1. ክላውድን መሠረት ያደረጉ የጥሪ ማእከላት አገልግሎቶች የሚሽጡት በቅድም ክፍያ ነው።
2. ለአንድ ጊዜ ማስጀመሪያ (Setup Fee)፣ ለሃርድዌርና ሶፍትዌር እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች ቢያንስ ለ12 ወራት (ለአንድ ዓመት) የፈቃድ ክፍያዎችን መክፈል አላባቸው።
3. ደንበኛው በስምምነቱ መሠረት ክፍያውን ካልፈጸመ ፈቃዱ ይታገድብታል/ይቋረጣል።
4. ለድርጅት ደንበኞች የሚሸጡት ዝቅተኛ የፈቃዶች ቁጥር ገደብ የላቸውም፤ ሆኖም ደንበኞች ቢያንስ ሁለትና ከዚያ በላይ ፈቃዶችን ማለትም አንድ ወኪልና አንድ ተቆጣጣሪ (ሱፐርቫይዘር) እንዲግዙ ይመክራል።
5. ደንበኛው ዝቅተኛውን ክፍያ ከከፈለ በኋላ፣ ከአስፈጻሚ ውል ጋር የተያያዘ አስቸጋሪ ሁኔታ (force majeure) ካልተፈጠረ በስተቀር፣ በማንኛውም ምክንያት ለደንበኛው ምንም ዐይነት ገንዘብ አይመለስም።
6. የድርጅት ደንበኞች ክላውድን መሠረት ያደረጉ ለጥሪ ማእከላት አገልግሎቶች ቢያንስ የአንድ ዓመት ውል ይፈርማሉ።