የቢዝነስ ሞባይል ጥቅሎች

ቢዝነስ ሞባይል ጥቅል

ለቢዝነስ ሞባይል ጥቅል ይመዝገቡተጨማሪ የድምፅ ጥሪ ቅናሽ ያግኙ!

ያልተገደበ ሲዩጂ

ይህ አገልግሎት ለድርጅትዎ በልዩነት የቀረበ ሲሆን በሰራተኞችዎ መካከል ቢል ይቆጥርብኛል ከሚል ስጋት ነፃ ሁነው እንዲነጋገሩ፤ እንዲፃፃፉ ያግዛል። በዚህ ቡድን ውስጥ፣ ሰራተኞችዎ እርስ በርስ ያለምንም ገደብ የድምፅ ጥሪዎችን ማድረግ እና የጽሁፍ መልዕክቶችን መላላክ ይችላሉ፤ ይህም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በነፃ በድርጅትዎ በኩል ይቀርብላቸዋል።
አዎ፣ በትክክል አንብበዋል – ስለ ደቂቃ ወይም ስለ እያንዳንዱ መልዕክት ዋጋ ሳይጨነቁ፣ ገደብ የለሽ የውስጥ ለውስጥ ጥሪዎችን እና መልዕክቶችን መጠቀም ይችላሉ።

የአገልግሎት ዓይነትየሰራተኛ ብዛት ዋጋ
ያልተገደበ ድምፅ እና የፅሁፍ መልዕክት ሲዩጂ ከ100 በላይ ሰራተኞች

150 ብር

ያልተገደበ ድምፅ እና የፅሁፍ መልዕክት ሲዩጂ ከ 41 እስከ 100 ሰራተኞች

165 ብር

ያልተገደበ ድምፅ እና የፅሁፍ መልዕክት ሲዩጂ ከ 21 እስከ 40 ሰራተኞች

175 ብር

ያልተገደበ ድምፅ እና የፅሁፍ መልዕክት ሲዩጂ እስከ 20 ሰራተኞች

185 ብር

የአገልግሎት ዓይነትየሰራተኛ ብዛት ዋጋ
ያልተገደበ ድምፅ ሲዩጂከ100 በላይ ሰራተኞች

145 ብር

ያልተገደበ ድምፅ ሲዩጂከ 41 እስከ 100 ሰራተኞች

160 ብር

ያልተገደበ ድምፅ ሲዩጂከ 21 እስከ 40 ሰራተኞች

165 ብር

ያልተገደበ ድምፅ ሲዩጂ እስከ 20 ሰራተኞች

175 ብር

የሀይብሪድ ጥቀል

250 ደቂቃ

100 የፅሁፍ መልዕክት

75 ብር

600 ደቂቃ

150 የፅሁፍ መልዕክት

145 ብር

2000 ደቂቃ

500 የፅሁፍ መልዕክት

370 ብር

3000 ደቂቃ

750 የፅሁፍ መልዕክት

450 ብር

ያልተገደበ ድምፅ እና የፅሁፍ መልዕክት

1,100 ብር

  • አገልግሎቱ ለሁሉም ቅድመ ክፍያ፣  ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ተጠቃሚዎች የቀረበ ሲሆን ነገርግን ያልተገደበ ሲዩጂ ዋና ሂሳብ (ከፋዩ) የድህረ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን ይኖርበታል፡፡
  • ከማሽን ወደ ማሽን፣ ዳታ ብቻ፣ መደበኛ ስልክ እና መደበኛ የብሮድባንድ አገልግሎት ቁጥሮች ያልተገደበ  የሲዩጂ አባል መሆን አይችሉም፡፡
  • ያልተገደበ የሲዩጂ ኢንተርፕራይዝ ደንበኛ በደብዳቤ እስከጠየቀ ድረስ የግለሰብ ደንበኞች አገልግሎቱን ለመጠቀም አባል መሆን ይችላሉ።
  • ለሁሉም የተመዘገቡ ቁጥሮች ገዢው ድርጅት ወርሃዊ ክፍያን ይሸፍናል።
  • በአንድ ቡድን ውስጥ የሚፈቀደው ዝቅተኛው የሲዩጂ አባላት መጠን አምስት ነው።
  • አንድ የአገልግሎት ቁጥር አባል መሆን የሚችለው ለአንድ ሲዩጂ ቡድን ብቻ መሆን አለበት።
  • ያልተገደበ የሞባይል ድምጽ ጥሪ እና መልዕክት መጠቀም የሚፈቀደው በአባላት መካከል ብቻ ነው።
  • ከቡድኑ አባላት መካከል በተለያየ ምክንያት የተቋረጠ ቁጥር ቢኖርም ሌሎች አባላት ላይ ተጽዕኖ አይደርስባቸውም።
  • አገልግሎቱ ከሲዩጂ አባላት ውጭያሉ ጥሪዎችን፣ አጭር ቁጥር አገልግሎት እና ዓለም አቀፍ ቁጥሮችን እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎትን አያካትትም። የተዘረዘሩት አገልግሎቶች በመደበኛታሪፍ መሰረት ተጠቃሚው የሚከፍል ይሆናል።
  • ገዢው ድርጅት በወሩ ውስጥ በማንኛውም ጊዜ አባላትን የመጨመር ወይም የመሰረዝ መብት አለው ነገርግን በወሩ መጀመሪያ ላይ ቢያደርገው የሚመከር ሲሆን ይህም ተጨማሪ የሲዩጂ ወርሃዊ ኪራይ በቢል መክፈያ ወቅት እንዳይከፍል ይረዳዋል፡፡
  • ሁሉም ዋጋዎች ተ.እ.ታን ያካተቱ ናቸው።

ተጨማሪ መረጃዎች

  • የጥቅል ጥሪዎች ለመደበኛ እና ሞባይል ቁጥሮች ብቻ የቀረቡ ናቸው፡፡
  • ለሁሉም ጥቅሎች፣ ደንበኞች የስድስት ወር የአገልግሎት ስምምነት ውል መግባትአለባቸው።
  • ሁሉም ታሪፎች ተ.እ.ታን ያካተቱ ናቸው
  • ሌሎች የቢዝነስ ሕጎች አይለወጡም።

የደንበኝነት ምዝገባ መስፈርቶች

የደንበኛ አይነት የመመዝገቢያ መስፈርቶች
ቁልፍ ደንበኞች (Key account) የሆኑ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ኤምባሲዎች፣ መለስተኛ፣ አነስተኛና ጥቃቅን ድርጅቶች የአገልግሎት መጠየቂያ ደብዳቤ
የጂኤስኤም (GSM) የድህረ ክፍያ መመዝገቢያ መስፈርት
የቢዝነስ ሲዩጂ ሞባይል ዝርዝር መስመሮችን ማቅረብ
የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ወደ ድህረ ክፍያ መቀየር አለባቸው
የደንበኝነት ምዝገባ ክፍያ መክፈል
በቢዝነስ ፖሊሲው መሠረት ገንዘብ ተቀማጭ ማድረግ