የልደት ጥቅል

የልደት ጥቅል የውድ ደንበኞቻችንን የልደት ቀን ምክንያት በማድረግ የመልካም ምኞት መግለጫ ከነፃ ጥቅል ስጦታ ጋር የምናበረክት ሲሆን፤በተጨማሪም የልደት ቀኑን ለሚያከብር ደንበኛችን፤ ከመደበኛ ጥቅል ላይ 20% ቅናሽ የተደረገባቸውን የልደት ጥቅል አገልግሎቶች አቅርበናል፡፡ እንዲሁም ሌሎች ደንበኞችም፤ ልደታቸውን ለሚያከብሩ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በልደታቸው ቀን የጥቅል ስጦታ ከመልካም ምኞት መግለጫ ጋር መላክ ማበርከት ከፈለጉ ስጦታ የልደት ጥቅል በአማራጭነት ቀርቧል፡፡

 

ነፃ የልደት ጥቅል

የጥቅል ዓይነት

ዋጋ

የአገልግሎት ቆይታ ጊዜ

1 ጊ.ባ + 20 ደቂቃ + 20 የፅሁፍ መልዕክት

ነፃ

24 ሰዓት

 

 • ነፃ የልደት ጥቅሉ ለ 4ጂ ደንበኞች በልደታቸው ቀን የሚደርሳቸው ይሆናል።
 • አገልግሎቱ በየአመቱ 1 ጊዜ ለደንበኞች ይቀርባል፡፡
 • ነፃ የልደት ጥቅሉ የሚላከው ደንበኞች ባስመዘገቡት የልደት ቀን መሰረት ነው።
 • ደንበኞች የልደት ቀን መረጃቸው ያልተሟላ ከሆነ እንዲያስሞሉ በፅሁፍ መልዕክት ይጠየቃሉ።

የልደት ጥቅል በ20 % ቅናሽ

ብር.20
 • 133 ደቂቃ.
 • 25 መልዕክት
 • 133 ነጻ የለሊት ጥቅል

የልደት ጥቅል በ20 % ቅናሽ

ብር.40
 • 1 ጊ ባ

ማስታወሻ

 • ሳምንታዊ ጥቅሎቹ ከመደበኛው የጥቅል ዋጋ ላይ 20% ቅናሽ የተደረገባቸው ናቸው፡፡
 • ለአገልግሎቱ ለመመዝገብ በአመት አንድ ጊዜ ለ3 ተከታታይ ቀናት ብቻ የቀረበ ነው።

የልደት ስጦታ ጥቅል

የጥቅል አይነት

የጥቅል መጠን

ዋጋ

የአገልግሎት ጊዜ

ዕለታዊ ድምፅ + ዳታ

12 ደቂቃ + 160 ሜ.ባ + 10 የፅሁፍ መልዕክት

12 ብር

24 ሰዓት

ሣምንታዊ ድምፅ + ዳታ

70 ደቂቃ  + 590 ሜ.ባ + 20 የፅሁፍ መልዕክት

50 ብር

7 ቀናት

ወርሃዊ ድምፅ + ዳታ

125 ደቂቃ  + 2 ጊ.ባ + 50 የፅሁፍ መልዕክት

140 ብር

30 ቀናት

 

ወዳጆችዎን በደስታቸው ቀን ልዩ የልደት ስጦታ ጥቅል ይላኩ እኛም ከመልካም ምኞት መግለጫ ጋር እናደርስልዎታለን፡፡

በቴሌብር ሲገዙ ተጨማሪ 10% ቅናሽ ያገኛሉ፡፡

 • ሁሉም የ4ጂ ቅድመ ክፍያ፣ ድህረ ክፍያ እና ሀይብሪድ ሞባይል ቁጥሮች የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ 2ጂ እና 3ጂ ደንበኞች የልደት ነፃ ጥቅል ተጠቃሚ መሆን አይችሉም፡፡
 • ነፃ የልደት ጥቅል ስጦታ (1 ጊ.ባ ኢንተርኔት, 20 ደቂቃ and 20 አጭር መልዕክት) ለደንበኞች በልደታቸው ቀን የሚደርሳቸው ሲሆን በየአመቱ አንድ ጊዜ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
 • አገልግሎቱን ለማግኘት የደንበኞች የልደት ቀን በትክክል ሲስተም ላይ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡ መረጃው ያልተሟላ ከሆነ ደንበኞች በሚደርሳቸው የማሳወቂያ መልዕክት መሰረት ቅርባቸው ያለ የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ማዕከል መታወቂያቸውን በመያዝ በማስመዝገብ ለአገልግሎቱ ብቁ መሆን ይችላሉ፡፡
 • ደንበኞች የልደት ቀን መረጃቸውን አሳማኝ እና እውነተኛ መረጃ ካላቀረቡ በስተቀር በህይወት ዘመናቸው ማስሞላት የሚችሉት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
 • ሁሉም ነፃ የጥቅል ሀብቶች ወደ ሌላ አገልግሎት መቀየር ይችላሉ ነገር ግን ወደ ሌላ ደንበኛ ማስተላለፍ አይችሉም፡፡ ያልተገደበ ጥቅል ተጠቃሚ የሆኑ ደንበኞች ግን የሚበረከትላቸውን ነፃ የልደት ጥቅል ወደ ሌላ ደንበኛ እንዲያስተላልፉ ይፈቀድላቸዋል፡፡
 • አንድ ደንበኛ የተለያየ የአገልግሎት ቁጥር በተለያየ የልደት ቀን የተመዘገበ ከሆነ ነፃ የልደት ጥቅል አገልግሎቱ በሁሉም ቁጥሮች ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
 • ደንበኞች የተበረከተላቸውን ነፃ የልደት ጥቅል ስጦታ ተጠቅመው እንደጨረሱ ከመደበኛው ጥቅል የ20 በመቶኛ ቅናሽ የተደረገበትን ሣምንታዊ ጥቅል ከልደታቸው ቀን ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት መግዛት እንደሚችሉ የማሳወቂያ መልዕክት ሲደርሳቸው መግዛት ይችላሉ፡፡
 • ቅናሽ የተደረገባቸውን የልደት ጥቅሎች ብቁ ያልሆኑ ደንበኞች ለመግዛት ከሞከሩ ለአገልግሎቱ ብቁ ላለመሆናቸው ማሳወቂያ መልዕክት የሚደርሳቸው ይሆናል፡፡
 • ቅናሽ የተደረገበት የልደት ጥቅል ሲገዙ የጥቅል ሀብቱ ወደ ሌላ አገልግሎት መቀየር እንዲሁም ወደ ሌላ ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡
 • ሁሉም ደንበኞች ማለትም ልደታቸውን የሚያከብሩ እንዲሁም የማያከብሩ የልደት ስጦታ ጥቅልን መግዛት እና በስጦታ ማበርከት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ጥቅሉን ሲገዙ የመልካም ልደት መግለጫ የፅሁፍ መልዕክት አብሮ የሚደርሳቸው ይሆናል፡፡
 • ቅናሽ የተደገበት እና የልደት ስጦታ ጥቅል በሁሉም አማራጮች ማለትም በኢትዮ ገበታ፣ በማይ ኢትዮቴል መተግበሪያ፣ በቴሌብር እና በድምፅ ራስ አገዝ አማራጮች ላይ ቀርቧል፡፡
 • ነባር የጥቅል ደንብና ሁኔታዎች ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡