የጥሪ ማሳመሪያ ከ አዳዲስ ገጽታዎች ጋር

የጥሪ ማሳመሪያ
 • ፍላጎትዎን ግምት ውስጥ በማስገባት የጥሪ ማሳመሪያ አገልግሎት በአዲስ አቀራረብ ተዘጋጅቷል፡፡ ለአገልግሎቱ በመመዝገብ ደዋዮችዎን እንዲሁም ራስዎን ዘና ያድርጉ!

 

የአገልግሎት ዓይነቶች

መደበኛ ጥሪ ማሳመሪ (ደዋዮችዎ የሚሰሙት)

የደዋይ ጥሪ ማሳመሪያ (ወጪ ጥሪ ሲያደርጉ ለራስዎ የሚሰማ)

የአገልግሎት ክፍያ
 • ወርሃዊ ኪራይ: 5 ብር
 • የቶን ግዢ: 5 ብር

የጥሪ ማሳመሪያ / ሲአርቢቲ ባህሪያት እና ጥቅሞች

ለአገልግሎቱ መመዝገብ፡-
 • A ወደ 822 መላክ
 • 822 ወይም *822# ይደውሉ
 • ወደ www.crbt.et ይጎብኙ
ጥሪዎችን ለመምረጥ እና አገልግሎቱን ለማስተዳደር
 • 822 ይደውሉ እና መጠየቂያውን ይከተሉ
 • በድረ-ገጻችን www.crbt.et ወይም
 • *822# ይደዉሉ

 

በ822 የፅሁፍ መልዕክት በመላክ የሚያገኟቸው መሰረታዊ አገልግሎቶች ማውጫ

ቁጥር

የአገልግሎት ዓይነት

መደበኛ ጥሪ መሳመሪያ

የደዋይ ጥሪ መሳመሪያ

1

ለአገልግሎቱ ይመዝገቡ

AA1
2

የጥሪ ማሳመሪያ  ለመግዛት

C የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር

C የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር

3

የጥሪ ማሳመሪያ ለመምረጥ

SN የቶን ኮድ

SC የቶን ኮድ


4

ሌሎች የሚጠቀሙትን ጥሪ ማሳመሪያ ለመቅዳት/ለራስዎ ለመጫን

መልሰው በመደወል ደንበኛው ከማንሳታቸው በፊት * ን ይጫኑ 


*


*


5


ለሌሎች ደንበኞች የጥሪ ማሳመሪያ በስጦታ ለመላክ

G የጥሪ ማሳመሪያ ኮድ

የተቀባዩ ስልክ ቁጥር

ምሳሌ: G 123456 09XXXXXXXX

G የጥሪ ማሳመሪያ ኮድ

የተቀባዩ ስልክ ቁጥር

ምሳሌ: G 123456 09XXXXXXXX

6

ስጦታ መቀበል

ga የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር

ga የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር

7

ስጦታን አለመቀበልዎትን ለማሳወቅ

gr የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር

gr የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር

8

እርዳታ ለማግኘት

HH
9

ከግል ማህደርዎ የጥሪ ማሳመሪያ ለመምረጥ

PP
10

የግል መቼት ለመጠየቅ 

QCQC
11

የጥሪ ማሳመሪያ መቼት ለማጥፋት

DC የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር

DC1 የጥሪ ማሳመሪያ መለያ ቁጥር

12

አገልግሎቱን በጊዜያዊነት ለማቋረጥ

DAC

DAC1
13

በጊዜያዊነት የተቋረጠውን መልሶ ለማስጀመር

ACAC1

14

አገልግሎቱን ለማቋረጥ

U

U1

 • ሁሉም የቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ሞባይል ተጠቃሚዎች ለአገልግሎቱ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
 • ደንበኞች ለመደበኛ እንዲሁም ለደዋይ ጥሪ ማሳመሪያ አገልግሎት በተመሳሳይ ጊዜ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
 • የጥሪ ማሳመሪ አገልግሎት 822 ላይ የድምፅ ጥሪ በማድረግ, *822# በመደወል እንዲሁም በድረ ገፃችን https://www.crbt.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • የጥሪ ማሳመሪያ ተጠቃሚ ላልሆነ ደንበኛ የመረጡትን የጥሪ ሙዚቃ ገዝተው በስጦታ ለመላክ ከፈለጉ በተጨማሪ የሚቀበለውን ደንበኛ የአንድ ጊዜ ወርሃዊ መመዝገቢያ መክፈል ይጠበቅብዎታል፡፡ ስጦታው የደረሰው ደንበኛ ለአገልግሎቱ መመዝገብ እንደሚፈልግ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት በአንድ ሰዓት ውስጥ ምላሽ መስጠት የሚጠበቅበት ሲሆን ከምዝገባው በኋላ የተበረከተለት የጥሪ ሙዚቃ የሚደርሰው ይሆናል፡፡
 • የጥሪ ማሳመሪያ ለመረጡት ደንበኛ ወይም ደንበኞች ለመረጡት ሙዚቃ በመክፈል በአንድ ጊዜ መላክ ይችላሉ፡፡
 • ወደሌሎች ደንበኞች ሲደውሉ ሰምተው ለራስዎ የፈለጉትን የጥሪ ማሳመሪያ ለመጠቀም ስልኩ ሳይነሳ (*) ምልክት በመጫን በስልክዎ የሚላክልዎትን የጥሪ ማሳመሪያው የመለያ ቁጥር ወደ 822 በመላክ የራስዎ ማድረግ ይችላሉ፡፡ የጥሪ ማሳመሪያው ተጠቃሚው ሌሎች ደንበኞች ጥሪውን እንዳይቀዱበት የማገድ መብት አለው፡፡·         ማንኛውም ደንበኛ ሲመዘገብ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጫነው ጥሪ መቀዳት የማይቻል ሲሆን ሌሎች ተጠቃሚ ደንበኞች ከመጀመሪያው ጥሪ ውጪ የቀየሩትን ማንኛውም ጥሪ ሰምተው ከወደዱት የራስዎ ማድረግ ይችላሉ፡፡
 • ለአገልግሎቱ እንደተመዘገቡ የመጀመሪያው ጥሪ በነፃ የሚጫን ሲሆን በማንኛውም ጊዜ አዲስ ጥሪ መቀየር ይቻላል፡፡
 • ደንበኞች የገዟቸው እስከ 20 የሚደርሱ ጥሪ ማሳመሪያዎች በግል ማህደራቸው የሚቀመጡ ሲሆን በማንኛውም ጊዜ መርጠው ከማህደራቸው ሊያጠፏቸው ይችላሉ፡፡
 • ደንበኞች በጊዜያዊነት የጥሪ ማሳመሪያ ማቋረጥ የሚችሉ ሲሆን በግል ማህደራቸው የተቀመጡት ጥሪ ማሳመሪያዎች ሳይጠፉባቸው በድጋሚ ማስጀመር ይችላሉ፡፡
 • ደንበኞች ወርሃዊ ኪራይ መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህን ለማድረግ በቂ ሂሳብ ከሌላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመዘገቡ የሚደረገው ነባር የጥሪ ማሳመሪያ የሚሰማ ሲሆን ኪራዩ ከ7 ቀናት በኋላም የማይከፈል ከሆነ አገልግሎቱ በጊዜያዊነት ይታደገዳል፡፡ ነገር ግን ደንበኞች ከ15 ቀናት በኋላ ወርሃዊ ክፍያውን መፈፀም ካልቻሉ አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ይደረጋል፡፡
 • ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ አገልግሎቱን ማቋረጥ የሚችሉ ሲሆን በድጋሚ አገልግሎቱን ለማግኘት ሲፈልጉ እንደ አዲስ ደንበኛ የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡