ለዕቃዎች እና አገልግሎቶች ይክፈሉ

ለገዟቸው ዕቃዎች እና ለሚያገኟቸው አገልግሎቶች በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ስካን (Scan) በማድረግ በቴሌብር አካውንትዎ ሂሳብዎን በቀላሉ ይክፈሉ።

በተጨማሪም ደንበኞች ከሆቴሎች፣ ጂምናዜሞች፣ ታክሲዎች፣ የውበት ሳሎኖች፣ ግሮሰሪዎች እና ሌሎች የንግድ እና የመንግስት ድርጅቶች ላገኙት አገልግሎት በቀላሉ ክፍያቸውን መክፈል ይችላሉ።

በቴሌብር ገንዘብ እንዴት ማስቀመጥ ይችላሉ?

  • *127# ይደውሉ ወይም ወደ ቴሌብር የሞባይል መተግበሪያ ይግቡ
  • ‘ለነጋዴ ይክፈሉ’ የሚለውን ይምረጡ;
  • የQR ኮዱን ያንሱ (Scan) ያድርጉ ወይም የነጋዴውን መለያ ቁጥር ያስገቡ።
  • የገንዘቡን መጠንያስገቡ
  • የሚስጥር ቁጥር (PIN) ያስገቡ
  • ክፍያ መፈጸምዎን ያረጋግጡ