ለሎጂስቲክስ አቅራቢዎች፣ ለሞተር ሳይክል ማህበራት/አሽከርካሪዎች እና ለብስክሌት አሽከርካሪዎች፤ በጋራ ለመሥራት የቀረበ ጥሪ!

የፍላጎት ማሳወቂያ ጊዜ፡ ከጥር 16 – የካቲት 6፣ 2018 ዓ.ም

ኢትዮ ቴሌኮም የዘመን ገበያን የአቅርቦት አገልግሎት አድማስን ለማስፋት ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት: የተለያዩ ምርቶችን ለደንበኞች  የማድረስ፣ ወደ ግምጃ ቤት የማጓጓዝ እና ተመላሽ ትእዛዞችን የማድረስ አገልግሎቶችን ማቅረብ ከሚችሉ አጋሮች ጋር በጋራ ለመስራት ጥሪውን ያቀርባል።

  1. የፍላጎት ማሳወቂያው ዓላማ
  • ከዘመን ገበያ ፍላጎቶች ጋር የተጣጣመ አቅም እና ልምድ  ስለመኖሩ መረጃ ለማሰባሰብ።
  • ውል ስምምነት ብቸኛ አገልገሎት ሰጪ ያልሆኑ ወይም በየአገልገሎቱ በሚፈጸም ክፍያ በሽርክና አብረው መስራት የሚችሉ አገልገሎት ሰጪዎችን አቅም ለመገምገም።

የዚህ የፍላጎት ማሳወቂያ ምላሾች ኩባንያውን የማያስገድዱ ሲሆን፤ ወደ ቀጣይ በሽርክና አብሮ የመስራት ሂደት ሊያመራ የችላል።

  1. የአገልግሎቱ ወሰን

አብሮ ለመስራት የሚመረጡ አጋሮች የሚሰማሩባቸው ስራዎች

  • የትራንስፖርት እና የተለያዩ ምርቶችን ለደንበኞች ማድረስ በሚገኙበት ከተማ ወይም አገር አቋራጭ በከተማ ወይም ገጠር ምርቶችን ማጓጓዝ፣ በአንድ የተጠቃለሉ የተለያዩ ምርቶችን ማጓጓዝ፣ እንዲሁም እንደ ማቀዝቀዣ የሚፈልጉ እና እንሣት የመሳሰሉ ልዩ ጥንቃቄ የሚፈልጉ ጭነቶችን ማጓጓዝ
  • ግምጃ ቤት አገልግሎት፡ የአካባቢ ማከፋፈያ እና የመውሰጃ ማዕከል አገልግሎት
  • ተመላሽ ዛዞችን የማድረስ አገልግሎ
  • ኦፕሬሽን፡ ከዘመን ገበያ የሎጅስቲክስ እና ዲስፓቸር መተግበሪያ ጋር የማስተሳሰር እና በGPS/API መከታተል

ጂኦግራፊያዊ ትኩረት፡- አዲስ አበባ እና የክልል ከተሞች (hyperlocal)፣ የክልል አገናኞች (100-400 ኪ.ሜ)፣ የረጅም ርቀት መስመሮች (300-1,000 ኪ.ሜ) እና የርቀት መዳረሻ።

  1. አስፈላጊ መረጃ

ከታች በተዘረዘሩት የማረጋገጫ ዝርዝሮች መሰረት ምላሽዎን አስፈላጊ ሰነዶችንና የድርጀቱን መረጃ፣ ደጋፊ ሰነዶችን በማደራጀት በፒ.ዲ.ኤፍ በማያያዝ ያቅርቡ

  • ለሶሰተኛ ወገን ሎጅስቲክስ Third-party logistics (3PL)
መስፈርትማብራሪያ/መስፈርትአስፈላጊው ምላሽ
ንግድ ፈቃድየታደሰ ንግድ ፈቃድ/የማኅበር ምዝገባ ፈቃድና የሥራ ልምድ፤የንግድ ፈቃድና የሠሩበትን ዓመት ኮፒ ያቅርቡ።
የአገልግሎት አቅም/ችሎታበቂ የአሽከርካሪ፣ የመጋዘን አገልግሎት፣ የትእዛዝ አፈጻጸምና የመጨረሻ መዳረሻ ስርጭት ማቅረብ

የራስና የሦስተኛ ወገን የተሽከርካሪ ብዛት/ዐይነት፤

የተሽከርካሪ መጠን/ዐይነት (ለምሳሌ ቫኖች፣ የጭነት መኪናዎች)፣ የመጋዘንና የእቃ ማከማቻ ዐቅም (ስኩዌር ሜትር) ዝርዝር፤

ከፍተኛውና ዝቅተኛው የመጫን አቅም በመጠን/በኪ.ግ

ጥያቄ፡ የሥራ ጫና በሚበዛባቸው ቀናት (ለምሳሌ፦ በበዓላት ቀናት) ያለውን ከፍተኛ የሥራ ጫና እንዴት ያስተዳድራሉ?

የጂኦግራፊ ሽፋንትኩረት የተደረገባቸው የሥራ እንቅስቃሴ የሚበዛባቸው የከተማ/የገጠር የኢትዮጵያ ከተሞች

የሚሸፍኑትን ክልሎችና ከተማዎች (ለምሳሌ፦ አዲስ አበባ፣ ድሬደዋ) እና የገጠር አካባቢዎች ሽፋን ፐርሰንት ዝርዝር

ጥያቄ፦ የከተሞችን፣ ብሔራዊ መተላለፊያዎችንና እንቅስቃሴ የሚበዛባቸውን የቦታዎችን ኔትዎርክ መግለጽ፤

ወጪ ቆጣቢነትዋጋን ከሚገመተው የማድረሻ ወጪ ጋር ማጣጣም

ለእያንዳንዱ የአሠራር ዘርፍ ማሳያ ሊሆኑ የሚችሉ የዋጋ ሞዴሎችን ማቅረብ (ለምሳሌ፦ በኪሎሜትር፣ በትዕዛዝ ብዛት)፣ ለከፍተኛ መጠን ትዕዛዞች የሚደረጉ የዋጋ ቅናሾች።

በልዩ ውል ያልተገደቡ (Non-exclusive)፣ በኮንትራት ላይ የተመሰረቱ፣ ወይም በአገልግሎት መጠን ልክ የሚከፈልባቸው (Pay-per-use) ሽርክናዎችን ለመጀመር ያለው ፈቃደኝነት።

የቴክኖሎጂ ወኅደትየዘመን ገበያ የሎጅስቲክ ሥርዐትን/ፖርታልንና የዲስፓቸርን መተገብሪያና ጂ.ፒ.ኤስ መከታተያ መጠቀም

የዘመን ገበያ የዲስፓቸር መተግበሪያን በአሽከርካሪዎች ስልክ ወይም መሣሪያ ላይ ለመጫንና ለመጠቀም ያለው ፈቃደኝነትና ዝግጁነት።

የዘመን ገበያ የጂ.ፒ.ኤስ/የክትትል ሲስተምን መጫን።

ስለ ኤ.ፒ.አይ (API) ወይም የመጋዘን አስተዳደር ሥርዓት (WMS) ውህደት፣ እንዲሁም ስለ ቀጥታ የክትትል መሣሪያዎች ማብራሪያ ይስጡ።

ጥያቄ፦ በአዋጅ ቁጥር 1321/2016 (የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ) መሠረት የመረጃን ደኅንነት እንዴት ያረጋግጣሉ?

የአገልግሎት ተለዋዋጭነትየሚለዋወጡ መጠኖችን ማስተዳደርየሥራ መጠን ሲጨምር (ለምሳሌ፦ ትዕዛዞች ከ50% በላይ ሲጨምሩ) እንዴት እንደተወጣችሁ የሚያሳዩ ተጨባጭ ተሞክሮዎችን/ጥናቶችንና የመጠባበቂያ ዕቅዶች ያቅርቡ።
መልካም ስምና አሰማማኝነትበኢ-ኮሜርስ የታወቀ ልምድ እና ቀድሞ የማድረስ አገልግሎት አፈጻጸም ማስረጃ።ሦስት የድጋፍ ደብዳቤ ዘርዝር፣ የሥራ አፈጻጸም ምስክር ወረቀት፣  የደህንነት/ ከወንጀል ነጻ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ
ልዩ አያያዝየሙቀት መጠን የሚቆጣጣር፣ ከፍተኛ ዋጋ/ከባድ የሆኑ ዕቃዎችየማቀዝቀዣና ወይም ከባድ ዕቃዎችን (ቶሎ የሚበላሹ፣ አደገኛና በቀላሉ የሚሰበሩትን) የመያዝ አቅምዎን ይዘርዝሩ።
ተገዢነት/ሕግን ማክበርየኢትዮጵያ ሕጎችንና መመሪያዎችን ማክበር፤

ሕግ አክባሪነትዎን ያረጋግጡ፡ ካለ የምስክር ወረቀቶችን ያቅርቡ

ጥያቄ: የአሽከርካሪዎችን ሥልጠናና የደንበኞች አያያዝ ጥራት እንዴት ያረጋግጣሉ?

ዘላቂነት አካባቢን የሚጠብቁ አሠራሮች (ለምሳሌ፦ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች፣ የጉዞ መስመሮችተፈጥሮን ለመጠበቅ የምታከናውኗቸውን ተግባራት፣ መቶ በመቶ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንደሚጠቀሙ ያብራሩ።

 

  • ለሞተር ብስክሌት ማህበራት እና ለግል ሞተረኞች

በቂ አባላት ያሏቸውና ዋስትና ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ተግባራቸው ከመመሪያ ቁጥር 155/2024 የሚሄድ ማህበራት ተሳታፊ መሆን ይችላሉ። በተጨማሪም የግል ሞተረኞች በተመሳሳይ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

መስፈርትማብራሪያ/መስፈርትአስፈላጊው ምላሽ
ፍቃድየታደሰ ንግድ ፍቃድ/የማህበር ምዝገባኮፒ ማቅረብ እንዲሁም የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ
የዕዳ ዋስትናየዋስትና ማስያዣ፤ የመንግስት ሰራተኛ ዋስ (ደሞዝ 15,000 ብር እና ከዚያ በላይ የሆነ)የዋስትና ሂደቱን በዝርዝር ያቅርቡ፤ የዋስትና ማስያዣዎችን ይጥቀሱ።
የአገልግሎት ክልልበተመረጡ ዋና ዋና ከተሞችመሰማራት የሚፈልጉበትን ከተማ ይጥቀሱ (ለምሳሌ በአዲስ አበባ ክ/ከተሞች፣ ድሬደዋ፣ ደሴ ወዘተ…) ወደ ገጠር ለመሰማራትም ፈቃደኛ የሆነ
ወጪ ቆጣቢነትከግምት ጋር የተመጣጠነ ዋጋለእያንዳንዱ የሥራ አካባቢ ለማጓጓዝ የሚሆኑ ዋጋዎች ይጥቀሱ(ለምሳሌ፤ በኪ.ሜ)፡፡ ብቸኛ ባልሆኑ፣ በውል ላይ በተመሠረቱ ወይም በተጠቀሙበት ልክ በሚከፈልባቸው (pay-per-use) የአጋርነት ስምምነቶች ለመሥራት ፈቃደኝነትዎን ይግለፁ።
የቴክሎኖጂ አጠቃቀምየዘመን ገበያ ዲስፓቸር አፕሊኬሽን እና ጂፒኤስ አጠቃቀም ማወቅብቁነትዎን ያሳውቁ፤ የክትትል ስርዓታችሁን ይግለጹ (ለምሳሌ፦መገኛ ቦታ፣ የፍጥነት ገደብ ማስጠንቀቂያዎች)
የአገልግሎት ተደራሽነትን የማሳደግ አቅምከፍተኛ የትዕዛዝ መጠኖችን የማስተናገድ ብቃትየሥራ ጫና በሚበዛባቸው ወቅቶች፣ በበዓላትና በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ለመስራት ዝግጁ መሆን
መልካም ስምና ተዓማኝነትጥሩ ደህንነት/ከወንጀል የጸዳ ታሪክ እንዲሁም የደንበኞች ምስክርነት ማጣቀሻስለማህበሩ የተለያዩ ማጣቀሻዎች፣ የአደጋ ታሪክን እንዲሁም የፖሊስ ማስረጃን ያቅርቡ።
የሞተርሳይክል ይዞታየቴክኒክ ብቃት ያላቸው፡፡ የኤሌክትሪክ ሞተሮች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡ዝርዝሮችን ማቅረብ (ለምሳሌ፡ ሞዴል፣ የአገልግሎት ዕድሜ፣  አሁናዊ ሁኔታ)፤ የኤሌክትሪክ ፍጆታ በመቶኛ፡፡  እንዲሁም የደህንነት መጠበቂያዎች መኖራቸውን ያረጋግጡ፡፡
ጥያቄ፦ መመሪያ ቁጥር 155/2024ን እንዴት እንደሚያከብሩ ያሳውቁ፡፡ (ለምሳሌ፦ የዕቃ መጫኛ ሳጥን መጠን ≤ 50x46x46 ሳ.ሜ መሆኑን ያሳውቁ)
ተገዢነትለአዋጅ ቁጥር 1321/2024 እንዲሁም 155/2016/2024 (ለምሳሌ ሄልሜት፣ ተሳፋሪ አለመጫን) ለመሳሰሉት ያሎት ተገዢነት

የደህንነት ስልጠናና የኢንሹራንስ ሽፋን እንዳሎት ያሳውቁ፡፡

ጥያቄ፦ የደንብ ልብስ መስፈርቶችና የጥሰት ቅጣቶችን ይግለጹ።

ዘላቂነትየኤሌክትሪክ ሞተር ሳይክል ቅድሚያ መስጠት

ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የሆኑ አሠራሮች (ለምሳሌ፦ የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመቀነስ የሚደረግ ሥራ

  • ለባለሳይክለኞች (ግለሰቦች)

በከተማ ቦታዎች በአጭር ርቀት ማድረስ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

መስፈርትማብራሪያ/መስፈርትአስፈላጊው ምላሽ
መለያማንነትዎን የሚገልፅ ዶክመንት (ብሔራዊ መታወቂጣ፣ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ)ኮፒ ማቅረብ
የዕዳ ዋስትናየዋስትና ማስያዣ፤ የመንግስት ሰራተኛ ዋስ (ደሞዝ 15,000 ብር እና ከዚያ በላይ የሆነ)ደብዳቤ ማቅረብ
የአገልግሎት ክልልበከተሞችየስራ ቦታዎችን መጥቀስ (ለምሳሌ ቦሌ፣ አራዳ፣ ልደታ፣ ሐዋሳ፣ ባህርዳር፣ መቀሌ ወዘተ…) ርቀቱ 6 ኪ.ሜ እና ከዛ በታች
ወጪ ቆጣቢነትከግምት ጋር የተመጣጠነ ዋጋለእያንዳንዱ የሥራ አካባቢ ለአነስተኛ ዕቃዎች ለማጓጓዝ የሚሆን ዋጋዎች ይጥቀሱ። ብቸኛ ባልሆኑ፣ በውል ላይ በተመሠረቱ ወይም በተጠቀሙበት ልክ በሚከፈልባቸው (pay-per-use) የአጋርነት ስምምነቶች ለመሥራት ፈቃደኝነትዎን ይግለፁ።
የቴክሎኖጂ አጠቃቀምየዘመን ገበያ ዲስፓቸር አፕሊኬሽን እና ጂፒኤስ አጠቃቀም ማወቅብቁ መሆንዎን ያረጋግጡ
የአገልግሎት ተደራሽነትን የማሳደግ አቅምየተለያዩ ለውጦችን ተቋቁሞ መስራትየሥራ ጫና በሚበዛባቸው ወቅቶች፣ በበዓላትና በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ለመስራት ዝግጁ መሆን
የባይስክል ሁኔታ እና የደህንነት መጠበቂያ መሳሪያዎች መሟላትየቴክኒክ ብቃት፣ የቅርብ ጊዜ ስሪት፣ የሳይክል ደህንነት መጠበቂያዎች (ጓንት፣ ሄልሜት፣ መስታወት፣ አንፀባራቂ ቁሳቁሶች፣ የክርንና የጉልበት መከላከያዎች)ዝርዝሮችን ማቅረብ (ለምሳሌ፡ ሞዴል፣ የአገልግሎት ዕድሜ፣  ዓይነት፣ የጥገና ታሪክ) እንዲሁም የደህንነት መጠበቂያዎች መኖራቸውን ያረጋግጡ፡፡
ተገዢነትለአዋጅ ቁጥር 1321/2024 እንዲሁም ለሌሎች ተያያዥ ደንብና ሁኔታዎች ተገዢ መሆን፡፡ብቁ መሆንዎን ያረጋግጡ፣ የደህንነት ስልጠናና ኢንሹራንስ

 ፍላጎትን ለማሳወቅ

  • ይዘት: በPDF
  • የሚያበቃበት ቀን: እስከ የካቲት 6 ቀን 2018 (ከሰኞ እስከ አርብ) በታሸገ ኤንቨሎፕ ያስገቡ
  • ፍላጎትዎን የሚያሳውቁባቸው ቦታዎች:
  • አዲስ አበባ: በኢትዮ ቴሌኮም የፍሊት ማኔጅመንት ዲፓርትመንት ቢሮ፣ ድል በትግል ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ የምስራች ኤፍሬም
  • ወላይታ ሶዶ: የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 105 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ በለጠ ሌንዲዶ
  • ባህርዳር: የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 203 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ዮናስ አዝመራው
  • ደብረብርሃን: የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 407 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ አዲሱ ማንደፍሮ
  • ሐዋሳ: የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 104 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ደበበ ሳሙኤል
  • ደሴ: የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 210 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ መራጊያው አስማረ
  • አሶሳ፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 203 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ሙሉዋስ አሰጌ
  • መቀሌ፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 212 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ወለደብርሃን መናስዎ
  • ድሬደዋ፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 02 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ዳዊት ታሪኩ
  • ጅማ፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 104 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ተመስገን በንቲ
  • ጋምቤላ፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 104 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ፓኖም ጀምስ
  • ነቀምት፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 407 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ጌታሁን ታሲሳ
  • ጅግጅጋ፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 204 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ አህመድ ሁሴን
  • ጎንደር፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 406 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ አብርሃም አዲስ
  • ሰመራ፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 102 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ አህመድ ያሂ
  • አምቦ፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 109 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ዱጋሳ አብዲሳ
  • አዳማ፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 502 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ፈንታሁም ታምሬ
  • ሮቤ፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 110 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ሞሀመድ ቡንቲ
  • ሐረር፡ የኢትዮ ቴሌኮም ሪጅናል ቢሮ ቁጥር 406 በስራ ቀንና ሰዓት ብቻ መረጃዎን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጠሪ፡ ዳኛቸው ክፍሌ

ጥያቄ አሎት? ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም በፊት በኢሜይል አድራሻ tesfaye.agza@ethiotelecom.et ይላኩ፡፡ ለተላኩት ጥያቄዎች የተሰጡትን ምላሾች ለሁሉም ተሳታፊዎችን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

  1. ሚስጥራዊነትና ማስተባበያ

የፍላጎት ማሳወቂያ ምላሾች ኩባንያውን የማያስገድዱ ሲሆን፤ ወደ ቀጣይ በሽርክና አብሮ የመስራት ሂደት ሊያመራ ይችላል። 

Share This Post:

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on reddit
Share on pinterest
Share on tumblr
Share on whatsapp

Follow Us

Recent Posts

Archives