
ወጪዎን የሚቆጣጠሩበት…ቀላል የአከፋፈል ዘዴ
ለድርጅትዎ በልዩነት የቀረቡ የሞባይል ጥቅሎችን ያግኙ!
ለድርጅቶች የቀረበው የሞባይል ጥቅል ለተጠቃሚዎች ምቹ፣ ቀላል፣ እና የተለያዩ አማራጭ ጥቅሎችን የያዘ አገልግሎት ነው፡፡ በተጨማሪም ድርጅቶች በተለያየ የአካውንት ቁጥር የሚጠቀሟቸውን አገልግሎቶች ወደ አንድ አካውንት በማድረግ ለክፍያ ምቹ እንዲሆንላቸው ማድረግ ይችላሉ፡፡
ይህንን ታሳቢ በማድረግ ያቀረብናቸው ሞባይል ጥቅሎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለአከፋፈል ምቹ በሆነ መልኩ ነው፡፡
የእኛን ሞባይል ጥቅሎች ምን ልዩ ያደርጋቸዋል ካሉ
የድርጅትዎ ሰራተኞችን የሞባይል አገልግሎት ፍላጎት የሚያሟሉ ለአጠቃቀም ቀላልና ምቹ የሞባይል ጥቅሎች መሆናቸው ነው፡፡ ቀላል ግን እጅግ ወሳኝ አገልግሎት ሲሆን የተበታተነውን የተለያየ የሞባይል አካውንት በአንድ በማድረግ የሰራተኞችዎን የሞባይል ጥቅል ፍላጎት አሟልተው ቢሉን ደግሞ ወጥ በሆነ የመክፈያ መንገድ መፈፀም ይችላሉ፡፡
ለድርጅትዎ የሚሰጠው ዋና ዋና ጥቅሞች:
- እጅግ ወጪ ቆጣቢ እና የቴሌኮም በጀትዎን ለመቆጣጠር ይረዳል፡ ከመደበኛ ዋጋ እጅግ በቅናሽ የቀረቡ የሞባይል ጥቅሎች ያገኙበታ እንዲሁም የቴሌኮም ወጪዎን ቀድመው እንዲያውቁ ይረዳል፡፡
- ለአስተዳደር ቀላል ነው: የተለያዩ የሞባይል መስመሮችን ክፍያ ለመፈፀም የተወሳሰበ አካሄድ ከሚጠቀሙ በቀላሉ በአንድ አካውንት በማምጣት ለማስተዳደር የሚፈጅቦትን ጊዜ ቆጥበው በቀላሉ ክፍያ ይፈፅማሉ፡፡
- የሰራተኞችዎን የቡድን መንፈስ ያጎለብታል፡ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ሰራተኞችዎ የስራ ላይ ግንኙነታቸውን እርስ በእርስ እንዲሁም ከንግድ አጋሮችዎ ጋር እንዲፈፅሙ ያግዛል፡፡
- ምርታማነትን ይጨምራል:የአስተዳደር ጊዜን ስለሚቆጠብ ይህንን የሚያስተዳድሩ ሰራተኞችዎ ትኩረት ወደ የሚፈልጉ ስራዎች ፊታቸው እንዲያዞሩ ያደርጋል እንዲሁም የሰራተኞችዎ የስራ ላይ ግንኙነት በእጅጉ ስለሚያሳድግ ውጤታማነታቸው ይጨምራል፡፡
- እንደፍላጎትዎ አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ:የሰራተኞችዎ ብዛት ሲጨምር የቴሌኮም ፍላጎትዎ እንደሚያድግ ግልፅ ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ተጨማሪ የሞባይል ጥቅሎችን እንደፈለጉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰራተኞችዎ ወጪ ቆጣቢ የሆነ እና ለአስተዳደር ቀላል የቴሌኮም አገልግሎት ከፈለጉ ለድርጅቶች በልዩነት የቀረቡ የሞባይል ጥቅሎቻችንን መጠቀም አይርሱ፡፡
ከዚህ በታች የቀረቡትን የሞባይል ጥቅሎቻችን ይመልከቱ!
ወርኃ ድምፅና የአጭር መልዕክት ጥቅሎች
ተ.ቁ | የአገልግሎቱ አይነት | ዋጋ በብር |
---|---|---|
1 | 100 ደቂቃ + 25 መልዕክት | 35 |
2 | 250 ደቂቃ + 50 መልዕክት | 68 |
3 | 600 ደቂቃ + 150 መልዕክት | 135 |
4 | 1000 ደቂቃ + 250 መልዕክት | 205 |
5 | 1500 ደቂቃ + 375 መልዕክት | 273 |
6 | 2000 ደቂቃ + 500 መልዕክት | 340 |
7 | 3000 ደቂቃ + 750 መልዕክት | 410 |
8 | 5000 ደቂቃ + 1250 መልዕክት | 680 |
9 | ያልተገደበ ድምፅ + መልዕክት | 979 |
ወርኃዊ ዳታ ጥቅል
ተ.ቁ | የአገልግሎቱ አይነት | ዋጋ በብር |
---|---|---|
1 | 500 ሜ.ባ | 40 |
2 | 1 ጊ.ባ | 60 |
3 | 2.5 ጊ.ባ | 140 |
4 | 5 ጊ.ባ | 250 |
5 | 10 ጊ.ባ | 455 |
6 | 15 ጊ.ባ | 589 |
7 | 20 ጊ.ባ | 660 |
8 | 30 ጊ.ባ | 780 |
9 | 50 ጊ.ባ | 960 |
10 | 100 ጊ.ባ + ያልተገደበ መልዕክት | 1229 |
11 | 150 ጊ.ባ + ያልተገደበ መልዕክት | 1250 |
12 | ያልተገደበ ዳታ + መልዕክት | 1300 |
ወርኃዊ ድምፅ እና ዳታ ጥቅል
ተ.ቁ | የአገልግሎቱ አይነት | ዋጋ በብር |
---|---|---|
1 | 1 ጊ.ባ + 200 ደቂቃ + 50 መልዕክት | 75 |
2 | 1 ጊ.ባ + 500 ደቂቃ + 150 መልዕክት | 135 |
3 | 5 ጊ.ባ + 600 ደቂቃ + 350 መልዕክት | 273 |
4 | 5 ጊ.ባ + 1500 ደቂቃ + 400 መልዕክት | 410 |
5 | 6 ጊ.ባ + 2000 ደቂቃ + 500 መልዕክት | 546 |
6 | 10 ጊ.ባ + 1000 ደቂቃ + 500 መልዕክት | 680 |
7 | 10 ጊ.ባ + 2000 ደቂቃ + 500 መልዕክት | 819 |
8 | 20 ጊ.ባ + 2000 ደቂቃ + 500 መልዕክት | 955 |
9 | 30 ጊ.ባ + 1500 ደቂቃ + 600 መልዕክት | 1090 |
10 | 50 ጊ.ባ + 3000 ደቂቃ + 750 መልዕክት | 1365 |
11 | 100 ጊ.ባ + 5000 ደቂቃ + 1250 መልዕክት | 1638 |
12 | ያልተገደበ ድምፅ + ዳታ + መልዕክት | 1699 |
የጅምላ መልዕክት ጥቅል
ተ.ቁ | የአገልግሎቱ አይነት | ዋጋ በሳንቲም በአንድ መልዕክት |
---|---|---|
1 | ከ10,000 በታች | 0.1366 |
2 | 10,001 እስከ 2,000,000 | 0.0185 |
3 | 2,000,001 እስከ ያልተገደበ | 0.0178 |
ደንብና ሁኔታዎችን ለማንበብ ይህንን ይጫኑ
ለድርጅቶች የቀረቡ የሞባይል ጥቅሎችን ከመጠየቅዎ በፊት ይህንን ደንብና ሁኔታ በጥንቃቄ ያንብቡ
ስለብቁነት:
- ይህ አገልግሎት ለቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ ወይም ሀይብሪድ የሆኑ የሞባይል አካውንቶች በሙሉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ጥቅሎቹ የቀረቡት ለ2ጂ፣ 3ጂ፣እና 4ጂ ኔትወርክ ተጠቃሚዎች ብቻ የቀረቡ ናቸው፡፡
የግዢ አማራጮች:
- የሞባይል ጥቅሎቹን ለመግዛት በአቅራቢያዎ የሚገኝ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ፡፡
- ጥቅሎቹን ለአንድ ጊዜ ብቻ ወይም በየወሩ በቋሚነት መግዛት ይችላሉ፡፡
የጥቅል ዓይነት:
- ጥቅሎቹን ለሰራተኞችዎ በቡድን ወይም ለተመረጠ አንድ ሰራተኛ ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
ስለአጠቃቀም ደንብና ሁኔታዎች:
- የቡድን ጥቅሎችን ስለማጋራት
- በድርጅት ስም የተገዛን የሞባይል ጥቅል ለሌላ ሶስተኛ ወገን ማጋራት አይቻልም፡፡
- ነገር ግን በድርጅቱ ስም ሳይሆን በግልዎ የገዙት የሞባይል ጥቅል ሞባይል ቁጥርዎ ላይ ካለ ግን ለእዛ ሞባይል በተፈቀደው ልዩ ደንብና ሁኔታ ለሌሎች ሊያጋሩት ይችላሉ፡፡
- ጥቅል ስለመቀየር
- የድምፅ እና መልዕክት ጥቅሎን በተመለከተ:በመደበኛው የሞባይል ጥቅል መቀየሪያ ህግ መሰረት መቀየር ይቻላል፡፡
- ዳታ ጥቅሎች(ከ500 ሜ.ባ እስከ 20 ጊ.ባ) ያሉት ወደ ሌላ ጥቅል መቀየር ይችላሉ፡፡
- ሌሎች ዳታ ጥቅሎች ማለትም 30 ጊ.ባ፣ 50 ጊ.ባ፣100 ጊ.ባ፣ 150 ጊ.ባ እና ያልተገደበ ጥቅሎች ወደ ሌላ ጥቅል ቀይረው መጠቀም አይችሉም፡፡
- የድምፅ እና የመልዕክት ጥቅሎችን በተመለከተ:እነዚህ ጥቅሎች ለመደወልም ሆነ መልዕክት መላላክ የሚፈቀደው ከተመሳሳይ የኢትዮ ቴሌኮም ኔትወርክ ቁጥር ብቻ ነው፡፡ ወደ ሌላ የአገር ውስጥ ኔትወርክ ለመደወል /መልዕክት ለመላላክ አያስችሉም፡፡
- ከጥቅል ውጪ ሲጠቀሙ:የቀረቡትን ጥቅሎች ከወር በፊተ ቀድመው ቢጨርሱ የአገልግሎት ቀኑ (Expiry date) እስኪደርስ ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ዝቅተኛ ዋጋዎች የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
- ዳታ:11 ሳንቲም በሜ.ባ
- ድምጽ: 50 ሳንቲም በደቂቃ
- መልዕክት: 12 ሳንቲም በመልክዕት
አጠቃላይ ህጎች
- ነባር የሞባይል ጥቅል ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚነት አላቸው፡፡
ዋጋ በተመለከተ
- ሁሉም ዋጋዎች 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እና 2% የኤክሳይስ ታክስ ያካተቱ ናቸው፡፡
አገልግሎቱን ለማግኘት
- የሞባይል ጥቅሎቹን ለመግዛት በአቅራቢያዎ የሚገኝ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችንን ይጎብኙ፡፡