ቪፒኤን አገልግሎት ቪፒኤን የግል እና የመንግስት ተቋማት ከተለያዩ ቅርንጫፎቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ ሲሆን ተቋማቱ የራሳቸውን የግል ኔትወርክ እንዲያደራጁ ያስችላቸዋል። አገልግሎቱ መረጃን ለማጋራት እንዲሁም በቅርንጫፎች ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓቶችን በመደበኛ ወይም በተንቀሻቃሽ አማራጮች መተግበር ያስችላል። አገልግሎቱ የሞባይል ኔትዎርክ ሽፋን ተደራሽ በሆነባቸው እና የዳታ አገልግሎትን በሚሰጡ በሁሉም ኢትዮጵያ ክፍሎች ይገኛል። የቪፒኤን አገልግሎቶችን በሁለት አማራጭ የምናቀርብ ሲሆን እነዚህም 1. የሞባይል ብሮድባንድ ቪፒኤን 2. የፊክስድ ብሮድባንድ ቪፒኤን ወርሃዊ የሞባይል ቪፒኤን ጥቅል አገልግሎቶች ወርሃዊ የሞባይል ቪፒኤን ጥቅል አገልግሎት ታሪፍ የጥቅል ዓይነት የድሮ ዋጋ ዋጋ 1 ጊ.ባ ብር 75 /td> ብር 60 2 ጊ.ባ ብር 130 ብር 105 4 ጊ.ባ ብር 250 ብር 200 6 ጊ.ባ አዲስ ብር 280 8 ጊ.ባ ብር 450 ብር 360 10 ጊ.ባ ብር 520 ብር 420 20 ጊ.ባ ብር 890 ብር 700 ያልተገደበ ዳታ ብር 1510 ብር 999 መደበኛ ብሮድባንድ ቪፒኤን መደበኛ ባለገመድ እና ገመድ አልባ የብሮድባንድ የቪፒኤን አገልግሎት በዋናነት በMPLS (Multi-Protocol Labeled Switch) በኩል የሚቀርብ ሲሆን ይህም በተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የአንድ ድርጅት ቅርንጫፎችን ፤ የመረጃ ማዕከልን እና ዋናውን መ/ቤት በማገናኘት ደህንነቱ የተጠበቀ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበ አገልግሎት ነው፡፡ ጥቅሞች ደህንነቱ የተጠበቀ የዳታ ወይም የመረጃ ፍሰት በተለያየ ቦታ የሚገኙ የአንድ ድርጅት ቅርንጫፎችን ከአንድ ቦታ ላይ ሆኖ ለመቆጣጠር ወይም ለማስተዳደር የሚያስችል ነው ለቢዝነስ ቀጣይነት ጠቀሜታው የጎላ ነው የዕለት ተዕለት ስራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመቀነስ ያገለግላል የመደበኛ ብሮድባንድ Local MPLS VPN ታሪፍ ፍጥነትወርሃዊ ኪራይ በብር64 ኪ.ቢ/ሰ2491 ሜ.ቢ/ሰ3992 ሜ.ቢ/ሰ4993 ሜ.ቢ/ሰ8995 ሜ.ቢ/ሰ1,4396 ሜ.ቢ/ሰ1,6897 ሜ.ቢ/ሰ1,9708 ሜ.ቢ/ሰ2,25010 ሜ.ቢ/ሰ2,75012 ሜ.ቢ/ሰ3,13016 ሜ.ቢ/ሰ4,17320 ሜ.ቢ/ሰ4,69927 ሜ.ቢ/ሰ5,76030 ሜ.ቢ/ሰ6,98040 ሜ.ቢ/ሰ9,10060 ሜ.ቢ/ሰ12,620100 ሜ.ቢ/ሰ19,990150 ሜ.ቢ/ሰ29,979200 ሜ.ቢ/ሰ39,950300 ሜ.ቢ/ሰ59,899500 ሜ.ቢ/ሰ99,799800 ሜ.ቢ/ሰ152,3751024 ሜ.ቢ/ሰ195,000 ተጨማሪ መረጃዎች ከ1ጊ.ባ በሴኮንድ በላይ ላለው የአገልግሎት ፍጥነት መጠን ዋጋው፡-Y= የ1 ጊ.ቢ በሴኮንድ ዋጋ + 200*(N-1024)Y የተፈለገው የአገልግት ፍጥነት ዋጋ ጊ.ቢ በሴኮንድ ከተጨማሪ እሴት ጋር ነውN የተጠየቀው የአገልግሎት ፍጥነት ነው፡፡200 በስሌቱ ውስጥ የማይለወጥ/ቋሚ ቁጥር ሲሆን የሜ.ቢ በሴኮንድ ታሪፍ ነው፡፡የተጠየቀው የአገልግሎት ፍጥነት መጠን ከላይ ባለው ቀመር መሰረት በሜ.ቢ በሴኮንድ የሚሰላ ይሆናል፡፡1024 በቀመሩ ውስጥ የማይለወጥ/ቋሚ ቁጥር ሲሆን 1 ጊ.ባ በሴኮንድ ወደ ሜ.ቢ በሴኮንድ ሲቀየር ነው፡፡የደንበኝነት ምዝገባ፣ በድጋሚ መስመር ለማገናኘት፣ የስም ለውጥ ለማድረግ፣ የባለቤትነት ለውጥ እንዲሁም የአድራሻ ለውጥ ከክፍያ ነፃ ናቸው፡፡ መደበኛ ገመድ አልባ ብሮድባንድ ቪፒኤን የፊክስድ ገመድ አልባ ብሮድባንድ ቪፒኤን ያለገመድ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ነገር ግን በተመረጡ ቦታዎች ብቻ የተገደበ አገልግሎት ነው፡፡ አገልግሎቱ በAironet ወይም VSAT አማራጮ ይሰጣል። ጥቅሞች የቢዝነስ ቀጣይነትን ለማረጋገጥ እንደ ተጨማሪ መጠባበቅያ የገመድ አልባ አማራጭ ያገለግላል የዕለት ተዕለት ስራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለመቀነስ ያገለግላል ባለገመድ ኔትወርክ በሌለበት አካባቢ ስራዎችን ለማከናወን ይረዳል አገልግሎትን በቀላሉ የማሳደግ አቅም ይፈጥራል – ደንበኞች አዳዲስ ቦታዎችን፣ ተጠቃሚዎችን እና መተግበሪያዎችን በፍጥነት ለማገኛኝት ይረዳቸዋል፡፡ በከፍተኛ ደረጃ የማዳረስ አቅም መኖር ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑ እና ደንበኞች አገልግሎቱን በሚፈልጉት መልኩ እንዲቆጣጠሩት ማስቻሉ፡፡ ደንበኞች አገልግሎቱን ለማስተዳደር የራሳቸውን የደህንነት ፓሊሲ በማዘጋጀት የትኞቹ ተጠቃሚዎች የትኛውን የኔትወርክ ክፍል መጠቀም እንዳለባቸው መከታተል እና መቆጣጠር ያስችላቸዋል፡፡ ቋሚ ገመድ አልባ MPLS -VPN በVSAT የፍጥነት አማራጭ (በሴኮንድ) የበፊቱ ወርሃዊ ታሪፍ አዲሱ ወርሃዊ ታሪፍ 512 ኪሎ ባይት 14,517.19 13,040 1 ሜ.ባ 27,465.21 14,735 2ሜ.ባ 53,361.25 20,629 4 ሜ.ባ አዲስ አገልግሎት 28,880 5 ሜ.ባ አዲስ አገልግሎት 31,768 የድሮው አዲሱ የምዝገባ ክፍያ 54,942.80 41,923 ተጨማሪ መረጃዎች ለVSAT ብሮድባንድ ድምጽ + ቪፒኤን አገልግሎት፣ የድምፅ ምዝገባ እና የኪራይ ክፍያ ከቪፒኤን የደንበኝነት ምዝገባ እና የኪራይ ክፍያ ላይ ተጨማሪ ያስከፍላል፡፡ የድምፅ አገልግሎት ብቻውን አይቀርብም፡፡ የድምጽ አገልግሎት ጥያቄ ለሚያቀርብ አንድ ደንበኛ ስድስት የድምፅ መስመሮች ይሰጡታል፡፡ የድምጽ ደንበኝነት ምዝገባ እና የአጠቃቀም ታሪፍ ከመደበኛ የስልክ አገልግሎት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህ ታሪፍ የወርሀዊ የአገልግሎት ክፍያን አያካትትም፡፡ ሁሉም ታሪፎች የተ.እ.ታን ያካትታሉ፡፡ የደንበኝነት ምዝገባ ክፍያ የቴምብር ቀረጥ ክፍያን ያካተተ ነው፡፡