ስለ መጭበርበር ግንዛቤ

photo_2022-08-02_15-26-22

ማጭበርበር ምንድን ነው?

ሆን ተብሎ የሚፈፀም የማታለል ድርጊት ሲሆን አጭበርባሪው ህገ ወጥ ጥቅም እንዲያገኝ ወይም የተጎጂውን መብት ለመንፈግ የሚደረግ ተግባር ነው፡፡

photo_2022-08-02_15-27-05

በብዛት የሚፈፀሙ የማጭበርበር አይነቶች የትኞቹ ናቸው

ማህበራዊ ምህንድስና (Social engineering) ፡ በዚህ ዘዴ አጭበርባሪዎች ያልሆኑትን ማንነት በመላበስ (ተቋማትን ወይም ሌሎች ግለሰቦችን በመምሰል) ሚስጥራዊ ቀጣዩን ለማንበብ

photo_2022-08-03_16-38-06

የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመከላከል መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች ምንድን ናቸው?

  • ሲም ካርድዎ የይለፍ ቃል ስለመኖሩ ያረጋግጡ
  • ጠንካራ የይለፍ ቃል በመጠቀም እና የግል መረጃዎችን በቀላሉ እንዳይገኙ ማድረግ በተለይም ከማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አያስቀምጡ
  • የይለፍ ቃልዎን ወይም የሚስጥር ቁጥርዎን ለሌላ ሰው አለማጋራት
  • የግል መረጃዎን ለማንም ሰው አለማጋራት በተለይም የአንድ ጊዜ የይለፍ ቁጥርዎን፣ የማይ ኢትዮቴል ወይም ቴሌ ብር አካውንቶችዎን የመሳሰሉ
  • በስህተት ጥቅል ልከንለዎታል እባከዎት መልሰው ይላኩ ለሚሉ መልእክቶች ምላሻ አለመስጠት
  • ከማያውቁት ሰው ከቴሌብር አካውንትዎ ላይ ገንዘብ ወይም የአየር ሰዓት ያስተላልፉልኝ ጥያቄ ምላሽ አለመስጠት
photo_2022-08-02_15-26-56

የአጭበርባሪዎች ዒላማ የትኞቹ አገልግሎቶች ናቸው?

  • የቴሌብር አካውንት
  • የሞባይል ባንኪንግ ዋሌት
  • የቅድመ ክፍያ ክሬዲት
  • ዓለም አቀፍ እና ልዩ አጭር ቁጥር ጥሪ
  • የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶች
  • ማንነትን በመጥለፍ የሚሰልሉ
photo_2022-08-03_16-09-26

ማጭበርበርን እንዴት መጠቆም ይችላሉ

  • የማጭበርበሪያ መልዕክቶች ሲደርስዎ ወይም ሲጠራጠሩ 994 ወይም 127 ላይ በመደወል እንዲሁም ወደ 9090 አጭር መልዕክት በመላክ ማሳወቅ ይችላሉ፡፡
  • በተጨማሪም በሁሉም የኢትዮ ቴሌኮም የማህበራዊ ድረ-ገፆች አማካኝነት ጥቆማዎን ማድረስ ይችላሉ፡፡