- ሁሉም የቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እንዲሁም ሀይብሪድ ሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚዎች አሻምቴሌ ሎያሊቲ ፕሮግራም ለመጠቀም ብቁ ናቸው፡፡
- ፕሮግራሙ የሚተገበረው በአገልግሎት ቁጥር እንጂ በአካውንት ቁጥር አይደለም፡፡
- አሻምቴሌ ለመመዝገብ እና ለማስተዳደር ደንበኞች ማይ ኢትዮቴል የሞባይል መተግበሪያን መጠቀም እንዲሁም ወደ *999# መደወል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ደንበኞች የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያላለፈ ነጥቦችን የአሻምቴሌ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሆኑ ደንበኞች ያለምንም ገደብ መላክ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ነጥቦቹ አባል ላልሀነ ደንበኛ መላክ አይቻልም ፡፡
- አገልግሎት እንዳይሰጥ የታገደ ነጥብ ወደ ሌሎች ማስተላለፍ እና መጠቀም አይቻልም፡፡
- የሞባይል ቁጥሩ ላይ የባለቤትነት ለውጥ ከተደረገ ነጥቦቹም አብረው ይዛወራሉ፡፡
- አገልግሎት መስጠት ባቋረጠ የሞባይል ቁጥር የአሻምቴሌ ነጥቦችን መጠቀም አይቻልም፡፡
- የነጥቦች ከፍተኛው የአገልግሎት ዘመን 12 ወራት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ደንበኛ 10 ነጥቦች ሚያዚያ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ቢኖረው የነጥቦቹ የአገልግሎት ጊዜ ማብቂያ ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ይሆናል፡፡
- ከ1 ብር በታች ተጠቅመው ከሆነ በቀጣይ ከሚጠቀሙት አገልግሎት የብር መጠን ጋር ተደምሮ ነጥብ የሚያገኙ ይሆናል፡፡
- ኢትዮ ቴሌኮም በነፃ ወይም በስጦታ የሚያቀርባቸው አገልግሎቶች ነጥብ ለመሰብሰብ አያስችሉም፡፡
- 1 የአሻምቴሌ ነጥብ ከ 2 ሣንቲም ጋር እኩል ሲሆን ተ.እ.ታ ያካተተ ነው፡፡
- ደንበኞች አገልግሎቱን ሲያቋርጡ የሰበሰቡት ነጥብም ይቋረጣል፡፡
- አሻምቴሌ ከመጀመሩ እንዲሁም ደንበኛው ለአገልግሎቱ ከመመዝገባቸው በፊት የተጠራቀመን ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያ መክፈል ነጥቦችን አያስገኝም፡፡
ነጥብ የሚሰላበት እና ለአገልግሎት ቁጥሮች የሚደርሰው በሚከተሉት መመሪያዎች መሰረት ነው:
- ቅድመ ክፍያ ሞባይል:
- ለድምፅ፣ ለአጭር መልዕክት እና ዳታ 1 ብር ሲጠቀሙ = 1 ነጥብ
- በየ24 ሰዓታት ያገኙት ነጥብ መረጃ ይላክልዎታል፡፡
- የጥቅል ተጠቃሚዎች ያልተገደበ ጥቅልን ጨምሮ ነጥብ የሚሰላው ጥቅሉን በገዙበት የብር መጠን ይሆናል (1 ብር = 1 ነጥብ)
- ጥቅል በስጦታ ሲላክ ላኪው የጥቅሉን ዋጋ ከፋይ እስከሆነ ድረስ ነጥብ ይሰጠዋል፡፡
- የአየር ሰዓት ወደ ሌላ ሰው ሲተላለፍ ነጥብ የማይያዝ ሲሆን ነገር ግን ተቀባዩ ሲጠቀምበት ነጥብ ይሰበስባል፡፡
- አጭር/ልዩ ቁጥሮችን ሲጠቀሙ ነጥብ አያገኙም፡፡
- በቀን ቢያንስ የ2.5 ብር አገልግሎት መጠቀም ይጠበቃል፡፡
- ለድህረ ክፍያ ሞባይል፡
- ወርሃዊ ቢል ሲከፍሉ 1 ነጥብ በ1 ብር ያገኛሉ፡፡
- ነጥብ ሲሰላ ለአጭር/ልዩ ቁጥሮች የተጠቀሙትን አያካትትም
- ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎ ቢያንስ 75 ብር መሆን ይኖርበታል
- ወርሃዊ ሂሳቡን የሚከፍለው ሌላ ደንበኛ ከሆነ ነጥቦቹ ወደ ተጠቃሚው ይላካሉ፡፡
- የአየር ሰዓት በቴሌብር ሲሞሉ
- 1 ብር ሲሞሉ 2 ነጥብ ያገኛሉ
- በየ24 ሰዓታት ያገኙት ነጥብ መረጃ ይላክልዎታል፡፡
- ለሌሎች ደንበኞች አየር ሰዓት ከተሞላ ለገዢው/ከፋዩ ነጥብ ይላካል
- ለነጋዴዎች በቴሌብር ከከፈሉ
- ለነጋዴዎች በቴሌብር 10 ብር ሲከፍሉ 1 ነጥብ ይሰበስባሉ፡፡