ሞባይል ዳታ ጥቅል የሞባይል ኢንተርኔት ጥቅል በመጠቀም ይደሰቱበት!! ከቀረቡት የሞባይል ኢንተርኔት/የዳታ ጥቅል አማራጮች መካከል መርጠው በቅናሽ ዋጋ ገዝተው ይጠቀሙ! በማይ ኢትዮቴል፣ በቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ ወይም *999# ላይ በመደወል ለራስዎም ይግዙ፤ ለወዳጆችዎም በስጦታ ያበርክቱ ደንብና ሁኔታዎችሁሉም የግለሰብ ቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ደንበኞች ለአገልግሎቱ ብቁ ሲሆን እስከፈለጉ ድረስ ያለገደብ ደጋግመው ጥቅሉን መግዛት ይችላሉ፡፡የጥቅል አገልግሎቱ በኢትዮ ገበታ፣ ማይ ኢትዮቴል መተግበሪያ፣ በቴሌብር እና የአገልግሎት ማዕከላችንን በመጎብኘት ማግኘት ይችላሉ፡፡ በቴሌብር የሚገዙ ደንበኞች የጥቅሉን 10 በመቶ ጭማሪ ያገኛሉ፡፡ዋናው ጥቅል የአጠቃቀም እና የአገልግሎት ቀነ ገደብ የለውም፡፡ ነገር ግን በስጦታ የቀረበው ጥቅል ለ7 ቀናት ከሌሊቱ 5፡00 እስከ ጠዋት 2፡00 ድረስ መጠቀም ይኖርብዎታል፡፡ በስጦታ የቀረቡት ጥቅሎች ወደ ሌላ ጥቅል ቀይረው የሚጠቀሙ ከሆነም የሚጠቀሙበት ሰዓት እና የአገልግሎት ቀነ ገደቡ ለውጥ አይኖረውም፡፡ዋናውም ሆነ ነፃ የስጦታ ጥቅሎቹ ወደ ሌላ ደንበኛ ማስተላለፍ የማይችሉ ሲሆን ነገር ግን ወደ ሌላ የጥቅል አይነት ቀይረው ለራስዎ መጠቀም ይችላሉ፡፡ ሲቀይሩ የጥቅል አገልግሎቱ ከገዙበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ የ7 ቀናት የአገልግሎት ቀነ ገደብ ይኖረዋል፡፡ከጥቅል ውጪ ሲጠቀሙ በመደበኛ የመጠቀሚያ ዋጋ መሰረት ይሆናል፡፡ ዕለታዊ የዳታ ጥቅል የጥቅል መጠንዋጋ 100 ሜ.ባ 5 ብር 200 ሜ.ባ 10 ብር 300 ሜ.ባ 15 ብር 600 ሜ.ባ 25 ብር 1 ጊ.ባ 33 ብር 2 ጊ.ባ 65 ብር ማስታወሻ፡ የቀረበው ቦነስ የሚያገለግለው ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 2፡00 ሰዓት ድረስ ነው ሣምንታዊ የዳታ ጥቅል የጥቅል መጠንዋጋ 500 ሜ.ባ 40 ብር 1 ጊ.ባ 65 ብር 2 ጊ.ባ 100 ብር 4.5 ጊ.ባ 200 ብር 8 ጊ.ባ 300 ብር 15 ጊ.ባ 450 ብር ወርሃዊ የዳታ ጥቅል የጥቅል መጠንዋጋ1 ጊ.ባ 75 ብር 2 ጊ.ባ 140 ብር 4 ጊ.ባ 250 ብር 10 ጊ.ባ 500 ብር 20 ጊ.ባ 850 ብር 50 ጊ.ባ 1340 ብር 100 ጊ.ባ 1720 ብር ለአንድ ጊዜ ወይም በየወሩ በቋሚነት መግዛት ይችላሉ የሌሊት የዳታ ጥቅል የጥቅል መጠንዋጋ200 ሜ.ባ3 ብር500 ሜ.ባ5 ብር1 ጊ.ባ10 ብር ተጨማሪ ማብራሪያከአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ በፊት ጥቅሉ ካለቀብዎ 15 ሣንቲም በሜ.ባ መጠቀም ይችላሉ፡፡በቴሌብር ሲገዙ ተጨማሪ 20% የጥቅል መጠን ያገኛሉ!