር ተግባርን ይፈፅማሉ፡፡

የአካውንት ዘረፋ፡ አጭበርባሪዎች አገልግሎት ከተጠቀሙ በኋላ ክፍያ አይፈፅሙም፡፡

ይህ የሚከሰተው አጭበርባሪዎች፤

 • የተሰረቁ ሲም ካርዶችን በመጠቀም
 • አጭበርባሪዎች የደንበኞችን አካውንት ከዕውቅናቸው ውጪ ሲጠቀሙ ነው፡፡

ሲም ካርድን በመጠቀም የሚደረግ የመረጃ ምንተፋ: –  የአካውንት ዘረፋ ዓይነት ሲሆን

በፅሁፍ መልዕክት የሚላክን የደንበኞች የአካውንት የይለፍ ቁጥር ደካማ አያያዝ (Weak Password Handling) ምክንያት ነው፡፡

የሞባይል ገንዘብ (ቴሌብር) ማጭበርበር: በቅርብ ጊዜ የታየ የማጭበርበር አይነት ሲሆን የቴሌብር አካውንት ላይ የተቀመጠን ገንዘብ ያለመ ነው፡፡

ይህ ማጭበርበር የሚከሰተው

 • አጭበርባሪዎች የስልክ ጥሪ በማድረግ ወይም የፅሁፍ መልዕክት በመላክ ደንበኞችን በተሳሳተ መረጃ ሲያታልሉ
 • የውሸት መተግበሪያ አዘጋጅተው ደንበኞች እንዲጭኑ ይጋብዛሉ (እንደ ሞባይል ባንኪንግ አይነት መተግበሪያ)፡፡ ነገር ግን ደንበኞች መተግበሪያውን ለመጠቀም ሲሞክሩ ያልጠየቁት አገልግሎት ከፍቃዳቸው ውጪ የሚሰራ ይሆናል፡፡

 • ሲም በመለወጥ የሚደረግን ማጭበርበር ለመከላከል ሁልጊዜ ሲም ካርድዎን መቆለፍ አይርሱ፡፡
 • ጠንካራ የይለፍ ቃል መጠቀም እንዲሁም ማንኛውንም ግላዊ መረጃዎን ከማህበራዊ ሚዲያዎች ያልተገናኘ ማድረግ፡፡
 • የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች የሚስጥር ቁጥርዎን ወይም የይለፍ ቃልዎን በምንም አይነት ሁኔታ እንዲያጋሯቸው የማይጠይቁዎት መሆኑን መረዳት
 • የግል መረጃዎችዎን ማለትም የሚላክልዎትን የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል፣ የማይ ኢትዮቴል ወይም የቴሌብር አካውንትዎን መረጃ ለማንም አለማሳወቅ፡፡
 • ከማይታወቁ ደዋዮች የሚደርስዎትን የስልክ መመሪያ አይቀበሉ፡፡
 • በማያውቁት ቁጥር ደውለው ወይም በፅሁፍ መልዕክት በስህተት የተላከ ጥቅል/የአየር ሰዓት ነው በማለት እንዲመልሱ የሚጠየቁትን ማንኛውንም ጥያቄዎች አያስተናግዱ፡፡
 • በማያውቁት ቁጥር ደውለው የአየር ሰዓት ወይም በቴሌብር ገንዘብ እንዲያስተላልፉ ከተጠየቁ ምላሽ አይስጡ፡፡

 • የቴሌብር አካውንት
 • የሞባይል ባንኪንግ ዋሌት
 • የቅድመ ክፍያ ክሬዲት
 • ዓለም አቀፍ እና ልዩ አጭር ቁጥር ጥሪ
 • የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች
 • ማንነትን በመጥለፍ የሚሰልሉ

 • አላስፈላጊ እና የማጭበርበሪያ መልዕክቶች እንደደረስዎት ሲጠራጠሩ 994 ወይም 127 ላይ ደውለው ማሳወቅ ይችላሉ፡፡
 • ሁሉንም የኢትዮ ቴሌኮም ማህበራዊ ድረ ገፆችን ተጠቅመው ጥቆማዎትን ማድረስ ይችላሉ፡፡