ኩባንያችን ከመልቲቾይዝ አፍሪካ ጋር በመመተባበር የዲኤስቲቪ ስትሪሚንግ አገልግሎትን ለኩባንያችን ቤተሰቦች አቀረበ!

ኩባንያችን ከመልቲቾይዝ አፍሪካ ጋር በመተባበር የመዝናኛውን ዘርፍ በእጅጉ ለማዘመን የሚያስችል፤የብሮድባንድ አገልግሎት ተደራሽነቱን የሚጨምር፤ ብሎም የሀገሪቱን የዲጂታል ኮኔክቲቪቲ እና አካታችነትን በእግጉ የሚያግዝ አገልግሎት ከፈጣኑ ፋይበር ብሮድባንድ ኢንተርኔት ጋር ዲኤስቲቪ ስትሪሚንግን በማጣመር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

ይህ አዲሱ አገልግሎት በፈጣኑ ፋይበር ብሮድባንድ ኢንተርኔት አማካኝነት ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የፕሪሚየም መዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ተፈላጊ የስፖርት ቻናሎችን፣ ምርጥ ተከታታይ ፊልሞችን፣ የቀጥታ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ስርጭቶችን፣ ዶክመንተሪዎችን፣ በፍላጎት የሚታዩ ቪዲዮዎችን (Video on Demand)፣ የቤተሰብ መዝናኛዎችን እንዲሁም ሌሎች የአኗኗር ዘይቤ ይዘቶችን በማቅረብ የደንበኞችን የዲጂታል ተሳትፎ ያለገደብ እና በተሻለ የግንኙነት ጥራት ለማቅረብ ያስችላል፡፡

በመሆኑም ኩባንያችን ለሁሉም ሰራተኞች ባላቸው መደበኛ ፋይበር ብሮድባንድ ኢንተርኔት ጥቅማጥቅም (Employees Benefit Package) ላይ በተጨማሪ (add-on) የዲኤስቲቪ ስትሪሚንግ አገልግሎት በቅናሽ ዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁኔታዎችን ያመቻቸ ሲሆን ሁሉም አዲስ ወይም ነባር የመደበኛ ብሮድባንድ ኢንተርኔት ያላቸው ሰራተኞቻችን በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የኩባንያችን አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመሄድ የዲኤስቲቪ ጥቅል አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ስንገልፅ በደስታ ነው።

ለኩባንያችን ቤተሰቦች የቀረበው የዲኤስቲቪ ስትሪሚንግ አገልግሎት ዓይነት እና ወርሃዊ ክፍያው ከዚህ ቀጥሎ ቀርቧል፡፡

ተ.ቁየዲኤስቲቪ ስትሪሚንግ አገልግሎት ስምወርሃዊ የአገልግሎት ዋጋ
1ወርሃዊ የዲኤስቲቪ ስትሪም_ፕሪሚየም4,785.00 ብር
2ወርሃዊ የዲኤስቲቪ ስትሪም_ሜዳ ፕላስ2000.00 ብር
3ወርሃዊ የዲኤስቲቪ ስትሪም_ሜዳ1000.00 ብር
4ወርሃዊ የዲኤስቲቪ ስትሪም_ቤተሰብ609.00 ብር
5ወርሃዊ የዲኤስቲቪ ስትሪም_ጎጆ349.00 ብር

ማሳሰቢያ፡

  • አንድ ሰራተኛ እንደየግል ፍላጎቱ ከአንድ በላይ የዲኤስቲቪ ተጨማሪ ጥቅሎችን መግዛት ይችላል፡፡
  • የኩባንያችን ቤተሰቦች ስማርት ቲቪ (Smart TV) የሌላቸው ከሆነ፣ በቀረቡት የክፍያ አማራጮች መሰረት (ማለትም በ12 ወራት ክፍያ ወይም በአንድ ጊዜ) ስማርት ቲቪ ስቲክ (Smart TV stick) ወይም ሴት-ቶፕ ቦክስ (Set-Top Box) መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
  • የተመረጠው የዲኤስቲቪ ስትሪም ወርሃዊ የአገልግሎት ዋጋ አሁን ባለው የኩባንያችን ወርሃዊ የክፍያ መጠየቂያ (ቢል) ላይ ይካተታል።