• አገልግሎቱ ዳታ ብቻ መጠቀም ለሚፈልጉ ለግለሰብ ደንበኞች በድህረ ክፍያ አማራጭ የቀረበ አገልግሎት ነው፡፡
• የ4ጂ ኤልቲኢ ኔትወርክ ባለባቸው ነገር ግን የመደበኛ ባለገመድ ብሮድባንድ ኢንተርኔት መጠቀም ላልቻሉ ደንበኞች የቀረበ ነው፡፡
• ሁሉም የጥቅል ዋጋዎች በየወሩ የሚከፈልባቸው ሲሆን አገልግሎቱ በቋሚነት በየወሩ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
• መጠንን መሰረት ያደረገ ጥቅል የሚጠቀሙ ከሆነ ከመደበኛ ሰዓት ውጪ የሚባለው ከምሽቱ 3 ሰዓት እስከ ጠዋት 2 ሰዓት ነው፡፡
• ደንበኞች ለአገልግሎቱ እንደተመዘገቡ ወዲያውኑ አገልግሎቱ የሚቀርብላቸው ይሆናል፡፡ የወሩ የመጀመሪያ ቀን ውጪ ለአገልግሎቱ ከተመዘገቡ በወር ውስጥ የሚጠቀሙበት ቀናት ብቻ ተሰልቶ የጥቅል መጠን የሚደርሳቸው ይሆናል፡፡
• መጠንን መሰረት ያደረገ አገልግሎት የሚጠቀሙ ደንበኞች ወርሃዊ ጥቅል ተጠቅመው ካልጨረሱ ቀሪው የጥቅል መጠን ወደ ቀጣይ ወር የሚተላለፍላቸው ይሆናል፡፡
• ደንበኞች የገዙትን ወርሃዊ ጥቅል ከቀረቡት አማራጮች ውስጥ ወደፈለጉት ማሳደግ ወይም እንዲቀነስላቸው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
• ለመመዝገብ፣ የተቋረጠውን ለማስቀጠል፣ የስም እና የባለቤትነት ለውጥ ለማድረግ እንዲሁም የቦታ ዝውውር አገልግሎቶች ከክፍያ ነፃ ናቸው፡፡
• አገልግሎቱ ለመኖሪያ ቤቶች ብቻ የሚያገለግል ሲሆን አገልግሎቱን የሚያስጠቅመው ሲም ካርድ ከአንድ ሞደም ጋር የተሳሰረ እንዲሁም አገልግሎቱ የሚያገኙበት ቦታ መጀመሪያ በተመዘገቡበት ብቻ እንዲሆን የተገደበ ነው፡፡
• ደንበኞች የመኖሪያ ቦታ ለውጥ አድርገው አገልግሎቱ እንዲዛወርላቸው ከፈለጉ ቀድመው መጠየቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
• በ12 ወራት የአከፋፈል ዘዴ አገልግሎቱን የገዙ ደንበኞች የኮንትራት ጊዜያቸው ሳይጨርሱ አገልግሎቱ እንዲቋረጥላቸው መጠየቅ አይችሉም፡፡ ነገር ግን ያለባቸውን ቀሪ የሞደም ክፍያ ሙሉውን በመክፈል አገልግሎቱን ማቋረጥ ይችላል፡፡