እንደራስ (አነስተኛ ብድር)

የግለሰብ ደንበኞች በቴሌብር እንደሚያከናውኑት የግብይት መጠን እስከ ብር 15,000 ድረስ የአነስተኛ ብድር አገልግሎት

የብድር አይነትየመመለሻ ቀነ ገደብየአገልግሎት ክፍያየተፈቀደው የብድር መጠን ቅጣት
   ዝቅተኛ ከፍተኛ  
ቴሌብር እንደራስ10 ቀናት4%100 ብር4,000 ብር0.5% በቀን
 25 ቀናት9% 10,000 ብር 
 60 ቀናት21% 15, 000 ብር
 •  18 አመት እና ከዛ በላይ
 • አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲምካርድ
 • የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም ንቁ ተጠቃሚ መሆን
 • የኔትወርክ የቆይታ ጊዜ 3 ወር እና ከዛ በላይ
 • የቴሌብር ተጠቃሚ በመሆን ቢያንስ 3 ወር የቆየ
  በማጭበርበር ሪከርድ የተደረጉ ቁጥሮች አገልግሎቱን መጠቀም አይችሉም
 •  የፋይናንሻል አገልግሎት በኢ.ን.ባ የሚለውን ይምረጡ
 •  ከእንደራስ የብድር አማራጮች ውስጥ ይምረጡ
 • መበደር የፈለጉትን የገንዘብ መጠን ይፃፉ
 • መረጃው ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ እና የሚስጥር ቁጥር በማስገባት ይጨርሱ
 •  1ን በመጫን የፋይናንስ አገልግሎት የሚለውን ይጫኑ
 • 1ን በመጫን የክሬዲት አገልግሎት የሚለውን ይምረጡ
 • 2ን በመጫን እንደራስን ይምረጡ
  11ን በመጫን ብድር ይውሰዱ የሚለውን ይምረጡ
 •  ከእንደራስ የብድር አማራጮች ውስጥ ይምረጡ
 • መውሰድ የፈለጉትን የገንዘብ መጠኑን ያስገቡ
  የሚጥር ቁጥርዎን በማስገባት ይጨርሱ
ደንብና ግዴታዎችን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 አነስተኛ የክሬዲት /  እንደራስ አገልግሎትን ለማስጀመር እና ለመጠቀም ደንቦች እና ሁኔታዎች

 1. የውል ስምምነት
  • ይህ ስምምነት (ከዚህ በኋላ "ደንቦች እና ሁኔታዎች" የሚባል) አነስተኛ የክሬዲት/ቴሌብር እንደራስ አገልግሎትን በተመለከተ አጠቃላይ ደንብ እና ሁኔታዎች ያካትታል፡፡
  • እነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች እንዲሁም ከዚህ ጋር የተያያዙ ማሻሻያዎች እና ለውጦች የክሬድት ተጠቃሚ ደንበኛው ተነበው ተቀባይነት ሲያገኙ (ይስማሙ የሚለውን ምርጫ ሲጫኑ) ሥራ ላይ ይውላሉ፡፡
 2. ትርጓሜ

በዚህ የደንቦች እና ሁኔታዎች መረጃ ውስጥ የተዘረዘሩ ቃላት እና አባባሎች የሚከተለውን ትርጉሜ ይይዛሉ፡-

 • "የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ” ማለት ቁጥጥር የሚደረግበት የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር ለቴሌብር ደንበኞች ቴሌብር እንደራስ አገልግሎት ለመስጠት የተስማማ የፋይናንስ ተቋም ነው።
 • “ኢትዮ ቴሌኮም” ማለት ክፍያ ለመፈፀም ፈቃድ ያለው እና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ቴሌብር እንደራስ አገልግሎትን ለቴሌብር ደንበኞች ለመስጠት ስምምነት ያለው ነው፡፡
 • “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ” ማለት በአዋጅ ቁጥር 591/2008 መሠረት የተቋቋመ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ነው።
 • “ቴሌብር” ማለት የሞባይል ስልክ በመጠቀም ገንዘብ ለማስቀመጥ፣ ለመላክ፣ ለመቀበል፣ አነስተኛ ክሬዲት፣ አነስተኛ ኢንሹራንስ፣ ጡረታ እና አነስተኛ ቁጠባ ወዘተ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችል የኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት የንግድ ስም ነው።
 • “የቴሌብር አካውንት” ማለት በቴሌብር ሲስተም ውስጥ ያለዎትን ኢሌክትሮኒክ ገንዘብ መጠን የሚገልፅ ነው፡፡
 • "እንደራስ አገልግሎት" ማለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚሰጥየክሬዲት አገልግሎት ሲሆን ግለሰብ የቴሌብር ደንበኞች የቴሌብር ቻናልን በመጠቀም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ውሎች እና ሁኔታዎች መሠረት የክሬዲት አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

 

 • "የክሬዲት አገልግሎት" ማለት ለግለሰብ አነስተኛ መጠን ያለው ክሬዲት የሚያገኙበት የአገልግሎት አይነት ነው።
 • “የደመወዝ ክሬዲት አገልግሎት” ማለት ወርሃዊ ደመወዛቸውን በቴሌብር አገልግሎት ለሚከፈላቸው የግል እና የመንግስት ተቋማት ሰራተኞች ከታች በተቀመጡ ደንብ እና ሁኔታዎች መሰረት በኢትዮ ቴሌኮም የቴሌብር አገልግሎት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚቀርብ የክሬዲት አገልግሎት ነው፡፡
 • “የግለሰብ ደንበኛ” ማለት በስሙ በቴሌብር አካውንት ለቴሌብር እንደራስ አገልግሎት የተመዘገበ ደንበኛ ማለት ነው።
 • “ኢ-ገንዘብ” ማለት እኩል መጠን ያለው ጥሬ ገንዘብን የሚወክል ደንበኛው የሚመለከተው የቴሌብር የኤሌክትሮኒክስ የገንዘብ ዋጋ ነው።
 • “አንተ” ወይም “የአንተ” ማለት የግለሰብ ደንበኛ ማለት ሲሆን የግለሰቡን የግል ተወካዮች ያጠቃልላል።
 • “እኛ” እና “የእኛ” ማለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም ማለት ነው፡፡
 • "የማስተላለፊያ ክፍያዎች" ማለት አነስተኛ የብድር አገልግሎት በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍያዎች፣ ቅጣቶች እና ሌሎች ክፍያዎች ማለት ነው። የዝውውር ዋጋ በኢትዮቴሌኮም እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውሳኔ በማንኛውም ጊዜ ሊቀየር ይችላል።
 • “የአገልግሎት ክፍያ” ማለት የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን ለመጠቀም በደንበኞች የሚከፈል የክፍያ መጠን ነው።
 • "የቅጣት ክፍያ" ማለት ለክሬዲት የመጨረሻ መክፍያ ቀነ ገደቡ አልፎ ክፍያው ሲፈጸም የሚከፍል ተጨማሪ የክፍያ መጠን ነው፡፡
 • "የክፍያ ቀን ገደብ" ማለት የክሬዲት መመለሻ የጊዜ ገደብን የሚያሳይ ቀነ ገደብ ነው፡፡
 • "ቀነ ገደቡ ያለፈ" ማለት የክሬዲት መመለሻ ቀነ ገደቡ ያለፈ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
 • "የተበላሸ ብድር" ማለት ክሬዲት ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በ90 ቀናት ውስጥ ያልተከፈለ ክሬዲት ሲሆን በወቅቱ ባለመመለሱ እንደ ተበላሸ ብድር መሆኑን የሚያሳይ ጊዜ ነው፡፡
 • "ግለሰብ" የሚለው ቃል ሁለቱንም ወንድ እና ሴትን ያካትታል::

 

 

 1. ደንብ እና ሁኔታዎችን ስለመቀበል
  • እንደራስ አገልግሎትን ለመጠቀም ከማመልከትዎ በፊት እነዚህን ደንብ እና ሁኔታዎች በጥንቃቄ በማንበብ የክሬዲት አጠቃቀም እና መመሪያን አንብበው ይስማሙ፡፡
  • በእነዚህ ደንቦችና ሁኔታዎች ካልተስማሙ እባክዎን ከዝርዝር መምረጫ ውስጥ ሰርዝ የሚለውን ይጫኑ፤
  • ደንቦችና ሁኔታዎችን እንዳነበቡ፣ እንደተረዱና እንደተቀበሉ የሚቆጠረው፡-
 • “ይስማሙ” የሚለውን አማራጭ ሲጫኑ ደንብ እና ሁኔታዎችን በማንበብ ተረድተው ለማክበር መስማማትዎን እንዳረጋግጡ ወይም ክሬዲት አገልግሎትን ለመጠቀም እንደተስማሙ ይወሰዳል
  • የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ለመተግበር እና የክሬዲት ክፍያ አገልግሎትን በኤሌክትሮኒካዊ መንገድ በቴሌብር ሲስተም ለመጠቀም ተስማምተዋል።
  • ደንብ እና ሁኔታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሊሻሻሉ ወይም ሊለወጡ የሚችሉ ሲሆን በቴሌብር ፖርታል፣በቴሌብር መተግበሪያ ወይም ድህረ ገጽ ላይ ከተለቀቁበት ዕለት ጀምሮ በደንበኛው ላይ ተግባራው ይደረጋሉ፡፡
  • ውሉ በኤሌክትሮኒክስ መንገድ ተቀባይነት ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ፣ እነዚህ ውሎች እና ሁኔታዎች በእርስዎ እና በእኛ መካከል በህጋዊ መንገድ አስገዳጅ ስምምነት ይሆናሉ። በዚህ ስምምነት ስር ያለዎትን ማንኛውንም መብት ወይም ግዴታ ለሌላ ለማንም ማስተላለፍ አይፈቀድልዎትም።
  • ደንበኛው ገንዘቡን ለህጋዊ አላማ ለማዋል ተስምቷል ።
 1. የክሬዲት አገልግሎትን ለማስጀመር
 • እንደራስ የክሬዲት አገልግሎትን ከኢትዮ ቴሌኮም እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ለማስጀመር ቢያንስ፡
 • 18 አመት እና ከዚያ በላይ

 

 • አገልግሎት የሚሰጥ የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርድ መያዝ
 • የቴሌብር እና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን እንደ ዳታ/ድምጽ/አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚጠቀሙ
 • የቴሌብር እና የቴሌኮም የደንበኝነት ቆይታ 3 ወር እና ከዛ በላይ መሆን አለበት
 • አገልግሎቱን ለማግኘት በዩኤስኤስዲ (*127#) ወይም በቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያ መጠቀም ይችላሉ፡፡
 • ለተሳካ ምዝገባ የማሳወቂያ አጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል፡፡
 1. የእንደራስ ክሬዲት አገልግሎት ለማግኘት መሰረታዊ መስፈርቶች
  • የደንበኛ የመበደር አቅም ደንበኛው የክሬዲት ክፍያ አገልግሎት ለመጠቀም ጥያቄ ካቀረበበት ቀን በፊት ባደረገው የ6 ወር የቴሌብር የገንዘብ እንቅስቃሴ እና በቴሌኮም አጠቃቀም ይወሰናል። ከታች ያሉት የቴሌብር ግብይቶች እና የገንዘብ ልውውጥ የደንበኛ የብደር አቅምን ለማስላት ይውላሉ።
  • ለእርስዎ ወይም ለስጦታ የአየር ሰዓት መሙላት ወይም ጥቅል መግዛት (በራስ አገዝ ወይመ ከወኪሎች)
  • ዕቃ ወይም አገልግሎት በመግዛት ግብይት መፈጸም
  • ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ ቢል ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)
  • ለእርስዎ ወይም የሌላ ደንበኛ የፍጆታ አገልግሎት ክፍያ (በራስ አገዝ ወይም ከወኪሎች)
  • ከውጭ አገር ገንዘብ መቀበል
  • የጅምላ ክፍያ (ደሞዝ፣ ሴፍቲኔት…)
  • የትኬት ክፍያ
  • ለገንዘብ ማሰባሰቢያ የእርዳታ ክፍያ
  • የቁጠባ አገልግሎት
  • ገንዘብ መላክ
  • የቴሌኮም ፍጆታ (ድምጽ፣ ዳታ ወይም መልዕክት) ወ.ዘ.ተ.
  • የደመዝ ክሬዲት ለማግኘት ወርሃዊ ደሞዝን በቴሌብር አማካኝነት መቀበል በቂ ነው፡፡
 2. የክሬዲት መጠን እና ክፍያ
  • በሚፈቀደው ዝቅተኛ እና ከፍተኛ የክሬዲት መጠን መካከል ማንኛውንም መጠን መበደር ይችላሉ።
  • የጠየቁትን የብድር መጠን እንዳገኙ በዋናው የቴሌብር ሂሳብዎ (ኤሌክትሮኒክ-ገንዘብ አካውንት) ላይ ገቢ ይደረጋል።
  • ሌላ ክሬዲት ለማግኘት መጀመሪያ ቀድመው የወሰዱትን ክሬዲት መክፈል ይጠበቅብዎታል፡
  • ያለብዎትን ክሬዲት በከፊል ወይም በሙሉ መክፈል ይችላሉ።

 

 • ለሁሉም ያለብዎን ክሬዲት በቀነ ገደቡ ውስጥ የማይከፍሉ ከሆነ ባለበዎት ክሬዲት መጠን ላይ በየዕለቱ የሚሰላ5% የቅጣት ክፍያ ይከፍላሉ፡፡
 • የክሬዲት መክፈያ ማብቂያ ቀነ ገደብ ብድሩን ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር እንደ ብድር አይነቱ 10 ቀን፣25ቀን እና 60 ቀናት ውስጥ ይሆናል።
 • የ10 ቀን ብድር የብድር ገደብ 4,000 ብር ፣ የ25 ቀን ብድር የብድር ገደብ 10,000 ብር እና የ60 ቀን ብድር የብድር ገደብ 15,000 ብር ፡፡
 • ያለብዎትን የአስር ቀን ክሬዲት በ10 ቀናት ውስጥ ከከፈሉ 1.25% የአገልግሎት ክፍያ እና ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን ከ 0.50% እስከ 0.80% ክፍያ ይከፍላሉ ፡፡
 • ያለብዎትን የሀያ አምስት ቀን ክሬዲት በ25 ቀናት ውስጥ ከከፈሉ 2.50% የአገልግሎት ክፍያ እና ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን ከ 0.50% እስከ 0.80% ክፍያ ይከፍላሉ ፡፡
 • ያለብዎትን የስልሳ ቀን ክሬዲት በ60 ቀናት ውስጥ ከከፈሉ 6.50% የአገልግሎት ክፍያ እና ከሁለተኛው ቀን ጀምሮ የክሬዲት መጠነዎን መሰረት ያደረገ በቀን ከ 0.50% እስከ 0.80% ክፍያ ይከፍላሉ ፡፡ ክፍያው በየወሩ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
 • የአንድ ወር ደመዝ ብድር ለሶስት ወር ተሰልቶ የተቀመጠው የክሬዲት መጠን በትክክል በሶስት ወር ከተከፈለ አስር በመቶ የአገልግሎት ክፍያ ይጠየቃል፡፡
 • የአንድ ወር ደመዝ ብድር ለአራት ወር ተሰልቶ የተቀመጠው የክሬዲት መጠን በትክክል በአራት ወር ከተከፈለ አስራ አራት በመቶ የአገልግሎት ክፍያ ይጠየቃል፡፡
 • የደመዝ ግማሽ ብድር ለሁለት ወር ተሰልቶ የተቀመጠው የክሬዲት መጠን በትክክል በሁለት ወር ከተከፈለ ስምንት በመቶ የአገልግሎት ክፍያ ይጠየቃል፡፡
 • የደመዝ አንድ አራተኛ ለአንድ ወር ተሰልቶ የተቀመጠው የክሬዲት መጠን በትክክል በአንድ ወር ከተከፈለ አራት በመቶ የአገልግሎት ክፍያ ይጠየቃል፡፡
 • ከብድሩ ቀነ ገደብ በኋላ ያልተመለሰ ክሬዲት መጠን ከቴሌብር ሂሳብ ወዲያውኑ ተቀናሽ ይደረጋል፡
 • በጉርሻ የሚያገኙት ገንዘብ ለክሬዲት ክፍያ አይውልም፡፡
 • ይህ የክሬዲት አገልግሎት የሚሰጠው ኢትዮ ቴሌኮም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ነው፡፡ ለክሬዲት አገልግሎት የሚውለውን ገንዘብ የሚያቀርበው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን ይህን ገንዘብ በባለቤትነት የሚቆጣጠረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው፡፡ የተበላሸ ወይም ቀነ ገደቡ ያለፈ ብድር በሚከሰትበት ጊዜ ባንኩ ጉዳዩን ወደ መደበኛ ፍርድቤት የመውሰድና የመክሰስ ሙሉ መብት አለው፡፡
 • ያለብዎትን እዳ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቀማጭ ሂሳብዎ ላይ መቁረጥን ጨምሮ በፍርድቤት እና ከፍርድ ቤት ውጭ ያሉ አማራጮች የመጠቀም መብት አለው፡፡

 

 1. የአስተዳደር ህግ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕጎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያዎች፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የኢትዮ ቴሌኮም አግባብነት ያላቸው አሠራሮች እነዚህን ውሎችና ሁኔታዎች ይቆጣጠራሉ።

 1. መጠይቆች (መረጃ)

ከቴሌብር እንደራስ አገልግሎት ሂደት፣ ውሎች እና ሁኔታዎች ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በቴሌብር የደንበኞች ግንኙነት ማእከል (127 በመደወል) ተጨማሪ መረማግኘት ይችላሉ።

 1. የውል መቋረጥ

ማንኛውንም የአነስተኛ ቁጠባ እና ብድር አገልግሎቶችን ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ ወይም ያለ ማስታወቂያ በእርስዎ አላግባብ መጠቀም ወይም ማጭበርበር ምክንያት ይህን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ለማገድ ወይም ለማቋረጥ መብት ይኖረናል። የዚህ ውል መቋረጥ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች መብቶችን እና ግዴታዎችን ሊነካ አይችልም።

 1. ቅሬታዎች

ቅሬታዎች በአካል፣ በጽሁፍ፣ በፖስታ፣ በፋክስ፣ በኢሜል ወይም በስልክ ሊቀርቡ ይችላሉ። ኢትዮ ቴሌኮም ቅሬታዎትን በተገቢው ጊዜ ለመፍታት ሁሉንም እርምጃዎች ይወስዳል። በመልሱ ካልተደሰቱ ጉዳዩን ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅደም ተከተል ማድረስ ይችላሉ።

 1. የክርክር መፍትሄ

ከዚህ ውል ጋር በተያያዘ የሚነሳ ማንኛውም አለመግባባት ከላይ በአንቀጽ 9 መሠረት ያልተፈታ አለመግባባት ሥልጣን ላለው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፍርድ ቤት መቅረብ ይችላል።

 1. በአደራ የተቀመጠ ንብርት

ዕዳ ካለብዎት በባንኩ ውስጥ እና በእጅዎት  ላይ ባሉ ንብረቶችዎ፣ ጥሬ ገንዘብ፣ እቃዎች፣ ዋስትናዎች፣ ውድ ጌጦች፣ ቼኮች ወዘተ ላይ አጠቃላይ ዋስትና ይኖረናል። ሌላ ተንቀሳቃሽ ወይም የማይንቀሳቀስ ንብረት የመልቀቂያ መብት በሚሰጥበት ሁኔታ ውስጥ ዕዳ ካለብዎ  የተያዘው ንብረት በሙሉ ለዕዳው መያዣ ተደርጎ ይቆጠራል።

 

 1. ዕዳ ክፈያ

የወሰዱትን ክሬዲት መጠን እንዲከፍሉ ካሳዎቅን በኋላ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ ውስጥ መመለስ ካልቻሉ ባንክ ውስጥ ካሉዎት ሌሎች የባንክ ተቀማጭ ጥሬ ገንዘብ፣ እቃዎች፣ ዋስትናዎች፣ ውድ ጌጦች፣ ቼኮች ላይ ያለበዎትን ክሬዲት መጠን ያህል ለመውሰድ ባንኩ ይገደዳል፡፡

 1. ማስተባበያ

የቴሌብር ሚስጥር ቁጥር (ፒን) በሚስጥር መቀመጥ አለበት፡፡ ከዕርስዎ ሌላ ለማንም ተደራሽ መሆን የለበትም። ከሚስጥር ቁጥር አጠቃቀም፣የሚስጥር ቁጥርን በየጊዜው አለመቀየር፣ ያልተፈቀደ የቴሌብር አካውንት መጠቀም፣ የሞባይል ስልክ ወይም ሲም ካርድ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ለሚከሰት ኪሳራ ወይም ስርቆት የእርስዎ ሃላፊነት ብቻ ይሆናል።