ዕሴት ጨማሪ አገልግሎቶች (VAS)

ዕሴት ጨማሪ አገልግሎቶች

ከተለያዩ ዕሴት ጨማሪ  አገልግሎት አማራጮች መካከል የፈለጉትን መርጠው ይጠቀሙ!

የቢፕ ኮል አገልግሎታችንን በመጠቀም ያለዎት ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ ከሆነ ወይም ቁጥርዎ የአገልግሎት ጊዜው በማለፉ/ሂሳብ በወቅቱ ባለመከፈሉ ምክንያት ወጪ ጥሪ ማድረግ ባያደርግም ለደንበኞች ሚስድ ኮል ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በተሳካ ሁኔታ መላክዎትን የሚገልፅ የማሳወቂያ መልዕክት በ710 የሚደርስዎት ይሆናል፡፡

ደንብና ሁኔታዎች

 • ያላቸው ቀሪ ሂሳብ አነስተኛ/ዜሮ ለሆነ እና ወጪ ጥሪ እንዳያደርጉ የታገዱ የቅድመ ክፍያ ሞባይል ተጠቃሚዎች እንዲሁም የአገልግሎት ክፍያ/ቢል በወቅቱ ባለመክፈላቸው ወጪ ጥሪ ማድረግ የማይችሉ የድህረ ክፍያ ሞባይል ቁጥር ደንበኞች ሚስድ ኮል ማድረግ እንዲችሉ በነፃ የቀረበ አገልግሎት ነው፡፡
 • ሁሉም የቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ሞባይል ተጠቃሚዎች ደንበኞች የቢፕ ኮል አገልግሎት ተቀባይ መሆን ይችላሉ፡፡
 • አገልግሎቱ ለሀገር ውስጥ ጥሪ ብቻ የሚያገለግል ነው፡፡
 • ለአንድ የአገልግሎት ቁጥር የተፈቀደው ከፍተኛ የቢፕ ኮል መላኪያ መጠን በቀን 8 ጊዜ ነው፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች ከሚገኙ እስከ አምስት የሚደርሱ ተጠቃሚዎችን የሚያካትት የስራ ወይም የማህበራዊ ጉዳይ ስብሰባ/ ውይይት የኮንፈረንስ ጥሪ አገልግሎትን በመጠቀም በቀላሉ ያካሂዱ

የኮንፈረንስ ጥሪ አገልግሎት አጠቃቀም

 • ወደ መጀመሪያው ቁጥር ይደውሉ
 • ስልኩ እስኪነሳ ይጠብቁ
 • የደወሉላቸውን ደንበኛ ሆልድ (hold) ላይ በማድረግ ለሁለተኛውን ቁጥር ለመደወል አድ ኮል (add call) የሚለውን ይንኩ
 • ሁለተኛውን ቁጥር በመደወል እስኪነሳ ይጠብቁ
 • “conference” ወይም “Merge call” የሚለውን ሲመርጡ ከደወሉላቸው ሁለቱም ደንበኞች በጋራ ማውራት ይችላሉ
 • ተጨማሪ ሰዎችን ወደ ኮንፈረንስ ጥሪዎ ለማካተት ከቅደም ተከተሉ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያሉትን ትዕዛዛት ይድገሙ

የአገልግሎት ዋጋ

 • የደወሏቸው ጥሪዎች በሙሉ በመደበኛው የድምፅ ጥሪ አገልግሎት ዋጋ ተሰልተው አጠቃላይ ድምሩን ይከፍላሉ

 • የሞባይሎ አየር ሰዓት መጠን ዝቅተኛ ሲሆን ለሚፈላጓቸው ደንበኛ የይደውሉልኝ ጥያቄ ይላኩ
 • አገልግሎቱን ለማግኘት፡ *807*የተቀባዮን ስልክ ቁጥር# በማድረግ ይደውሉ

ካለዎት የሞባይል የአየር ሰዓት ላይ ለወዳጅ ዘመድዎ ወይም ወደ ሁለተኛ ስልክዎ አየር ሰዓት ይላኩ

አገልግሎቱን ለማግኘት፡   *806*የተቀባዮን ስልክ ቁጥር*የሚላከውን የብር መጠን# በማድረግ ይደውሉ

የአገልግሎቱ ዝርዝር አጠቃቀም እና ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

 • የሞባይል አየር ሰዓት ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በቀላሉ ለማካፈል ይረዳዎታል
 • የአየር ሰዓት ማስተላላፍ የሚቻለው ከቅድመ ክፍያ ው ቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ብቻ ነው
 • የአየር ሰዓት ተቀባዩ ደንበኛ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላለፈ መሆን ይኖርባታል
 • አንድ ደንበኛ ከ1 ብር ጀምሮ እስከ 1,000 ብር መላክ ይችላል
 • በተሳካ ሁኔታ የአየር ሰዓት ሲልኩ 20 ሳንቲም ያስከፍሎታል

ደዋዮችዎን በመረጡት የጥሪ ማሳመሪያ ጣዕመ ዜማዎች ያዝናኑ

ዋጋ
የመመዝገቢያ ዋጋ ነጻ
ወርሀዊ የአገልግሎት ዋጋ 5 ብር
የሀገር ውስጥ ዜማዎች 5 ብር
አለም ዓቀፍ ዜማዎች

7 ብር

 

ለአገልግሎቱ ለመመዝገብ ወደ 822 የእንግሊዝኛውን ፊደል ‘A’ ይላኩ ወይም www.crbt.et. ‘ን ይጎብኙ

አገልግሎቱን ለማቋረጥ ‘U’ ይላኩ

ስለ አገልግሎቱ አጠቃቀም ርጋፍ ካስፈለገዎ የእንግሊዝኛውን ፊደል ‘H’ ይላኩ

የአገልግሎቱ ዝርዝር አጠቃቀም እና ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

 • ከሌሎች ደንኞች ለየት ያለ ማንነት ያላብሶታለል
 • የሰልክ ጥሪው እስኪነሳ ያለውን ቆይታ አዝናኝ ያድርጋል
 • ደዋዮችዮን ዘና ያደርጋል
 • ለተለያዩ ደዋዮች የተለያየ የጥሪ ማሳመሪያ ምጠቀም ይችላሉ
 • እንደ ፍላጎትዎ ለተለያየ ጊዜ የተለያየ የጥሪ ማሳመሪያ መጠቀም ይችላሉ ለምሳልይ ለጠዋት፣ ለበዓላት ለቫላንታይንስ ወዘተ

በተለያየ ምክንያት በስልክዎ መገኘት በማይችሉበት ጊዜ ደዋዮችዎ የቮይስ ሜይል መልዕክት እንዲያስቅምጡልዎ ያድርጉ

የአገልግሎቱ አይነት

ዋጋ

ለአገልግሎቱ ለመመዝገብ ወይም ለማቋረጥ

ነጻ

ወርሀዊ ክፍያ

ነጻ

የተቀመጠልዎትን መልዕክት ለማዳመጥ

ነጻ

ከ824 የሚደርሱ ማሳወቂያ መልዕክቶች ክፍያ

ነጻ

የተቀመጠልዎትን መልዕክት ሲያዳምጡ ለሚነገሩ የማሳወቂያ መልዕክቶች ክፍያ

ነጻ

 

አገልግሎቱ ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

 • ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ሲሆኑ፣ ስልክ ለማንሳት ሳይመችዎ ሲቀር፣ ስልክዎ ዝግ ሲሆን ወይም ሌላ የስልክ ጥሪ እያስተናገዱ ቢሆንም ጠቃሚ መልዕክቶችን እንዲያግኙ ይረዳዎታል

ከዚህ በፊት ደውለው ማግኘት ላልቻሏችው ደንበኛ  አሁን መልሰው ቢደውሉ ሊያገኟቸው እንድሚችሉ በአጭር ጽሁፍ መልዕክት የሚያሳውቅ አገልግሎት ነው::

የአገልግሎቱ አጠቃቀም:

 • አገልግሎቱ ለሁሉም ደንበኞች የተለቀቀ ሲሆን እንደፍላጎትዎ አጭር ጽሁፍ መልዕክት እና USSD በመጠቀም ማቋረጥም ሆነ መልሰው ማስጀመር ይችላሉ.

 

አገልግሎቱን ማቋረጥ እና ማስጀመር

 • አገልግሎቱን ለማቋረጥ D1 ብለው ወደ 824 ይላኩ
 • አገልግሎቱን መልሰው ለማስጀመር A1 ብለው ወደ 824 ይላኩ

አገልግሎቱ ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

 • ውጤት አልባ የሆኑ ተደጋጋሚ ጥሪዎችን ከማድረግ ይታድጎታል
 • በተደጋጋሚ የጥሪ ሙከራ የሚያባክኑትን ጊዜ በመቆጠብ ምርታማነትዎን ያሳድጋል

 

አገልግሎት ዋጋ

 • አገልግሎቱ ለሁሉም ደንበኞቻችን ያለምንም የአገልግሎት ምዝገባ እንዲሁም ወርሀዊ ክፍያ በነጻ ይቀርቧል
 • የአጭር ጽሁፍ መልዕክት ማሳወቂያ ያለመንም ክፍያ ይደርስዎታል

ስልክዎ ዝግ በነበረበት ወይም ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ በነበሩበት ሰዓት የትኞቹ ደንበኞች ደውለው እንዳጡዎ በአጭር ጽሁፍ መልዕክት የሚያሳውቅ አገልግሎት ነው

 አገልግሎቱ ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

 • ለሁሉም ያልተሳኩ ጥሪዎች ማሳወቂያ ይደርስዎታል
 • ስልክዎ ዝግ በነበረበት ወይም ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ በነበሩበት ሰዓት ደውለው ስላጡዎ ደንበኞች የተሟላ መረጃ ያገኛሉ (የስልክ ቁጥራቸውን፣ የደወሉበትን ሰዓት ወዘተ

አገልግሎት ዋጋ

 • አገልግሎቱ ለሁሉም ደንበኞቻችን ያለምንም የአገልግሎት ክፍያ በነጻ ይቀርቧል

የአገልግሎቱ አጠቃቀም:

 አገልግሎቱ ለሁሉም ደንበኞች ተለቋል

አገልግሎቱን ማቋረጥ እና ማስጀመር

 • አገልግሎቱን ለማቋረጥ D2 ብለው ወደ 824 ይላኩ
 • አገልግሎቱን መልሰው ለማስጀመር A2 ብለው ወደ 824 ይላኩ

 • ስልክ እያነጋገሩ ሌላ አስፈላጊ ጥሪ ቢመጣ ምልክት የሚሰጥዎ እና እንዳያመልጥዎት የሚያስችል አገልግሎት ነዉ
 • አገልግሎቱ በነፃ የሚሰጥ ሲሆን በአብዛኛው ስልኮች ላይ ይገኛል፡፡

 • ገቢ ጥሪዎችን ወደሌላ ቁጥር ማስተላለፍ የሚያስችልዎ አገልግሎት ነው
 • አገልግሎቱን ስልክዎን በመጠቀም ማስጀመርም ሆነ ማቋረጥ ይችላሉ
 • ከታች በተዘረዘሩት ሁኔታዎች ውስጥ ሲሆኑ ጥሪዎችዎ ወደ ሌላ ስልክ እንዲተላለፍ ማድረግ ይችላሉ
 • ሌላ ጥሪ እያስተናገዱ ሲሆን
 • ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጭ ሲሆኑ
 • ስልኩን ሳያነሱት ሲቀር
 • ሁሉንም ገቢ ጥሪዎች እንደፍላጎትዎ ማስተላለፍ ይችላሉ

አገልግሎቱ ለደንበኞች የሚያስገኘው ጥቅም

 • መገኘት ባልቻሉበት ሰዐት ጠቃሚ ስለኮች እንዳያመልጡዎ ይረዳል

አገልግሎት ዋጋ

 • የአገልግሎት ምዝገባ ክፍያ: በነጻ
 • የአገልግሎት ክፍያ:
 • በመደበኛ ሰዓት : በደቂቃ 50 ሳንቲም (ተእታን ጨምሮ)
 • ከመደበኛ ሰዓት ውጪ: በደቂቃ 35 ሳንቲም (ተእታን ጨምሮ)

 • ለማስታወስ እና ለመደወል ቀላል የሆኑ በአራት ምድቦች የተመደቡ (ፕላቲኒየም ፣ ወርቅ ፣ ብር እና ነሐስ) የሞባይል ስልክ ቁጥሮችን በአቅራቢያዎ ባለ የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ለሥራ፣ ለትምህርት ወይም ለሌላ ጉዳይ ወደ ውጪ አገር ሲሄዱ አልያም ሀገር ውስጥ ሆነው ረዘም ላለ ጊዜ የመደበኛ ወይንም የሞባይል ስልክዎን ሳይጠቀሙበት ለማቆየት ቢፈልጉ ቁጥሬን ያቆዩልኝ አገልግሎትን በመጠቀም ቁጥርዎን በአደራ እንዲቀመጥልዎት በማድረግ መልሰው መጠቀም ይችላሉ፡፡

ቁጥርዎን እስከ 5 ዓመታት ድረስ ማቆየት ይችላሉ፡፡

የአገልግሎት ዋጋ በዓመት 109 ብር

አገልግሎቱን ለማግኘት የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከል ይጎብኙ፡፡