ኢትዮ ቴሌኮም እና ሲኔት ሶፍትዌር ቴክኖሎጂ የሲኔት ሶፍትዌር ተጠቃሚ አጋሮች ደንበኞቻቸው የአገልግሎትና የግብይት ክፍያቸውን በቴሌብር አማካኝነት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን አሰራር በዛሬው ዕለት ተግባራዊ ያደረጉ ሲሆን፣ ይህም አሰራር ቴሌብርንና ሲኔት ሶፈትዌርን በማስተሳሰር የሲኔት ሶፍትዌር ተጠቃሚ አጋሮች ደንበኞቻቸው ግብይት ሲያከናውኑ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹና አስተማማኝ የሆነውን የዘመኑን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ቴሌብርን ተጠቅመው የአገልግሎት ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል፡፡

በተለይም ይህ አሰራር የሲኔት ሶፍትዌርን በመጠቀም አገልግሎት የሚሰጡ ሆስፒታሎች፣ ፋርማሲዎች፣ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ካፌዎች፣ ሱፐር ማርኬቶች፣ የመዝናኛና የመስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች መሰል ተቋማት ደንበኞቻቸው ከ25 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚ ደንበኞች ያሉትን ቴሌብርን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የአገልግሎት እና የግብይት ክፍያዎቻቸውን እንዲያከናወኑ ይረዳቸዋል፡፡

በዚህም መሰረት ደንበኞች ለአገልግሎት ወይም ግብይት ክፍያዎችን ለመፈጸም የአገልግሎት ሰጪውን ተቋም/ድርጅት ኪው አር ኮድ (QR code) በማንሳት (scan) እንዲሁም በቅዲሚያ ክፍያቸውን በቴሌብር እንደሚከፍሉ በማሳወቅ በሞባይል ስልካቸው በሚደርሳቸው የክፍያ የሚስጥር ቁጥር ለሂሳብ ባለሙያው/ዋ በመናገር ክፍያቸውን በቴሌብር መተግበሪያ ወይም አጭር ቁጥር (USSD) ሲፈጽሙ ከ127 የክፍያ ማረጋገጫ አጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚደርሳቸው ይሆናል፡፡

ኩባንያችን በቅርቡ #ቴሌብር መላ – የግለሰብ ደንበኞች፣ ነጋዴዎች እንዲሁም ወኪሎች የአነስተኛ ብድር አገልግሎት በቴሌብር አካውንታቸው አማካኝነት የሚያገኙበት፣ #ቴሌብር እንደኪሴ የቴሌብር ደንበኞች በአካውንታቸው ላይ ያላቸው ቀሪ የሂሳብ መጠን በቂ ባልሆነበት ጊዜ የሚጠቀሙት እንዲሁም #ቴሌብር ሳንዱቅደንበኞች ከወለድ ነጻ ወይም የተለያየ የወለድ መጠን የሚታሰብባቸው የቁጠባ ዓይነቶችን የሚጠቀሙበት ሲሆን አገልግሎቶቹን ከዳሸን ባንክ ጋር በአጋርነት ፋይናንስ ለሁሉም በሚል መርህ በማቅረብ የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ ላይ ይገኛል፡፡

ኩባንያችን በቴሌብር አገልግሎት እስከ አሁን ድረስ 25.85 ሚሊዮን ደንበኞችን፣ 101 ዋና ወኪሎችን (Master Agents) ፣ 87 ሺህ ወኪሎች 23 ሺህ ነጋዴዎች /Merchants/ ማፍራት የቻለ ሲሆን፣ ከ153 ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ማስተናገድ (Transaction Value) ችሏል፡፡ በተጨማሪም ከ17 ባንኮች ጋር ትስስር (Integration) በማድረግ ከባንክ ወደ ቴሌብር ገንዘብ ማስተላለፍ የተቻለ ሲሆን፣ ከ14 ባንኮች ጋር ደግሞ ከቴሌብር ወደ ባንክ የገንዘብ ዝውውር እየተደረገ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩልም ከበርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ድርጅቶች ጋር ስምምነት በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የክፍያ ስርአታቸውን በማቀላጠፍ ለተቋማቱም ሆነ ደንበኞቻቸው እፎይታን አጎናጽፏል፡፡

በቀጣይ ጊዜያትም ኩባንያችን ከሌሎች መሰል ተቋማት ጋር በመተባበር የክፍያ ስርዓታቸውን በቴሌብር የሚተገብሩበትን አሰራር በማመቻቸት ደንበኞቻቸው የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እና የቴሌብር ደንበኞች በአንድ ስርዓት ሁሉንም ክፍያ ባሉበት ሆነው እንዲፈጽሙ ለማድረግ እና የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ ዕውን የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እናረጋግጣለን፡፡

ህዳር 15 ቀን ቀን 2015 .

ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin

Follow Us

Recent Posts

Archives