ፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ

ዲጂታል መታወቂያ ለአካታች ዲጂታል ኢኮኖሚ!

የዲጂታል መታወቂያ ዓይነት ሲሆን የነዋሪዎችን የባዮሜትሪክ (የጣት አሻራ፣ የአይን አይሪስ እና የፊት ምስል) እንዲሁም የግል መረጃዎችን በመሰብሰብ አንድን ግለሰብ ልዩ በሆነ መልኩ እንዲታወቅ የሚያስችል ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም መሪ የዲጂታል ሶሉሽን አቅራቢ ድርጅት በመሆኑ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ራዕይ በአጋርነት ለማሳካት እና ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን የማድረግ ራዕይ ለማፋጠን በዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ፣ በመታወቂያ ህትመትና ስርጭት፡ ማንነትን በማረጋገጥ (Authentication) ስራዎች ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

ፋይዳ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን የግለሰቦች፣ የንግዱን ዘርፍ እና የዜጎችን ችግሮች በቋሚነት ይቀርፋል፡፡

ለግለሰቦች

  • ማንነታቸውን በህጋዊ መንገድ ያላረጋገጡ ግለሰቦች መሰረታዊ የዜግነት መብቶቻቸውን አለማግኘት
  • የዜጎችን ፍላጎት ያላገናዘበ አገልግሎት አሰጣጥ
  • የተገልጋዮች ግላዊ መረጃዎች በአግባቡ ስለማያዙ ዜጎች ለዝርፍያና ለሌሎች አደጋዎች ተጋላጭ መሆን
  • ማንነትን ለማረጋገጥ ሰነዶችን ማገላበጥ የሚጠይቅ በመሆኑ የተጓተተ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖር

ለነጋዴዎች

  • የተቋማት በተንዛዛ ሂደት ቅልጥፍና የጎደለው አገልግሎት አሰጣጥ መኖር
  • የተለያዩ የንግድ ጥናቶች በመረጃ እጥረት ምክንያት ትክክለኛውን የወደፊት አደጋ በመተንበይ የቅድመ መከላከል ስራ ለመስራት መቸገር
  • አገልግሎት ተጠቃሚዎች የተሳሳተ የማንነት መረጃ ይዘው ሲመጡ ለማጣራት መቸገር እና በዚህም ምክንያት የተቋማት መጭበርበር መበርከት
  • የማንነት ማረጋገጫዎች የመገልገያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ሰነድ ማገላበጥ የሚጠይቅ መሆን የሰው ሀይል እና የጊዜ ብክነት መኖር

ለዜጎች

  • ማንነትን ማረጋገጥ አስቸጋሪ በመሆኑ ዜጎች ከማህበራዊ ተቋማት ማግኘት የሚገባቸውን አገልግሎቶች ለማግኘት መቸገር
  • በመረጃ እጥረት ምክንያት ያልተገባ የአገልግሎት አሰጣጥ መኖር
  • አጭበርባሪዎች ሀሰተኛ የማንነት መረጃዎችን በማዘጋጀት ለትክክለኛ ዜጎች መሰጠት የነበረበትን አገልግሎት ለራስ ጥቅም ማዋል
  • አብዛኛው የወቀረት ሂደትን የሚከተሉ አሰራሮች ከፍተኛ የሆነ የሰው ሀይል እንዲሁም ማስተካከያዎችን መፈለግ

እነዚህንና መሰል ችግሮች በፋይዳ ይቀረፋሉ!

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ህጋዊ ነዋሪ በሙሉ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ ነው። በመተዳደሪያ አዋጁ መሰረት በህጋዊ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ወይም የሌለው የተፈጥሮ ሰው እንዲሁም በሀገሪቱ ህግ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ወይም የሚሰራ የውጭ ሀገር ዜጋ ይካተታሉ፡፡

  • ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች መመዝገብ ይችላሉ
  • ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት, በቅርቡ ልዩ የምዝገባ ፕሮግራም የሚጀመር ይሆናል
  • ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የነዋሪነት ማረጋገጫ ያላቸው
  • የመኖሪያ አድራሻ ማረጋገጫ ሰነድ ያላቸውም ሆነ የሌላቸው
  • ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪነታቸው “በአዋጁ መሰረት” የተሰጠ
  • የት እንደሚኖሩ ምንም ዓይነት ሰነድ የሌላቸው ሰዎች የዲጂታል መታወቂያ ያለው ሰው እንደ ምስክር ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።

 

·       የቀበሌ መታወቂያ

·       ፓስፖርት

·       የልደት ሰርተፊኬት

·       የትምህርት ማስረጃ

·       የንግድ ምዝገባ ወይም የንግድ ፈቃድ ሰርተፊኬት

·       የጋብቻ ሰርተፊኬት

·       መንጃ ፈቃድ

·       የባንክ አካውንት ደብተር

·       የመኪና ሊብሬ

·       የቤት ካርታ

·       የሙያ ፈቃድ ማስረጃ

·       የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ መታወቂያ (ፎቶ ያለው)

·       የምርጫ ካርድ/መታወቂያ (የተመራጭነት/የመራጭነት ማስረጃ/መታወቂያ)

·       የጤና መድህን መታወቂያ

·       የጡረታ መታወቂያ

·       የሥራ ፈላጊ መታወቂያ

·       የተማሪነት መታወቂያ

·       ዕድር ደብተር

·       የእቁብ ደብተር

·       የህፃናት ማሳደጊያ ተቋማት የሚሰጡ በፎቶ የተደገፈ ደብዳቤ

·       የዲፕሎማት መታወቂያ(ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ መሆኑን የሚያመለክት)

·       የዲያስፖራ ነዋሪነት ማረጋገጫ /Yellow card/ ( ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ)

·       የስደተኛ ካርድ ወይም ከስደትና ስደት ተመላሽ አገልግሎት የሚሰጠው ማስረጃ

·       የሥራ ፈቃድ መታወቂያ ( ለውጭ ሃገር ዜጎች)

·       የአለም አቀፍ ተቋማት የሰራተኛ መታወቂያ

·       በማንኛውም የመንግሥት አካል የሚሰጥ መታወቂያ

·       የቀበሌ ስራ አስኪያጅ የሚሰጠው ማረጋገጫ

·       ፈቃድ ያላቸው ማንኛውም የፋይናንስ ተቋማት የሚሰጥ የማንነት ማስረጃ

·       የነዋሪነት ፍቃድ (ለውጭ ሀገር ዜጎች)

ማስታወሻ

·       ሁሉም ዓይነት ተቀባይነት ያላቸው ሰነዶች የግለሰቡን ፎቶ ማካተት አለባቸው

·       የሰነድ ማስረጃ ከሌለዎ የፋይዳ መታወቂያ ስርዓት ውስጥ የተመዘገበ የሰው ምስክር ማቅረብ ይችላሉ፡፡

በመላ ሀገሪቱ የኢትዮ ቴሌኮም    
የተመረጡ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎች   
በነፃ ይችላሉ!
   
አጋር ድርጅቶች   
   
ተንቀሳቃሽ የምዝገባ ጣቢያዎች   

በምዝገባ ወቅት የምዝገባ ባለሞያዎች የባዮሜትሪክ መረጃን (10 የጣት አሻራ፣ የ2 አይን አይሪስ እና የፊት ምስል) እና በቅድመ-ምዝገባ ወቅት የተሞሉ ተቀባይነት ያላቸውን ሰነዶችን ይሰበስባሉ።

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባዎን ካጠናቀቁ በኋላ በምዝገባ ወቅት በሰጡት ሞባይል ቁጥርዎ National ID በሚል ባለ 12 አሃዝ የፋይዳ ልዩ ቁጥር በፅሁፍ መልዕክት የሚላክልዎ ሲሆን ቁጥሩን ቴሌብር ሱፐርአፕን ላይ ከገቡ በኋላ “መተግበሪያዎች’’ የሚለውን በመጫን የብሔራዊ መታወቂያ ሚኒ አፕን በመምረጥ ቁጥሩን በማስገባት ለህትመት ዝግጁ የሆነ (softcopy) መታወቂያዎን ማግኘት ይችላሉ፡፡

  • If you did not receive your Fayda ID via SMS
  • If you lost your Fayda number
  • If you did not get your Fayda digital ID on telebirr superApp fayda mini app

Click Here https://id.et/help

Or dial 9779

0
ሀገራዊ የምዝገባ ዕቅድ
0
የ 2018 ዓ.ም ተቋማዊ ዕቅድ
0
አማካይ ወርኃዊ ተቋማዊ ዕቅድ

  1. ፋይዳዲጂታል መታወቂያ ምንነው? ጠቀሜታውስ?

ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ግለሰቦች ማንነታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል እና ለአገልግሎት አቅራቢዎች ታማኝ የዲጂታል ማረጋገጫ በዚያው ቅጽበት የሚሰጥ መታወቂያ ስርዓት ነው ።

ጠቀሚታውም;

  • መሰረታዊ “የመታወቅ መብትን” የሚሰጥ ትክክለኛ እና ህጋዊ የማንነት ማረጋገጫ ነው።
  • በሁሉም አካባቢዎች የተለያዩ የገቢ ደረጃ ላይ ላሉ እና የከተማ መስፋፋት ውስጥ ለሚካተቱ ማህበረሰቦች፣ ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲኖር የሚያስችል የመታወቂያ ስርአት ነው።
  • በባዮሜትሪክ ላይ የተመሰረተ መለያ ሲኖር የአንድ ሰው ካርድ ወይም የምስክር ወረቀት መጥፋት ማለት የማንነት ማጣት ማለት አይደለም
  • በአገልግሎት ሰጪ እና በተጠቃሚው መካከል ለሚደረጉ ግብይቶች ተአማኒነትን ይጨምራል ፣ ይህም ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል
  • በሁሉም የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖሊሲዎች ተጠያቂነትን እና ግልፅነትን ያበረታታል።
  1. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ የሆነው ማነው?

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ህጋዊ ነዋሪ በሙሉ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ብቁ ነው። በ "ረቂቅ አዋጁ" ነዋሪ የሚገለፀው “በህጋዊ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ፣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው ወይም የሌለው የተፈጥሮ ሰው እንዲሁም በሀገሪቱ ህግ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ወይም የሚሰራ የውጭ ሀገር ዜጋ ነው።” ይህም የሚያካትተው ፡-

  1. ዕድሜያቸው ከ 5 ዓመት በላይ የሆኑ ልጆች መመዝገብ ይችላሉ። ከ 5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት, በቅርቡ ልዩ የምዝገባ ፕሮግራም የምንጀምር ይሆናል።
  2. ኢትዮጵያዊ እና ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ የነዋሪነት ማረጋገጫ ያላቸው
  3. የመኖሪያ አድራሻ ማረጋገጫ ሰነድ ያላቸውም ሆነ የሌላቸው ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪነታቸው “በአዋጁ መሰረት” የተሰጠ።
  4. የት እንደሚኖሩ ምንም ዓይነት ሰነድ የሌላቸው ሰዎች ፣ የዲጂታል መታወቂያ ያለው ሰው እንደ ምስክር ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።
  5. ማንኛውም ለምዝገባ ብቁ የሆነ ሰው id.et/proof ላይ በተጠቀሰው መሰረት ተቀባይነት ያለው የማንነት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል።
  6. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የት መመዝገብ እችላለሁ?

ለአገልግሎቱ ብቁ የሆኑ ዜጎች የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት መስጫ ማዕከሎችን እንዲሁም ምዝገባ እንዲያደርጉ ፈቃድ ያላቸው አጋሮች ጋር መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የባዮሜትሪክ መረጃ መስጠት ስለሚጠበቅብዎ ለአገልግሎቱ በአካል መቅረብ ይጠበቅብዎታል፡፡

  1. የፋይዳ መታወቂያን ለማግኘት ምን ያክል መክፈል ይኖርብኛል?

ለዲጂታል መታወቂያ በነፃ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ አዋጅ መሰረት በስኬት መመዝገብዎን የሚገልፅ “የፋይዳ መለያ ቁጥር” በፅሁፍ መልዕክት የሚደርስዎ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የተረጋገጠ “የፋይዳ መለያ“ አለዎት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን የታተመ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከፈለጉ የህትመት የሚከፍሉ ይሆናል፡፡

  1. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ ምን ያክል ጊዜ ይፈጅብኛል?

ሁሉም መረጃዎች በተሟሉበት ሁኔታ ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለመመዝገብ በአማካኝ ከ5 እስከ 10 ደቂቃ ይፈጃል።

  1. የፋይዳ መለያ ቁጥር ለማግኘት ምን ያክል ጊዜ ይፈጃል?

በተሳካ ሁኔታ ምዝገባዎን ከአጠናቀቁ በኋላ መረጃዎን የማረጋገጡ ሂደት ጥቂት ደቂቃዎች አልያም የተወሰኑ ቀናት ሊወስድ ይችላል፡፡ ልዩ የፋይዳ መለያ ቁጥርዎ በምዝገባ ወቅት ባስመዘገቡት የሞባይል ቁጥር ቁጥር የሚላክልዎ ይሆናል፡፡ ያስመዘገቡት ቁጥር ሊቀየር የማይችል ብቸኛ እርስዎ የሚገኙበት አድራሻ በመሆኑ ሲያስመዘግቡ ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡

መረጃዎን ሲስተም ውስጥ ለማስገባት እና ለማረጋገጥ በእጅ (manually) ከሆነ ጥቂት ቀናት የሚወስድ ሲሆን መዘግየት ቢኖርም ነገር ግን ማረጋገጫ ቁጥርዎን በ9779 ወይም National ID Ethiopia በሚል የፅሁፍ መልዕክት የሚላክልዎ ይሆናል፡፡

  1. ከምዝገባ በኋላ መረጃዬን ማስተካከል እችላለሁ?

ደንበኞች የግል መረጃቸውን በማንኛውም ጊዜ ያረጋግጡልኛል ያሏቸውን ሰነዶች በኦንላይን ወይም በአካል በማስገባት ማስተካከል ይችላሉ፡፡ ይህ አገልግሎት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሚጀምር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ መረጃ ማደስ አይቻልም።

 

  1. ለምዝገባ የሚያስፈልጉ የሰነድ ማስረጃዎች ምን ምን ናቸው?

አሁን ላይ የሚኖሩበት ትክክለኛ አድራሻ እና የማንነት ማረጋገጫ ያስፈልጋል። እንደ፦

  • የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፈቃድ እንዲሁም ሌሎች ህጋዊ ተቀባይነት ያላቸው የግለሰቡ መለያዎች በማስረጃነት መቅረብ ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ ዝርዝር gov.et/proof ይሄን ይጫኑ
  • አንድ ግለሰብ ለመመዝገብ ትክክለኛ ሰነድ ማቅረብ ካልቻለ ዲጂታል መታወቂያ ያለው ሰው ምስክር አምጥቶ መመዝገብ ይችላል።
  1. የፋይዳ መለያ ቁጥር ከጠፋብኝ/ከረሳሁት እንዴት መልሼ ማግኘት እችላለሁ?

የፋይዳ መለያ ቁጥርዎን መልሶ ለማግኘት በምዝገባ ወቅት የሞሉትን ግላዊ ወይም የባዮሜትሪክ መረጃዎን በማቅረብ እንዲሁም አቅራቢያዎ የሚገኝ የምዝገባ ጣቢያ በመጎብኘ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ይህን በማድረግ የፋይዳ መለያ ቁጥርዎን በቀላሉ በፅሁፍ መልዕክት ወይም ከምዝገባ ጣቢያዎች ማግኘት ይችላሉ፡፡

ይህ አገልግሎት በቅርቡ የሚጀምር ሲሆን የምናሳውቅዎ ይሆናል፡፡

  1. ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መመዝገብ ግዴታ ነው?

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መብት እንጂ ግዴታ አይደለም። ሆኖም የዲጂታል መታወቂያ አዋጁ እንደሚለው፡- “ማንኛውም አካል አገልግሎትን ለማቅረብ ዲጂታል መታወቂያን የግዴታ መስፈርት አድርጎ የማቅረብ ህጋዊ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  1. የውጭ ሀገር ዜጎች ዲጂታል መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ?

አዎ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ በህጋዊ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች የነዋሪነት መታወቂያቸውን፣ ፓስፖርት ወይም ሌሎች ተዛማጅ ሰነዶችን በመጠቀም ዲጂታል መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ።

  1. የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዬ የመጠቀሚያ ጊዜው ሊያልፍ ይችላል?

የዲጂታል መታወቂያ ለአንድ ግለሰብ ልዩ የሆነ የህይወት ዘመን ቁጥር ነው። ሆኖም ግን የካርዱ እና የባዮሜትሪክ መረጃ በተወሰነ ጊዜ መታደስ አለበት። አሁን ላይ የካርድ እና የባዮሜትሪክ መረጃ በየ10 አመቱ የሚታደስ ይሆናል።

 

 

 

  1. በክልል ደረጃ ምዝገባ የምትጀምሩት መቼ ነው?

በቀጣይ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሁሉም የክልል ዋና እና በተመረጡ ከተሞች የሚጀመር ይሆናል፡፡ የፈረንጆቹ 2025 ከመጠናቀቁ በፊት 90 ሚሊዮን የተለያዩ የገቢ ደረጃ ላይ ላሉ እና የከተማ መስፋፋት ውስጥ ለሚካተቱ ማህበረሰቦች ለመመዝገብ ታቅዷል፡፡

  1. የታተመ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያዬን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

በብሔራዊ መታወቂያ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ዲጂታል መታወቂያ የሚባለው ለግለሰቡ የሚሰጠው ልዩ መለያ ቁጥር ሲሆን ይህ ቁጥር ምዝገባዎን ካጠናቀቁ በሰዓታት ወይም ከጥቂት ቀናት በኋላ በነፃ በሞባይል ቁጥርዎ የሚላክልዎ ይሆናል፡፡ የዲጂታል መታወቂያ በሚጠየቁበት ጊዜ ይህን ልዩ ቁጥር በመስጠት ማንኛውንም አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

በቅርቡ የዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት በመጀመር የምናሳውቅዎ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ለህትመት ዝግጁ የሆነውን መታወቂያዎን በቴሌብር ሱፐርአፕ ላይ መለያ ቁጥርዎን ተጠቅመው ማግኘት ይችላሉ፡፡

  1. የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ይተካል? ያላቸው ግንኙነትስ ምንድነው?

አይተካም፤ የከተማ እና የክልል የመንግስት ነዋሪ መታወቂያ ካርድ የሚሰጡት በአካባቢ አስተዳደር ነው። ነገር ግን “ፋይዳ” ዲጂታል መታወቂያ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጥ ነው። ሁለቱም “ቀበሌ” እና “ፋይዳ” እጅ ለእጅ ተያይዘው እንዲሰሩ የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው። ዲጂታል መታወቂያ ማንነትን የሚያረጋግጥ መሠረታዊ መታወቂያ ሲሆን የቀበሌ መታወቂያ ግን ተግባራዊ መታወቂያ (አገልግሎት ለማግኘት የሚጠቅም) ነው። ዲጂታል መታወቂያ የመኖሪያ አካባቢ ገደብ ሳይደረግበት በሀገሪቱ ውስጥ በየትኛውም ቦታ በተፈቀደ አካል ሊሰጥ የሚችል የአንድ ሰው ልዩ መለያ ነው። በአንፃሩ የቀበሌ መታወቂያ ሊሰጥ የሚችለው በሚኖርበት ቀበሌ ብቻ ነው።

በኢትዮ ቴሌኮም ሪጅኖች የሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት

ተቁየኢትዮ ቴሌኮም መዋቅራዊ ሪጅንየአገልግሎት ማዕከላት የሚገኙበት አካባቢ
1ማዕከላዊ ምስራቅ ሐረማያ
2ማዕከላዊ ምስራቅ ሐረር አራተኛ
3ማዕከላዊ ምስራቅ ሐረር -2
4ማዕከላዊ ምዕራብ አምቦ 2
5ማዕከላዊ ምዕራብ ሆለታ
6ማዕከላዊ ምዕራብ አምቦ
7ማዕከላዊ ምዕራብ ቱሉቦሎ
8ማዕከላዊ ምዕራብ ወሊሶ
9ማዕከላዊ ምዕራብ ሰበታ
10ማዕከላዊ ሰሜን ደብረ ብረሃን
11ማዕከላዊ ሰሜን ሰንዳፋ
12ማዕከላዊ ሰሜን ለገጣፎ
13ማዕከላዊ ሰሜን ፊቼ
14ምስራቅ ምስራቅ ጎዴ
15ምስራቅ ምስራቅ ቀብሪዳሃር
16ምስራቅ ምስራቅ ጅግጅጋ ፕሪሚየም
17ምስራቅ ዞንድሬዳዋ ኪዮስክ
18ምስራቅ ዞንቱሎ
19ምስራቅ ዞንድሬዳዋ ፕሪሚየም
20ምዕራብ ባኮ
21ምዕራብ ደምቢ ዶሎ
22ምዕራብ ጊምቢ
23ምዕራብ ነጆ
24ምዕራብ ነቀምት
25ምዕራብ ነቀምት2
26ምዕራብ ሻምቡ
27ምዕራብ ምዕራብ ባምባስ ኪዮስክ
28ምዕራብ ምዕራብ አሶሳ ፕሪሚየም
29ሰሜን አዲግራት
30ሰሜን መቀሌ
31ሰሜን አድዋ
32ሰሜን አክሱም
33ሰሜን እንደስላሴ
34ሰሜን ማይጨው
35ሰሜን መቀሌ 1
36ሰሜን ኩይሃ (መቀሌ)
37ሰሜን መቀሌ 2
38ሰሜን ምስራቅ አኬስታ
39ሰሜን ምስራቅ ባቲ
40ሰሜን ምስራቅ ደሴ 2
41ሰሜን ምስራቅ ደሴ ሰኞ ገበያ
42ሰሜን ምስራቅ ሃይቅ
43ሰሜን ምስራቅ ከሚሴ
44ሰሜን ምስራቅ ቆቦ
45ሰሜን ምስራቅ ደሴ
46ሰሜን ምስራቅ ላሊበላ
47ሰሜን ምስራቅ ወልድያ
48ሰሜን ምስራቅ ኮምቦልቻ
49ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ አዋሽ 7
50ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሎጊያ
51ሰሜን ምስራቅ ምስራቅ ሰመራ
52ሰሜን ምዕራብ አባይ ማዶ
53ሰሜን ምዕራብ ባህር ዳር 3
54ሰሜን ምዕራብ ቢቸና
55ሰሜን ምዕራብ ቻግኒ
56ሰሜን ምዕራብ ዳንግላ
57ሰሜን ምዕራብ ደብረ ማርቆስ 1
58ሰሜን ምዕራብ ፍኖተ ሰላም 1
59ሰሜን ምዕራብ ኮሶበር
60ሰሜን ምዕራብ ሞጣ
61ሰሜን ምዕራብ ባህር ዳር 1
62ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ጭልጋ
63ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ደባርቅ
64ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ደብረ ታቦር
65ሰሜን ሰሜን ምዕራብ አዘዞ
66ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ንፋስ መዉጫ
67ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ጎንደር 1
68ሰሜን አዲስ አበባፈረንሣይ
69ሰሜን አዲስ አበባ6 ኪሎ
70ሰሜን አዲስ አበባኮተቤ
71ሰሜን አዲስ አበባመገናኛ/የካ
72ሰሜን አዲስ አበባጉርድሾላ
73ሰሜን አዲስ አበባሽሮ ሜዳ
74ደቡብ አዶላ
75ደቡብ አርሲ ነጌሌ
76ደቡብ ቤንሳ
77ደቡብ ዲላ
78ደቡብ ነገሌ ቦረና
79ደቡብ ሻኪሶ
80ደቡብ ያቤሎ
81ደቡብ ይርጋጨፌ
82ደቡብ ይርጋለም
83ደቡብ ሀዋሳ ግራንድ
84ደቡብ ሀዋሳ ፕሪሚየም
85ደቡብ ሻሸመኔ ግራንድ
86ደቡብ ምስራቅ አዳማ 4
87ደቡብ ምስራቅ አሰላ
88ደቡብ ምስራቅ ባሌ ሮቤ
89ደቡብ ምስራቅ ባቱ
90ደቡብ ምስራቅ መቂ
91ደቡብ ምስራቅ መተሐራ
92ደቡብ ምስራቅ ሞጆ
93ደቡብ ምስራቅ አዳማ 2
94ደቡብ ምስራቅ ቢሾፍቱ 1
95ደቡብ ምዕራብ በደሌ
96ደቡብ ምዕራብ ጅማ ፕሪሚየም
97ደቡብ ምዕራብ ጅማ 2
98ደቡብ ምዕራብ መቱ
99ደቡብ ምዕራብ ቦንጋ
100ደቡብ ምዕራብ ሚዛን
101ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ባሮ ሜዳ
102ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ጋምቤላ ፕሪሚየም
103ደቡብ ምዕራብ ምዕራብ ኒውላንድ ኪዮስክ
104ደቡብ ደቡብ ምዕራብ አርባምንጭ 1
105ደቡብ ደቡብ ምዕራብ አርባምንጭ 2
106ደቡብ ደቡብ ምዕራብ አረካ
107ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ቡታጅራ
108ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ዱራሜ
109ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ጂንካ
110ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሆሣዕና 1
111ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ወሎያ ፕሪሚየም
112ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ወልቂጤ

በአዲስ አበባ እና አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኙ የምዝገባ ማዕከላት

ተ.ቁየአገልግሎት መስጫ ማዕከል
1ባምቢስ
2ጌጃ ሰፈር
3ካዛንቺስ
4ልደታ
5መስቀል ፍላወር
6ስታዲየም
7ተክለኃይማኖት
8ቴሌ ጋራጅ
9ውሃ ልማት
10አያት አደባባይ
11አያት ሲኤምሲ
12ቦሌ መድሃኒያለም
13ቦሌ ሚካኤል
14ቦሌ ኖቪስ
15ፊጋ
16ገርጂ
17ሀያ ሁለት
18ሰሚት 72
196 ኪሎ
20ፈረንሳይ
21ጉርድሾላ
22ኮተቤ
23መገናኛ/የካ
24ሽሮ ሜዳ
25አቃቂ 2
26ቃሊቲ
27ንፋስ ስልክ
28ሳሪስ
29አቃቂ1
30አልማዚዬ ሜዳ
31ገላን
32ቂርቆስ
33ንፋስ ስልክ
34ሳሪስ
35አለምገና
36አየር ጤና
37ቤተል
38ጀሞ
39ጀሞ 1
40ለቡ
41መካኒሳ
42ጦርሃይሎች
43ቀለቴ
44ቲፒዮ
45አዲሱ ገበያ
46አድዋ መታሰቢያ
47አራዳ
48አሸዋ ሜዳ
49አስኮ
50አውቶቢስ ተራ
51ቡራዩ
52እንቁላል ፋብሪካ
53ቀጨኔ
54ኮልፌ
55መርካቶ 02
56መርካቶ
57መሳለሚያ
58ሸጎሌ

በኢትዮ ቴሌኮም ሪጅኖች የሚገኙ ጊዜያዊ የምዝገባ ማዕከላት

ተ.ቁሪጅንየምዝገባ ማዕከል
1ማዕከላዊ ምስራቅሐሮማያ ዩኒቨርስቲ
2ማዕከላዊ ምስራቅየሐረር ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
3ማዕከላዊ ምስራቅሰዎች ለሰዎች ዩኒቨርስቲ
4ማዕከላዊ ምስራቅምስራቅ ሐረርጌ ገቢዎች ቢሮ
5ማዕከላዊ ሰሜንአረርቲ
6ማዕከላዊ ሰሜንጠባሴ ክፍለ ከተማ
7ማዕከላዊ ሰሜንሱሉልታ
8ማዕከላዊ ሰሜንጫጫ ክፍለ ከተማ
9ማዕከላዊ ሰሜንደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
10ማዕከላዊ ሰሜንደብረ ብርሃን ኢንደስትሪ ፓርክ
11ማዕከላዊ ሰሜንለገጣፎ
12ማዕከላዊ ሰሜንደብረ ብርሃን መምህራን ኮሌጅ
13ማዕከላዊ ምዕራብአምቦ ዩኒቨርስቲ ጉደር ካምፓስ
14ማዕከላዊ ምዕራብአምቦ አውቶበስ ተራ
15ማዕከላዊ ምዕራብአምቦ ዩኒቨርስቲ ሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ
16ማዕከላዊ ምዕራብአምቦ ዩኒቨርስቲ ዋና ካምፓስ
17ምስራቅ ምስራቅጂጂጋ ዩኒቨርስቲ
18ምስራቅ ምስራቅጂጂጋ ሪፈራል ሆስፒታል
19ምስራቅድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ
20ሰሜን ምስራቅ ምስራቅሰመራ ዩኒቨርስቲ
21ሰሜን ምስራቅ ምስራቅኮምቦልቻ ጨርቃጨርቅ
22ሰሜን ምስራቅ ምስራቅወሎ ዩኒቨርስቲ ደሴ ካምፓስ
23ሰሜን ምስራቅ ምስራቅደሴ መምህራን ኮሌጅ
24ሰሜን ምስራቅ ምስራቅደሴ ፔፕሲ
25ሰሜን ምስራቅ ምስራቅደሴ ሪፈራል ሆስፒታል
26ሰሜን ምስራቅ ምስራቅወሎ ዩኒቨርስቲ ኮምቦቻ ካምፓስ
27ሰሜን ምስራቅ ምስራቅኮምቦልቻ ኢንደስትሪያል ፓርክ
28ሰሜን ሰሜን ምዕራብ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፒያሳ
29ሰሜን ሰሜን ምዕራብጎንደር ሆስፒታል
30ሰሜንመቀሌ ኒቨርሲቲ አዲ ሃቂ ካምፓስ
31ሰሜንመቀሌ ኒቨርሲቲ አሪድ ካምፓስ
32ሰሜንመቀሌ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ
33ሰሜንዶ/ር ተወልደ ጤና ኮሌጅ
34ሰሜን ምዕራብባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፖሊ
35ደቡብ ምስራቅ አፄ ገላውዲዮስ ከፍተኛ እና ቴክኒክና ሞያ ት/ቤት
36ደቡብ ምስራቅ አዳማ ኢንዱስትሪየል ፓርክ
37ደቡብ ምስራቅ ሪፍት ቫሌ ዩኒቨርሲቲ
38ደቡብ ምስራቅ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
39ደቡብ ምስራቅ ናዝሬት ልብስና ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ
40ደቡብ ምስራቅ ሐራምቤ ዩኒቨርሲቲ
41ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሌጅ
42ደቡብሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ
43ደቡብሀዋሳ መምህራን ማስልጠኛ ኮሌጅ
44ደቡብሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል
45ደቡብሀዋሳ መምህራን ማስልጠኛ ኮሌጅ
46ደቡብሀዋሳ ካምፓስ ግብርና ኮሌጅ
47ደቡብሀዋሳ ነርስ ማሰልጠኛ
48ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
49ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ወለይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ
50ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
51ደቡብ ምዕራብጅማ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ካምፓስ
52ደቡብ ምዕራብጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ/የተማሪዎች መመገቢያ አካባቢ
53ደቡብ ምዕራብጅማ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ኮሌጅ
54ደቡብ ምዕራብጅማ ማዘጋጃ
55ደቡብ ምዕራብጅማ ዩኒቨርሲቲ ዋና ካምፓስ/የተማሪዎች መመገቢያ አካባቢ
56ደቡብ ምዕራብጅማ ሪፈራል ሆስፒታል
57ደቡብ ምዕራብጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ
58ደቡብ ምዕራብ ምዕራብጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ
59ደቡብ ምዕራብ ምዕራብየጋምቤላ ክልል አስተዳደር
60ምዕራብ አዋሽ ለካ ቅርጫፍ
61ምዕራብ ምዕራብ ወለጋ ዞን ማረሚያ
62ምዕራብ ነቀምት ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል
63ምዕራብ ንግድ ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት
64ምዕራብ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ-3
65ምዕራብ አዋሽ ለካ ቅርጫፍ
66ምዕራብ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ-1
67ምዕራብ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ-2
68ምዕራብ ነቀምቴ ከተማ አስተዳደር-2
69ምዕራብ ምዕራብአሶሳ ዩኒቨርሲቲ
70ምዕራብ ምዕራብየክልሉ ኪራይ ህንፃ ላይ

በአዲስ አበባ እና አዋሳኝ አካባቢዎች የሚገኙ ጊዜያዊ የምዝገባ ማዕከላት

ተ.ቁ

የምዝገባ ማዕከል
1ልደታ ክ/ከ ወረዳ 7
2ልደታ ክ/ከ ወረዳ 3
3ልደታ ክ/ከ ወረዳ 1
4ቦሌ ክ/ከ ወረዳ 5
5ቦሌ ክ/ከ
6ጉለሌ ክ/ከ ወረዳ 2
7የካ ክ/ከ ወረዳ 04
8የካ ክ/ከ
9አራዳ ክ/ከ
10አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ
11ሙለጌ ሕንጻ
12ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ
13ቄራ
14አዲስ ኢንደስትሪ ቪሌጅ (ካዲስኮ)
15ግሎባል ሆቴል
16ኮልፌ ወረዳ 9
17ንፋፋ ስልክ ላፈቶ ወረዳ 2
18አለምገና
19ጉለሌ ክፍለ ከተማ
20አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3
21ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9
22አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13
23ፊሊ ዶሮ ወረዳ ጽ/ቤት
24ቡራዩ ከተማ አስተዳደር
25አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ
26ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10
27ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05