የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር SC/L/WRM/002/2017 እና FD/A&FR/01/2017

ኢትዮ ቴሌኮም ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ የተለያዩ ጀነሬተሮች፣ የተለያዩ የእጅ ሞባይሎች ቀፎዎች፤ የቤት ስልኮች እና ሞደሞች፣ የፓወር እና ኔትዎርክ ስፔር ፓርቶች፣ የፊክስድ ኔትዎርክ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ዐይነት ዴስክ ቶፕ  ኮምፒውተር ሲፒዩ እና ሞኒተሮች፣ የተለያዩ  ዓይነት ራኮች፣ የኔትዎርክ አንቴናዎች፣ ያገለገሉ ትራንሰፎርመሮች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ፕሪንተሮች፣ ፋክስ ማሽኖች፤ ሲግኒቸር ፓዶች፤ ስካነሮች እና የኮምፒውተር አክሰሰሪዎች፣ ያገለገሉ ላፕቶፖች፣ የተለያዩ የፋሲሊቲ ዕቃዎች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ የተለያዩ አዳዲስ የከባድ እና የቀላል የመኪና ስፔር ፓርቶች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ሰርቨሮች እና የሰርቨር ራኮች፣ የተለያዩ የአይሲቲ ስፔር ፓርቶች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ስክራኘ የፖል እንጨቶችን  ባሉበት ቦታና ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ  በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት ከኦክሽን ኢትዮጵያ ዌብ ሳይት ወይም ከኦክሽን ኢትዮጰያ መተግበረሪያ በመግባት መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ንብረቶቹን መመልከት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ ተጫራቾች አቃቂ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ግምጃ ቤት፣ በወሎ ሰፈር በሚገኘው የኩባንያው ዕቃ ግምጃ ቤቶች እና በቴሌ ጋራጅ እንዲሁም በምስራቅ አዲስ አበባ (ገርጂ) እና በምዕራብ አዲስ አበባ (አስኮ) በመገኘት የታደሰ መታወቂያችሁን በመያዝ መጎብኘትና መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብ መወዳደር ይችላሉ፡፡

የኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ በኦክሽን ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል 9164 / 09-0511-5511 ወይም 0116-66-8828 ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡

ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on reddit
Share on pinterest
Share on tumblr
Share on whatsapp

Follow Us

Recent Posts

Archives