የሞባይል ሼር ፕላን አገልግሎት

የሞባይል ሼር ፕላን

ድርጅቶች በነፃነት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ያደረጓቸውን ሰራተኞች የሚያስፈልጋቸውን የጥቅል መጠን መወሰን እና መቆጣጠር የሚያስችል አገልግሎት ነው፡፡ የቡድን አስተዳዳሪነት ድርሻ የተሰጠው አባል የመቆጣጠር፣ ለእያንዳንዱ አባል የሚያስፈልገውን ወርሃዊ የቴሌኮም አገልግሎት የመወሰን እንዲሁም አባላት ከክፍያ ሁኔታ ጋር የሚኖራቸውን ትስስር መወሰን ይችላል፡፡ በተጨማሪም የተመደበላቸውን አገልግሎቶች ቀድመው የሚጨርሱ ሰራተኞች ካሉ ከሌሎች ተጠቃሚዎች በመቀናነስ ለሚያስፈልጋቸው አባላት በቀላሉ ማዘዋወር ይቻላል።

ለድርጅት ደንበኞቻችን የሚያሰገኘው ጥቅም
 • በድርጅትዎ የተመረጠ የቡድን አስተዳዳሪ ለአባላት የሚታደለውን ጥቅል መጠን መወሰን፣ አባላትን የማካተት እንዲሁም የማስወጣት፣ ለሁሉም/ለተመረጡ የአባላት አገልግሎት ቁጥሮች የክፍያ ሁኔታን መወሰን፣ ከ < 50ሺህ ፕላን ሲሆን የቡድን ስያሜ መቀየር እንዲሁም > 100ሺህ ለሆኑ ፕላኖች በሰራተኞች መካከል ለመደዋወል የሚረዳ አጭር ቁጥር ለመምረጥ ይችላል፡፡
 • ቅናሽ የተደረገበት የቴሌኮም አገልግሎት ዋጋ
 • በአባላት መካከል ለመደዋወል የሚረዳ አጭር ቁጥር
 • ከፍተኛ ቅናሽ ያላቸው አገልግሎቶች እንዲሁም በአባላት የሚደረግ ነፃ የጥሪ
 • ያልተጠቀሙበት ነፃ ጥቅል ወደ ቀጣይ ወር ይተላለፋል
 • በድርጅቱ ፍላጎት መሰረት የጥቅል መጠን እንደአስፈካጊነቱ ለአባላት በድጋሚ መመደብ ፣ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
 • ከብር 500 ጀምሮ 20 የሞባይል ሼር ፕላን አማራጮች ያሉን ሲሆን ከአማራጮቹ በተጨማሪ ድርጅቶች የቴሌኮም በጀታቸውን መሰረት አድርገው በፈለጉት የብር መጠን እና የሠራተኞቻቸውን ብዛት በማሳወቅ በጀታቸውን ያገናዘበ የድምፅ፣ ዳታ፣ አጭር መልዕክት እና በሰራተኞች መካከል የሚደረግ ነፃ የጥሪ መጠን ተዘጋጅቶ የሚቀርብላቸው ይሆናል፡፡

4. እርስ በርስ ለመደዋወል የሚያገለግል አጭር ቁጥር (ኤምኤስፒ 50,000 እና ከዛ በላይ)

 • የኤምኤስፒ 50,000 እና ከዛ በላይ ተጠቃሚ ደንበኞች በተደጋጋሚ ወደሚደወሉ ቁጥሮች ከ200000 እስከ 200030 ድረስ ያሉ አጭር ቁጥሮችን በመጠቀም መደወል ይችላሉ።

5. ሲዩጂ

 •  ከኤምኤስፒ_50,000 ጀምሮ በሰራተኞች መካከል ያልተገደበ ጥሪ

6. ጥቅም ላይ ያልዋለ አገልግሎት ወደ ቀጣዩ አንድ ወር ይዛወራል

7. ደንበኛው ለአባላት የተሰጠውን የቴሌኮም አገልግሎት በፈለገ ጊዜ በድጋሚ መመደብ ፣ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።

8. አከፋፈል፡- ደንበኞች ከክፍያ አፈጻጸም አማራጮች  በአንድ ጊዜ ሙሉ ክፍያ ወይም በከፊል መምረጥ ይችላሉ።

አገልግሎቱን እንዴት ማግኘት ይቻላል?

አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያዎ የሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከልን ይጎብኙ!

 • ለሁሉም ወይም ለተወሰኑ የአገልግሎት ቁጥሮች የአከፋፈል ሁኔታ በአካል የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመምጣት ማስወሰን ይቻላል፡፡
 • ሁሉም የሞባይል ሼር ፕላን አማራጮች አስፈላጊውን ማስረጃ በመያዝ አቅራቢያዎ የሚገኝ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከላችን ቀርበው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 • ለትልቅ ድርጅቶች፣ ለጥቃቅንና አነስተኛ፣ መለስተኛ ንግድ እና አገልግሎት እንዲሁም መሰረታዊ የድርጅት ደንበኞች ለሞባይል ሼር ፕላን 500 እስከ ሞባይል ሼር ፕላን 50,000 ድረስ ለመመዝገብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 • ሁሉም የኮርፖሬት ድርጅት ደንበኞች ከ50,000 በላይ የሞባይል ሼር ፕላን አማራጭ ለምዝገባ ማመልከት ይችላል፡፡
 • አንድ የሞባይል ሼር ፕላን ቡድን ለመኖር ቢያንስ አንዱን አገልግሎት መመዝገብ ይኖርበታል፡፡ በፊት የሚጠቀሙት የሞባይል ሼር ፕላን አገልግሎት ወደ ሌላ አገልግሎት ደንበኞች ከፈለጉ በማንኛውም ጊዜ መቀየር ይችላሉ፡፡ ይህም ሲሆን በፊት የተመዘገቡበት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ አዲሱ አገልግሎት የሚጀምር ይሆናል፡፡ አገልግሎቱን ለመቀየር ክፍያ የሌለው ሲሆን ደንበኞች ወደ አገልገልሎት ማዕከላችን በአካል ቀርበው ማስደረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ሞባይል ሼር ፕላንን ለማስተዳደር በሲአርኤም እና በኢ-ኬር ሲስተም ይሆናል፡፡
 • ከፍተኛው የአባላት መጠን በኢ-ኬር ሲሰተም መስተካከል የማይችል ሲሆን ነገር ግን ደንበኞች የአገልግሎት ማዕከላችን በአካል በመቅረብ በመረጡት ፕላን መሰረት የተፈቀደው የአባላት ብዛት ማስወሰን ይችላሉ፡፡
 • የቡድን አስተዳዳሪ ከታች የተዘረዘሩትን ተግባራት ማከናወን ይችላል
  • የጥቅል መጠኖችን ለቡድን አባላት ማከፋፈል
  • አባላትን መቀነስ/መጨመር
  • ነፃ የቴሌኮም አገልግሎቶችን ከቡድን አባላት መቀነስ፣ መጨመር እንዲሁም በድጋሚ መመደብ
  • ከሞባይል ሼር ፕላን 50 ሺህ በታች ላሉ አገልግሎቶች የቡድን ስያሜ መቀየር
  • ከ100 ሺህ በላይ ለሆኑ የሞባይል ሼር ፕላን አማራጮች አባላት የሚደዋወሉበት አጭር ቁጥር መወሰን
 • ቅናሽ የተደረገበት የቴሌኮም አገልግሎት ዋጋ ተጠቃሚ ለመሆን ቅድመ ሁኔታዎች
  • ደንበኛው ንቁ የሞባይል ሼር ፕላን ቡድን አባል/የቡድን አስተዳዳሪ መሆን አለበት
  • አባል የሆነበት የሞባይል ሼር ፕላን ቢያንስ አንድ አገልግሎት የተመዘገበ መሆን አለበት
  • ደንበኛው ነፃ የቴሌኮም አገልግሎት ካለው ተጠቅሞ መጨረስ አለበት
 • አንድ ደንበኛ አባል እንደተደረገ ነፃ የቴሌኮም አገልግሎቶች እስኪመደቡለት ድረስ ለአባላት የተፈቀደውን የቴሌኮም አገልግሎት በከፍተኛ ቅናሽ መጠቀም ይችላል፡፡
 • ነፃም ሆነ ቅናሽ የተደረገባቸው የቴሌኮም አገልግሎቶች ለአጭር ቁጥር እና ለዓለም አቀፍ ግልጋሎት አይውሉም፡፡
 • አባላትም ሆኑ የቡድን አስተዳዳሪ የሞባይል ሼር ፕላን ተጠቃሚ በመሆናቸው ያገኙትን ነፃ የቴሌኮም አገልግሎቶች ወደ ሌላ ሶስተኛ ወገን ማጋራት እንዲሁም ወደ ሌላ አገልግሎት ቀይረው መጠቀም አይችሉም፡፡
 • የሀይብሪድ፣ የቅድመክፍያ እና ድህረ ክፍያ ደንበኞች የሞባይል ሼር ፕላን አገልግሎትን በአባልነት መጠቀም ወይም የቡድን አስተዳዳሪ መሆን ይችላሉ፡፡
 • ትልቅ ድርጅቶች፣ ጥቃቅንና አነስተኛ፣ መለስተኛ ንግድ እና አገልግሎት እንዲሁም መሰረታዊ የድርጅት ደንበኞች የሚጠቀሙት ሞባይል ሼር ፕላን 500 እስከ ፕላን 50 ሺህ የአገልግሎቱ ባለቤት መሆን የሚችለው ድህረ ክፍያ ተመዝጋቢ የሆነ ቁጥር ብቻ ነው፡፡
 • የሞባይል ሼር 50 ሺህ በላይ ፕላን ባለቤት ለመሆን የኮርፖሬት ቢዝነስ የደንበኝነት ድህረ ክፍያ አካውንት ቁጥር ካላቸው መጠቀም ወይም አዲስ ማውጣት ይችላሉ፡፡
 • የሞባይል ሼር ፕላን 50 ሺህ እና ከዛ በላይ ለሆነ አገልግሎት የቅድመ ክፍያ/ድህረ ክፍያ/ሀይብሪድ ተመዝጋቢዎች አስተዳዳሪ መሆን የሚችሉ ነገር ግን የባለቤቱ አካውንት ድህረ ክፍያ ኮርፖሬት አካውንት መሆን አለበት፡፡
 • አዲስ የቡድን አባል ወይም አስተዳዳሪ ለመሆን የደንበኛው የአገልግሎት ቁጥር ንቁ መሆን አለበት፡፡
 • አንድ የሞባይል ሼር ፕላን ቡድን አባል በአንድ ጊዜ የሌላ ሞባይል ሼር ፕላን ቡድን መሆን አይችልም፡፡
 • ለሁሉም አገልግሎቶች ያልተጠቀሙት ቀሪ የቴሌኮም አገልግሎት መጠን ካለ ከቀጣይ አንድ ወር ብቻ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
 • ደንበኞች ለሞባይል ሼር ፕላን እየተጠቀሙበት ባለው አካውንት መመዝገብ ወይም ለአዲስ ፕላን በመመዝገብ ቀድመው ላዘጋጇቸው ቡድን አባላት ማከፋፈል ይችላሉ፡፡
 • በቡድን አባላት መካከል የተፈቀደን ነፃ ጥሪ ከአባላት ውጪ ለመደዋወል መጠቀም አይችሉም፡፡
 • አገልግሎቱ ለሞባይል ቁጥሮች ብቻ የሚሰራ ሲሆን ሌሎች አገልግሎቶች (እንደ ብሮድባንድ፣ መደበኛ ስልክ) የቡድን አባል እንዲሁም የቡድን አስተዳዳሪ ለመሆን ብቁ አይደሉም፡፡
 • የቡድን አስተዳዳሪ አንድ አባል ምን አይነት አገልግሎት ማግኘት እንዳለበት መወሰን ይችላል፡፡ ለምሳሌ የተወሰኑ የቡድን አባላት የድምፅ አገልግሎት ብቻ ሊያገኙ ይችላሉ፣ የተወሰኑት የዳታ አገልግሎት ብቻ ሊፈቀድላቸው ይችላሉ እንዲሁም ለሌሎች አባላት ሁሉንም የድምፅ፣ የዳታ፣ የመልዕክት እና የሲዩጂ አገልግሎት እንዲያገኙ ሊፈቀድላቸው ይችላል፡፡
 • አባላት ከታች ባለው የአጠቃቀም ቅድመ ሁኔታ መሰረት የቴሌኮም አገልግሎቶችን መጠቀም ይችላሉ
  • በአባላት መካከል ለሚደረግ ጥሪ ቅድሚያ የሲዩጂ ነጻ ደቂቃ እንዲጠቀሙ ይደረጋል
  • ቀጥሎ ግለሰቡ በራሱ የገዛው ጥቅል ካለ እንዲጠቀም ይደረጋል
  • በመቀጠል የተመደበላቸው ነፃ የቴሌኮም አገልግሎት
  • የደንበኞች አከፋፈል ሁኔታ ከታች ከተጠቀሱት ሁለቱ አማራጮች ማስወሰን ይችላሉ፡፡
   • ሙሉ ክፍያ፡ ሁሉም ክፍያዎች ተመዝጋቢው ድርጅት መክፈሉን እስካላቋረጠ ድረስ ሙሉ በሙሉ ክፍያዎችን የሚሸፈን ይሆናል፡፡
   • የተወሰነ ድርሻ እና ግማሽ ክፍያ፡ አባላት የተወሰነ የተጠቀሙበት የቴሌኮም አገልግሎት ክፍያ በተመዝጋቢው ድርጅት የሚሸፈን ሲሆን ነው፡፡
  • 5 የቡድን አባላት የተመደበላቸው ነፃ የቴሌኮም አገልግሎት ከሌለ ወይም ተጠቅመው ከጨረሱ በከፍተኛ ቅናሽ አገልግሎቶችን ማግኘት ይቀጥላሉ፡፡
  • ደንበኞች ከሞባይል ሼር ፕላን አባልነት ከተሰረዙ ነባር የአጠቃቀም ደንብና ሁኔታዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
 • አባላት ወይም የቡድን አስተዳዳሪዎች ከንቁ የሞባይል ሼር ፕላን አባልነት ሳይሰረዙ የአገልግሎት ቁጥራቸውን እንዲዘጋ/ከአገልግሎት መስጫ ውጪ እንዲደረግ መጠየቅ አይችሉም፡፡
 • ከአባልነት የተሰረዘ ደንበኛ ከሞባይል ሼር ፕላን ጋር የተያያዘ ማንኛውንም ጥቅም ማግኘት አይችልም፡፡
 • አንድ የሞባይል ሼር ፕላን ቡድን በተመሳሳይ ጊዜ እንዲኖረው የተፈቀደ ከፍተኛው የቡድን አስተዳዳሪ ብዛት 10 ብቻ ነው፡፡
 • ለአገልግሎቱ የተመዘገበ ድርጅት ያልተከፈለ ሂሳብ እያለው አገልግሎት እንዲቋረጥ መጠየቅ አይችልም፡፡

 

ስለአገልግሎቱ መረጃ ለማግኘት 09 - 00-74-74-74 ይደውሉ::

ለተጨማሪ መረጃ እና ምዝገባ አቅራቢያዎ የሚገኝ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከል ይጎብኙ!