የስድስት ተጨማሪ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን የእጣ አወጣጥ መርሃ ግብርም አከናውኗል!
ኩባንያችን 130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለደንበኞች ባዘጋጀው የኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ እና ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሃ ግብር ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ሲያበረክት መቆየቱ ይታወቃለ፡፡ በዛሬው ዕለትም ዕጣ ለወጣላቸው የአዲስ አበባ እና የጅማ ባለ እድለኞች ሁለት ዘመናዊ የቢ.ዋይ.ዲ የኤሌክትሪክ መኪኖችን ቁልፍ በቃሉ መሠረት አስረክቧል፡፡
ኩባንያችን የ130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን በማስመልከት ለ65 ሳምንታት፣ 4 የኤሌክትሪክ መኪኖችን ለአዲስ አበባ፣ ለአዳማ እና ለወሊሶ ባለ እድለኞች እንዲሁም 13 ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን ለአርባምንጭ፣ ሀረር፣ አርሲ ነጌሌ፣ አዲስ አበባ፣ ለሆሳእና፣ አዳማ፣ አዋሳ፣ ወልቂጤ እና ቦንጋ ባለእድለኛ ደንበኞቻችን ቁልፍ ማስረከቡ ይታወሳል፡፡
በተጨማሪም 372 ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን፣ በየቀኑ እና በየሳምንቱ በድምሩ 40.8 ሚሊዮን ብር በቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ለ2,059 ደንበኞቻችን እንዲሁም ከ2.7 ሚሊዮን በላይ የሞባይል ጥቅሎችን ጨምሮ እስካሁን ከ127.8 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ሽልማቶችን አበርክቷል።
በዛሬው እለትም የመጨረሻዎቹን ስድስት ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖችን እጣ የማውጣት መርሃ ግብር የኩባንያችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ተወካዮች፣ የሚዲያ አጋሮቻችን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እና በቀጥታ ስርጭት በኩባንያችን ማህበራዊ ሚዲያ ሁሉም ድንበኞቻችን በተከታተሉት መርሃ ግብሩ ተከናውኗል፡፡በዚህም አሸናፊዎች የተለዩ በመሆኑ በቀጣይ በሚደረግ ዝግጅት ሰድስቱን መኪኖች ለባለ እድለኞች የምናስረክብ ይሆናል፡፡
ታህሳስ 25 ቀን 2018 ዓ.ም
ኢትዮ ቴሌኮም




