ረጅም የቆይታ ጊዜ የሞባይል ጥቅል

ለሩብ ዓመት ወይም ዓመታዊ የሞባይል ጥቅል ይመዝገቡ! አገልግሎታችንን በቅናሽ ይጠቀሙ!

የሩብ ዓመት ጥቅል

ብር820
  • 800 ደቂቃ + 36 ጊ.ባ ዳታ + 300 መልዕክት

የሩብ ዓመት ያልተገደበ ጥቅል

ብር4375
  • ያልተገደበ ድምፅ + 231 ጊ.ባ ዳታ + 300 መልዕክት

የሩብ ዓመት ጥቅል

ብር1085
  • 2000 ደቂቃ + 36 ጊ.ባ ዳታ + 300 መልዕክት

የሩብ ዓመት ያልተገደበ ጥቅል

ብር4915
  • ያልተገደበ ድምፅ + ዳታ + መልዕክት

የሩብ ዓመት ያልተገደበ ጥቅል

ብር3300
  • 800 ደቂቃ + ያልተገደበ ዳታ + 300 መልዕክት

ዓመታዊ ያልተገደበ ጥቅል

ብር9600
  • ያልተገደበ ድምፅ + ያልተገደበ መልዕክት

ዓመታዊ ያልተገደበ ጥቅል

ብር9999
  • ያልተገደበ ዳታ + ያልተገደበ መልዕክት

ዓመታዊ ያልተገደበ ጥቅል

ብር14500
  • ያልተገደበ ድምፅ + ዳታ + መልዕክት

  • ሁሉም የቅድመ ክፍያ ሞባይል፣ የድህረ ክፍያ ሞባይል እና የሀይብሪድ ሞባይል አገልግሎት ደንበኞች የረጅም የቆይታ ጊዜ ሞባይል ጥቅል በማንኛውም ሰዓት መመዝገብና አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • ለረጅም የቆይታ ጊዜ ጥቅል ሲመዘገቡ የመረጡትን ጥቅል ዋጋ አንድ ጊዜ ብቻ የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
  • ለሩብ ዓመት ወይም ለ 90 ተከታታይ ቀናት ፕላን በሽያጭ ማዕከላችን ለሚመዘገቡ ደንበኞች ሁለት ዓይነት የጥቅል መልቀቂያ አማራጮች ያሉ ሲሆን
    • ሁሉም የጥቅል አገልግሎቶቹ በአንድ ጊዜ እስከ አገልግሎት ማብቂያ ድረስ የሚለቀቁ ሲሆን ሌላኛው ደሞ
    • የተጠቀሱትን የጥቅል አገልግሎቶች የአገልግሎት ቀነ ገደቡ እስኪያልቅ ድረስ በየወሩ ከፋፍሎ የሚቀርብ ሲሆን ያልተጠቀሙት ቀሪ ጥቅል ካለ ወደ ቀጣይ ወር የሚተላለፍ ይሆናል፡፡
  • የቅድመ ክፍያ ሞባይል ተጠቃሚዎች በአጭር ቁጥር *999#፣ በማይ ኢትዮቴል መተግበሪያ እና የሽያጭ ማዕከላችን በመቅረብ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የድህረ ክፍያ ሞባይል ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን በሽያጭ ማዕከሎቻችን በአካል በመቅረብ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • የግለሰብም ሆነ የድርጅት ደንበኞች የረጅም የቆይታ ጊዜ ሞባይል ጥቅል አገልግሎት መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  • ደንበኞች የረጅም ጊዜ ጥቅልን ለራሳቸው መግዛት ወይም ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በስጦታ መላክ ይችላሉ
  • አንዴ ለረጅም የቆይታ ጊዜ ጥቅል ከተመዘገቡ ተመላሽ ሂሳብ መጠየቅ ወይም ወደ ሌላ የረጅም የቆይታ ጊዜ ጥቅል አማራጭ መቀየር አይፈቀድም፡፡
  • ለረጅም የቆይታ ጊዜ የሞባይል ጥቅል ለመመዝገብ እየተጠቀሙበት ያለው ሲም ካርድ የሚሠራ መሆን አለበት፡፡
  • የሞባይል ድምጽ እና የአጭር ጽሁፍ ጥቅሉ ለሀገር ውስጥ የጥሪና መልዕክት አገልግሎት ብቻ የሚውል ይሆናል፡፡
  • ከገዙት ጥቅል ውጭ እንዲሁም አጭር ቁጥር ሲጠቀሙ መደበኛው የአገልገሎት ታሪፍ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
  • ሁሉም ዋጋዎች የተጫማሪ እሴት ታክስን ያካትታሉ፡፡

ረጅም የቆይታ ጊዜ ጥቅል ተጠቃሚዎች የተዘጋጀ፤ ነጻ የመሸጋገሪያ ጥቅል አገልግሎት

ደንበኞች፤ ያለ ማቋረጥ እንደ ተገናኙ እንዲቆዩ፤ በተለየ ያልተገደበ ረጅም ጊዜ የሚቆዩ ጥቅሎችን የሚጠቀሙ ደንበኞችን ታስቦ የተዘጋጀው አዲሱ ነጻ የጥቅል መሸጋገሪያ አገልግሎት ይጠቀሙ!

 የረጅም ጊዜ ጥቅልዎ ልክ እንደ ተጠናቀቀ፤ ቀደም ብለው በገዙት ጥቅል መሠረት በስጦታ መልክ ወዲያውኑ የሚያገኙት የመሸጋገሪያ ጥቅልዎን በነጻ ለሦስት ቀናት በመጠቀም እንደ ተገናኙ ይቀጥሉ።

የቆይታ ጊዜየጥቅል ዐይነት ነጻ የጥቅል መሸጋገሪያየቆይታ ጊዜ
የሩብ ዓመት ጥቅል800 ደቂቃ + 36 ጊ.ባ ዳታ + 300 መልእክት
2000 ደቂቃ + 36 ጊ.ባ ዳታ + 300 መልዕክት
አይተገበርም-
የሩብ ዓመት ጥቅል800 ደቂቃ + ያልተገደበ ዳታ + 300 መልእክት
ያልተገደበ ድምፅ + 231 ጊ.ባ ዳታ + 300 መልእክት
ያልተገደበ ድምፅ + ዳታ + መልእክት
1 ጊ.ባ + 30 ደቂቃ3 ቀናት
ዓመታዊ ያልተገደበ ጥቅልያልተገደበ ድምፅ + መልእክት
ያልተገደበ ድምፅ + መልእክት
ያልተገደበ ድምፅ + ዳታ + መልእክት
2 ጊ.ባ
30 ደቂቃ
2 ጊ.ባ + 30 ደቂቃ
3 ቀናት

ማስታወሻ፡

  • የሩብ ዓመትና ዓመታዊ ያልተገደበ ጥቅል የተጠቃሚ ደንበኞች፤ የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜያቸው አንድ ቀን ብቻ ሲቀረው የነጻ ጥቅል መሸጋገሪያ ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል። በመሆኑ ጥቅሉ ለ3 ቀናት ብቻ የሚያገለግል ሲሆን፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ቀጣይ ለመግዛት የሚፈልጉትን የጥቅል እቅድ ለመወሰን በቂ ጊዜ እንዲያገኙ ያስችላል።
  • ነጻ ጥቅሎቹ፤ እየተጠቀሙት ያለው የረጅም ጊዜ ጥቅልዎ እንዳለቀ ወዲያው የሚለቀቁ ሲሆኑ፤ በዚህም ያለምንም እንከን ግንኙነትዎ እንዳይቋረጥ ይረዳዎታል።
  • ይህ ነጻ የመሸጋገሪያ ጥቅል ለግልዎ ብቻ የተዘጋጀ በመሆኑ፤ ወደ ሌሎች ደንበኞች ማስተላለፍም ሆነ ጥቅሉን መቀየር አይቻልም።
  • ነጻ የመሸጋገሪያ ጥቅሎችን ከ1% እስከ 100%  ሲጠቀሙ የማሳወቂያ መልእክት ይደርስዎታል።
  • ቀደም ብለው የነበሩት ሌሎች የሞባይል ጥቅል ደንብና ሁኔታዎች ባሉበትን ያቆያሉ።